Get Mystery Box with random crypto!

Christian Tadele Tsegaye

የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye C
የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye
የሰርጥ አድራሻ: @marheirgebrye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.97K
የሰርጥ መግለጫ

This channel serves as a platform to reflect political and socio-economic views of Christian Tadele Tsegaye.

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-04-14 07:46:06 የመቃብር ጠባቂዎች ኃይል ትንሳዔውን አላስቀረውም፤
*
በቅድሚያ በአገር ውስጥና በውጭ ለምትገኙ ለመላው ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊያት እንኳን ለ2015 ዓ.ም የስቅለትና የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና የትንሳዔ በዓል ነው፡፡ ትንሳዔ የሚለው ቃል በክርስትና ኃይማኖት አስተምኅሮ መሰረት «መነሳት» ማለት ሲሆን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥ አዳም በሳተ ጊዜ፥ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ብሎ በገባለት ቃል መሰረት በቀራኒዮ ተሰቅሎ በ3ኛው ሌሊት «መግነዝ ፍቱልኝ፥ መቃብር ክፈቱልኝ» ሳይልና የመቃብር ጠባቂዎች ኃይል ሳያግደው ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱን የምናበስርበትና የምናስብበት የፍቅር፣ የደስታና የድል በዓል ነው።

የትንሳዔ በዓል ኃቅንና እውነትን ወግነው ለቆሙ ሁሉ ከሞት አጠገብ ሕይወት፤ ከመቃብር አጠገብ ትንሳዔ መኖሩን የምናስብበት፤ ፈጣሪ ለሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞታችንን በሞቱ ድል አድርጎ የመዳንን ጸጋ ያገኘንበት፤ ስለ ፍቅር የሚከፈለውን መራራ መስዋእትነትን ያየንበት፤ ትኅትናንና ይቅር ባይነትን የምንማርበት ታላቅ በዓል ነው፡፡

ትንሳዔ የተስፋ መሟሸሽንና ሞትን የማሸነፍ በዓል ነው፤ በእለተ አርብ በጦር ጉልበታቸው የሚተማመኑ ሮማውያንና ሁሉን እናውቃለን በሚሉ ፈሪሳውያን የሀሰት ክስና ፍርድ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መዋሉን ተከትሎ ፀሐይ የጨለመችበት፣ ጨረቃ ደም የለበሰችበት፣ ከዋክብት የረገፉበት እና ሞት የነገሰበት እንዲሁም ብዙዎች ተስፋ የቆረጡበት እለት ነበር፡፡ የጌታ ትንሳዔ በመከራና በጨለማ ውስጥም ሆነው ኃቅንና እውነትን ወግነው ለቆሙትና በጽናት ለጠበቁት ግን ከጨለመችው ፀሐይ ባሻገር አማናዊ ብርሃን፣ ደም ከለበሰችው ጨረቃ ባሻገር በደሙ የሚድኑ የሰው ልጆች መኖራቸውን፣ ከረግፉ ከዋክብት ባሻገር በሞቱ ሞትን ድል የሚነሳ አምላክ መኖሩን ያዩበት የድል እለት ነው፡፡

ዛሬ ላይ የዘመናችን መቃብር ጠባቂዎች የሕዝባችንን ፈተና በማብዛት እጅግ አስከፊ ለሆነ ሰቆቃ ዳርገውት ይገኛሉ። ይኼ ፈተና ትናንትም የነበረ፤ ዛሬም የቀጠለ፤…ነገ ግን በብርቱ የጋራ ትግላችን ወደ የሁሉም፥ በሁሉም የሆነች ፍትኅ የሰፈነባት፣ ነፃነት የለመለመባት፣ እኩልነት የተንሰራፋባትና ዴሞክራሲ የዳበረባት ኢትዮጵያን እውን በማድረግ በድል የምንደምቅበት ይሆናል። ነገ የሌላቸው አካላት ዛሬያችንን ቢያበላሹትም፤ ትናንት የሌላቸው ሰዎች ለትዝታ አልቦነት ደዌያቸው ፈውስ ዛሬያችንን ቢያጠለሹትም፥ ከአምላክ ጋር ወጀቡን በድል ተሻግረን በትንሳዔያችን እንደምቃለን። ይኼ ተጠየቅ የማይቀርብበት እውነታ ነው። በትናንታችን ብቻ ሳይሆን በነጋችንም ብሩኅ ተስፋ የሚቀኑ የጥፋት ማኅበርተኞች ከዚህም በላይ በብርቱ እንደሚፈትኑን ለኃቅ የቀረበ ግምት ነው። ፈተናው በበረታ ቁጥር ትንሳዔያችን እየቀረበ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነውና፥ በጽናት እንበርታ።

የመቃብር ጠባቂዎች ኃይልና ብርታት የክርስቶስን ትንሳዔ እንዳላስቀረው ሁሉ፤ የዘመናችን መቃብር ጠባቂዎች የሕዝባችንን የፍትኅ፣ የነፃነት፣ የእኩልነትና የዴሞክራሲ ትንሳዔ የማርዘም ካልሆነ የማስቀረት አቅም ከቶውንም ሊኖራቸው አይችልም። ትንሳዔው እንደማይቀር፤ ያለስቅለትም ትንሳዔ እንደማይኖር እሙን ነው። ከተባበርን፣ ከተናበብን፣ ከተደማመጥንና በጋር ጸንተን ቆመን የሕዝባችንን አቅም በሚገባ መጠቀም ከቻልን፥ በስቅለቱና በመከራው መጨረሻ ሕዝባችን ትንሳዔን ሲጎናፀፍ፥ የሕዝባችን ጠላቶች ደግሞ የኃፍረትን ማቅን ይለብሳሉ።

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳዔ በዓልን ስናከብር አንድነታችንን በማጠናከር፤ ቤት ንብረት ወድሞባቸው የተፈናቀሉትን፣ ተንከባካቢ የሚሹ አረጋውያንን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ የኑሮ ሁኔታ ያልተሟላላቸውን እንዲሁም የታመሙና በእስር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን በመጠየቅ እንዲሆን የአደራ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።

መልካም የስቅለትና ትንሳዔ በዓል!
4.9K views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 12:14:30
5.2K views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 12:14:23 4) የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሕዝባቸውና የቁርጥ ቀን ባለውለታቸው በሆነው ልዩ ኃይል ላይ የሚወስዱትን እርምጃ እንዲያቆሙና ወደ ካምፓቸው እንዲመለሱ፤ በተለይም የአማራ ልዩ ኃይል አባላት የአገር አንድነት የመጨረሻ ምሽግ ከሆነው የመከላከያ ኃይል ጋር ወደ ግጭት የሚያስገቡ ጉዳዮችን በማስወገድ ተረጋግተውና አንድነታቸውን ጠብቀው በካምፓቸው እንዲሰበሰቡ፤ የአማራ ሕዝብ ለልዩ ኃይሉ ተገቢውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርግ፤ መላው ኢትዮጵያውያንም የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴን ኢሕገመንግስታዊ አገር አፍራሽ እርምጃ በአንድነት እንድታወግዙ ጥሪያቸንን እናቀርባለን።

5) የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ልኂቃን፣ ሚዲያዎችና የማኅበረሰብ አንቂዎች ግጭት አባባሽ ከሆኑ ጉዳዮች በመታቀብ የገዥውን ፓርቲ ፋሽስታዊ እርምጃዎች በመርሕና ሕግ በመመርኮዝ በጽናት ትታገሉ ዘንድ ከአደራ ጭምር ጥሪያችንን እናቀርባለን።

6) የዓለምአቀፍና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ የብልጽግና ፓርቲ ከገባበት አገርን የማፍረስ እኩይ ተልእኮው በመታቀብ ሕግ አክብሮ እንዲንቀሳቀስ፤ በየጊዜው ግጭቶችን እየጠመቀ በንፁኃን ላይ የሚያደርሰውን የዘር ፍጅትና ማንነት ተኮር ጅምላ ጭፍጨፋዎች እንዲያቆም፤ የሰብአዊ መብቶችን አክብሮ የመንቀሳቀስ ዓለምአቀፋዊ መርሆ እንዲያከብር አስፈላጊ እርምጃዎችን ሁሉ በመውሰድ ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን። ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ዓለምአቀፍ ማኅበረሰቡ በሩዋንዳ የዘር ፍጅት የፈፀመውን ታሪካዊ ስህተት እንደሚደግም ማስጠንቀቅ እንፈልጋለን።


ሚያዝያ 03፣2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ፥ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ
5.1K views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 12:14:23 የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የክልል ልዩ ኃይሎች እንዲፈርሱ ያሳለፈውን ውሳኔ በፌዴራል መንግስት ስምና በመከላከያ ሰራዊት የኃይል እርምጃ ለማስፈፀም የሚያደርገውን ፋሽስታዊ እርምጃ ሊያቆም ይገባል፤

ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ባለፉት አስርት ዓመታት በተለይም ባለፉት አምስት ዓመታተ እጅግ አስከፊ በሆነ ርሀብና ጠኔ፣ ስደትና መፈናቀል፣ ማንነት ተኮር ጅምላ ግድያዎችና የዘር ፍጅቶች እንዲሁም በማያባሩ ግጭቶችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ውስጥ ይገኛሉ። ሕዝባዊ የፍትኅ፣ የእኩልነት፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ሲበረቱበት የኢሕአዴግ አገዛዝ የሄደባቸውን የጥፋትና አገር የማፍረስ እኩይ ስምሪቶች የመንፈስ ግብር ወራሹ የሆነው ገዥው የብልጽግና ፓርቲም ዓይነትና መጠናቸውን አሳድጎ ቀጥሎባቸዋል። ፓርቲውና የፓርቲው አመራሮች በአመራር ስልታቸውና ብቃታቸው ላይ እንደአካልና ግለሰብ የሚቀርቡባቸውን ጥያቄዎችና ትቺቶች የብሔርና ኃይማኖት ቅርጽ በመስጠት ነቀፌታዎቹ የሆነ ብሔርና ኃይማኖት ላይ የቀረቡ በማስመሰል ወደለየለት ሕዝብን በሕዝብ ላይ የሚያነሳሳ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ ገብቷል። አገዛዙ ግጭትን እንደኅልውና ማስቀጠያ መሣሪያ እየተጠቀመበት ይገኛል።
ለአብነትም የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በመጋቢት፣2015 ዓ/ም የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀትን በተመለከተ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ አገራችን ከነበረችበት አንፃራዊ መረጋጋት፣ ሰላምና ተስፋ መፈንጠቅ ወደ ትርምስ፣ ስጋትና የመበተን አደጋ ገብታለች። ይህንንም ተከትሎ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በጎ እሳቤ ያላቸው ወገኖች ሁሉ ገዥው ፓርቲ የወሰነውን አስተውሎት የጎደለው ውሳኔ እንዲያጤነው ደጋግመው ቢወተውቱም ካፈርሁ አይመልሰኝ በሚመስል ጎረምሳዊ ግብር ውሳኔውን የተቹ ንቁ ዜጎችን የመንግስት የፀጥታ መዋቅሮችን በመጠቀም ወደ ማፈን ተሸጋግሯል፤ የአገር መከላከያ ሰራዊቱንም ከሕግና ሕገመንግስታዊ መርሆዎች ባፈነገጠ መልኩ በፓርቲ ጥርነፋ በማስገባት በሕዝብና የክልል መንግስት መዋቅሮች ላይ በይፋ በማዝመት በንፁኃን ላይ ግድያና አፈናዎችን በመፈፀም ላይ ይገኛል።

በዚህም በ6ኛው ዙር ምርጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል ሆነን በእንደራሴነት የተመረጥን እኛ፦
1) የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ
2) የተከበሩ ክርስቲያን ታደለ
3) የተከበሩ ሙሉቀን አሰፋ
4) የተከበሩ አበባው ደሳለው እና
5) የተከበሩ ዘመነ ኃይሉ

የብልጽግና ፓርቲ፤ በመረጠን ሕዝባችን ላይ እየፈፀመ ያለውን ፋሽዝም በጽኑ እያወገዝን፤የተፈፀሙ ሕገመንግስታዊ ጥሰቶቸንና መደረግ ያለባቸውን ምክረሐሳቦች እንደሚከተለው እናቀርበቀለን።

1) ብልጽግና ፓርቲ እንደሌሎች የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁሉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ሆኖ ሳለ፤ በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የክልል ልዩ ኃይሎችን በተመለከተ ያስተላለፈው ውሳኔ በየትኛውም የአገሪቱ ሕግ ለፓርቲው በሥልጣንነት ያልተፈቀደ ሆኖ አግኝተነዋል። የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ ፓርቲው ሕገመንግስታዊ የመንግስትና ሕዝብ ተቋማትን እንደፓርቲው አደረጃጀት የቆጠረ፤ ለብቻው በፓርቲ ደረጃ በሕዝብና መንግስት ተቋማት ላይ አዛዥ ናዛዥ እንደሆነ አድርጎ ያቀረበ በመሆኑ ከሕግ፣ ሞራልና አሰራር አንፃር ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑም ባሻገር በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የታጠቀ ኃይል ማንቀሳቀስ የማይችሉ መሆናቸውን የሚደነግገውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር የተመለከተውን አዋጅ ቁጥር 1162/2011 የተላለፈ ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይኸንኑ የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሕግ የጣሰ ውሳኔ በመርመር በፓርቲው ላይ ተገቢውን የሕግ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን።

2) በኢፌዴሪ ሕገመንግስት የክልሎችን ሥልጣን በሚደነግገው አንቀጽ 52/2/ሰ ሥር «የክልሉን ፖሊስ ኃይል ያደራጃል፤ ይመራል፤ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ ያስጠብቃል» በማለት ክልሎች የየራሳቸውን የፖሊስ ኃይል የማደራጀት ሕገመንግስታዊ መብት እንዳላቸውና አደረጃጀቱና አመራሩም በራሳቸው የሚወሰን መሆኑን በማያሻማ መልኩ ያስቀምጣል። የክልል ልዩ ኃይሎች በክልል መንግስታት ምክርቤቶች በኩል በአዋጅ የተቋቋመው የፖሊስ ኃይል አካል ሲሆኑ ተጠሪነታቸውም ለየክልሎቹ ፖሊስ ኮሚሽኖች ነው። ሰይጣን ላመሉ ከመጽሐፍ ያጣቅሳል እንዲሉ የብልጽግና ፓርቲ ክልሎች የመደበኛ ፖሊስ ብቻ ነው የተፈቀደላቸው የሚል የዓይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ሙግት ቢያቀርብም ቅሉ፤ እንደኃይማኖታዊ ቅዱስ መጽሐፍ በሚያመልከው የኢፌዴሪ ሕገመንግስት ውስጥ አንድም ቦታ መደበኛ ፖሊስ ብቻ ስለመፈቀዱ የሚያትት የሕግ ድንጋጌ የለውም። ይልቁንም በዚሁ ሕገመንግስት አንቀጽ 52/1 ላይ «ለፌዴራል መንግስት በተለይ ወይም ለፌዴራሉ መንግስትና ለክልሎች በጋራ በግልጽ ያልተሰጠ ሥልጣን የክልል ሥልጣን ይሆናል» የሚለው ድንጋጌ «የልዩ ኃይል ፖሊሰ» ማቋቋምን የክልሎች ልዩ መብት አድርጎ የሚያስቀምጥ ነው። የክልሎች የልዩ ኃይል አደረጃጀት ሕገመንግስታዊ አይደለም ቢባል እንኳን በአንድ ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውሳኔ ሳይሆን ባቋቋሟቸው የክልል መንግስታት በኩል የማቋቋሚያ አዋጆቻቸው ማስተካከያ እንዲደረግበት ተደርጎ የሕግ ክፍተቱ  የሚታረም ሆኖ መሰል መብቶች ለክልሎች የተተው መሆናቸው ተጠየቅ የሚቀርብባቸው አይሆኑም።

3) የፌዴራል መንግስቱና የአገር መከላከያ ሰራዊት የአንድ ፓርቲ የግል ንብረቶች አለመሆናቸው እየታወቀ በተለይም በኢፌዴሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 87 ስለመከላከያ መርሆዎች በሚያትተው ንዑስ አንቀጽ 5 «የመከላከያ ሰራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ያከናውናል» የሚለውን ድንጋጌ በመጣስ እንዲሁም የአገር መከላከያ ሰራዊት በፖሊስ ሰራዊት በተለይም በክልሎች የፖሊስ አደረጃጀት ላይ ውሳኔ ለመስጠትና ማስተካከያ ለማድረግ የሕግ ሥልጣን ሳይኖረው በመረጠን ሕዝብና በራሱ በጀት በሚያስተዳድራቸው ሕዝባዊ ተቋማቱ ላይ የታወጀው ጦርነት የለየለት ፋሽስታዊ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል። ጣልቃገብነቶችም በኢፌዴሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 51/14፣ 55/16 እና 62/9 መሰረት የተከናወኑ ባለመሆናቸው ግልጽ ሕገመንግስታዊ ጥሰቶችና አገር አፍራሽ ተልእኮዎች ናቸው።  የፌዴራል መንግስቱ በክልሎች ላይ በተለይም በአማራ ክልል እያደረገ ያለው ጣልቃገብነት የብልጽግና ፓርቲ በመቃብሬ ካልሆነ አልደራደርባቸውም የሚልላቸውን ፌዴራሊዝምና የኢፌዴሪ ሕገመንግስት ጭምር ገደል የከተተ ነው። በተለይም ሰራዊቱ በማናቸውም ጊዜ ለሕገመንግስቱ ተገዥ መሆን እንዳለበት የሚደነግገውን አንቀጽ 87/4 ድንጋጌ የሻረ ነው።

በብልጽግና ፓርቲ የተፈፀሙ መሰል የአገር አፍራሽነት ሕገመንግስታዊ ጥሰቶችን የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት፣ የፌዴሬሽን ምክርቤትና መላው ኢትዮጵያውያን በጽኑ እንድታወግዙት ጥሪያችንን እናቀርባለን። በተለይ ሕገመንግስታዊ ሥርዓትን የመጠበቅና የማስጠበቅ የሕግ ግዴታ ያለባችሁ ተቋማት አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ በመውሰድ የብልጽግና ፓርቲን አገር የማፍረስ እኩይ ተልእኮ ታስቆሙ ዘንድ በአጽንዖት እናሳስባለን።
4.5K viewsedited  09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 11:27:44 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከተቃዋሚ የምክርቤት አባላት የተሰጠ መግለጫ።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02Foddm8bo7tLHYsFSZGSb1cJeKfrrzPS1Gupnr9Rhp9CENdhazRxiNJ2zD1gNtw92l&id=100050270028734&mibextid=Nif5oz
4.4K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 08:31:32
2.5K views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 08:31:23 ሲሳይ መሸለም ያለበት ሰው ነው!
****
ከሞቀ ቤታቸው በግፈኞች ለተፈናቀሉ እና ሀብት ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች የእለት ደራሽ ፍጆታዎችን የሚያደርሰው፤ ቀና ሰዎችን በማስተባበር መጠለያ በማስገንባት እናቶችን፣ ሕፃናትንና አረጋውያንን ከሜዳ ያነሳው ሲሳይ አውግቸው (ረ/ፕሮፌሰር) ሕግን ባልተከተለ መንገድ መታሰሩ ተገቢነት የለውም።

ሲሳይ መሸለም እንጂ መታሰር ያለበት ሰው እንዳልሆነ አሳሪዎቹም ያውቁታል። ሕግ አስፈፃሚው የመብት ጥያቄ የሚያቀርቡ ዜጎችን በኃይል ማፈን እንደፋሽን ተያይዞታል። መሰል የሕግ ስነሥርዓትን ያልተከተሉ የአፈናና የኃይል እመቃ እርምጃዎች ከፍ ሲሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፥ ብሎም የዜጎችን ሕገመንግስታዊ መብቶች ማጣበብ መሆናቸውን ለማስታወስ እንወዳለን።
2.5K views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 16:13:50 ከአልፋ ቲቪ ጋር የነበረንን ቆይታ ይከታተሉ።
1.2K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 16:13:50

1.2K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 21:15:48 Channel photo updated
18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ