Get Mystery Box with random crypto!

ሲሳይ መሸለም ያለበት ሰው ነው! **** ከሞቀ ቤታቸው በግፈኞች ለተፈናቀሉ እና ሀብት ንብረታቸው | Christian Tadele Tsegaye

ሲሳይ መሸለም ያለበት ሰው ነው!
****
ከሞቀ ቤታቸው በግፈኞች ለተፈናቀሉ እና ሀብት ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች የእለት ደራሽ ፍጆታዎችን የሚያደርሰው፤ ቀና ሰዎችን በማስተባበር መጠለያ በማስገንባት እናቶችን፣ ሕፃናትንና አረጋውያንን ከሜዳ ያነሳው ሲሳይ አውግቸው (ረ/ፕሮፌሰር) ሕግን ባልተከተለ መንገድ መታሰሩ ተገቢነት የለውም።

ሲሳይ መሸለም እንጂ መታሰር ያለበት ሰው እንዳልሆነ አሳሪዎቹም ያውቁታል። ሕግ አስፈፃሚው የመብት ጥያቄ የሚያቀርቡ ዜጎችን በኃይል ማፈን እንደፋሽን ተያይዞታል። መሰል የሕግ ስነሥርዓትን ያልተከተሉ የአፈናና የኃይል እመቃ እርምጃዎች ከፍ ሲሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፥ ብሎም የዜጎችን ሕገመንግስታዊ መብቶች ማጣበብ መሆናቸውን ለማስታወስ እንወዳለን።