Get Mystery Box with random crypto!

Christian Tadele Tsegaye

የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye C
የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye
የሰርጥ አድራሻ: @marheirgebrye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.97K
የሰርጥ መግለጫ

This channel serves as a platform to reflect political and socio-economic views of Christian Tadele Tsegaye.

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-11-15 18:04:04 ፖለቲካ በተፈጥሮው የግል ጉዳይ አይደለም፤ የጋራ ነው። በጋራ ትግል ውስጥ በግለሰብ ደረጃ የምንጫዎተው ሚና የተለያየ መሆኑ የሚጠበቅ ነው። እንደእንደራሴ በእኛ በኩል በብዙ ፈተናዎች ውስጥ እያለፍንም፥ ለሕዝባችን የገባነውን ቃል አላጠፍንም፤ ከሕዝባችን የተቀበልነውን አደራም አላጎድልንምም።

ከዚህ በተሻለ ለዴሞክራሲ ግንባታ፥ ለሕዝባችንም የፍትኅ፣ እኩልነትና ነፃነት ጥማት የድርሻችንን በጎ ሚና እንጫዎት ዘንድ ግን የሁላችሁንም ድጋፍ እንሻለን።
4.8K views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 10:01:11
5.2K views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 10:01:05 አመሰግናለሁ የተከበሩ አፈጉባዔ፤
አመሰግናለሁ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፤

በመጀመሪያ በምክርቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት በመካከላችን ስለተገኙ ማመስገን እፈልጋለሁ። የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ለመፍታት የፌዴራሉ መንግስትና የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር በደቡብ አፍሪካ በፈረሙት የሰላም ስምምነትም እንደሕዝብ እንደራሴ በበጎ የምመለከተውና ለሕዝባችንም ለጊዜውም ቢሆን እፎይታን የሰጠ በመሆኑ ደስተኛ ነኝ።

ከዚህ በመቀጠል ጥያቄዎችን እንደሚከተለው አቀርባለሁ።
1) በመራጭ ተመራጭ መድረክ በነበረን ውይይት ሕብረተሰቡ የአገራችን መሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለምንድን ነው መጥተው ያልጎበኙን የሚል ጥያቄ አቅርቧል። በተለይም በቋሪት የምርጫ ክልል በቅኔ መፈጠሪያነት በሚታወቀው ዋሸራ ለታሪካዊ የቱሪዝም መስህብነት እጅግ ምቹ ከመሆኑም በላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ታሪካዊውን ቦታ እንዲጎበኙ እና የመዳረሻ ልማት እንዲሰራላቸው ብርቱ ጥያቄ ስላቀረቡ ይህን የሕዝብ ግብዣና አደራ ለማቅረብ ነው። በተመሳሳይ መንገድ በከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ተፈታኝ ተማሪዎች ቁጥር ከአገራችን የመጀመሪያውን ስፍራ የሚይዘው እና ለአገር ኢኮኖሚም ጉልህ ሚና እየተጫወተ ያለው የምዕራብ ጎጃም ዞን ዩኒቨርሲቲ ስላልተከተፈተለት ከፍተኛ ቅሬታ አድሮበታል። ይኼ የዘመናት ዩኒቨርሲቲ ይከፈትልን የሕዝብ ጥያቄን እንዴት ያዩታል?

2) የፌዴራሉ መንግስት በዚህ ምክርቤት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው ትሕነግ ጋር ድርድር አድርጎ ስምምነት ተደርሶ እያለ የመንግስትን አሰራርና አመራር የሚተቹ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እየታፈኑ ለእስር ተዳርገዋል። በአንዳንድ አካባቢዎችም በየአካባቢው የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን እየነቀሱ የፖለቲካ ትግል እያደረጉ ያሉ የአብን አባላትና አመራሮች ጭምር ታፍነው እየታሰሩ ነው። እርስዎ በዚህ ምክርቤት ጭምር በማሸማገልና በማቀራረብ አግዙን ብለው ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት ለአብነት እነአርበኛ ዘመነ ካሴን ለማቀራረብ ጥረት ብናደርግም ይህን በጎ ጥረት መና በሚያስቀርና የቆዬውን የሕዝብ የሽምግልና ወግና ባሕል በሚጥስ መልኩ እስር እየተፈፀመ ነው። መንግስትዎ እነዚህን ቅሬታዎችና ቅራኔዎች በምን መልኩ ለመፍታትና ከሕዝብ ጋር ያለውን መተማመን ለማሳደግ አስቧል?

3) የፌዴራሉ መንግስት ከትሕነግ ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት ስምምነት ያልተደረሰባቸውን አካባቢያዎች «በሕገመንግስታዊ መልኩ ይፈታሉ» የሚል ስምምነት መደረሱን ነግሮናል። ይሁንና አካባቢያዎች (ወልቃይትና ራያ) የኢፌዴሪ ሕገመንግስት ከመጽደቁ በፊት ወደ ትግራይ ክልል በፖለቲካ ውሳኔ የተካለሉ ናቸው። በሁለቱ አካባቢዎች የሚኖረው ሕዝባችን ማንነቱ እንዲከበርለት፣ ባሕሉን እንዲያበለጽግ፣ በቋንቋ ልጆችን እንዲያስተምርና እንዲዳኝ እንዲሁም አስተዳደሩም በማንነት ከሚቀርበው የአማራ ሕዝብ አስተዳደር ጋር እንዲሆን ከ3 አስርት ዓመታት በላይ በሰላማዊ መንገድ ሲታገል ኖሯል። ሕገመንግስታዊ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱ ተደፍቆ ማንነቱ ተፍቆ የኖረው ወገናችን በኃይል በትግራይ ክልል በሚተዳደርበት ዘመን ሁሉ ጅምላ ፍጅትና ማፈናቀልን ጨምሮ የማያባራ ግፍ ሲደርስበት ኖሯል። የቅርቡን ብናስታውስ እንኳን የማይካድራ ጭፍጨፋ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሪፖርት ጭምር ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ መፈፀሙ ተረጋግጧል። ይህ በሆነበት ሁኔታ እነዚህን አካባቢዎች በመስዋእትነታቸው ያረጋገጡትን አንፃራዊ እፎይታ ለአላስፈላጊ ክርክርና ሙግት በሚዳርግ መልኩ ስምምነት መደረሱን እንዴት ያዩታል? 

አመሰግናለሁ!

(በተከበሩ አበባው ደሳለው የጂጋ ምርጫ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ተመራጭ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች)
5.1K views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 18:59:57
2.2K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 18:59:47 የክልል መንግስት አመራሮች በምን አገባብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆኑ?
*
አሁን በሥራ ላይ ባለው ሕገመንግስት የውጭ ጉዳይ ሥራ የፌዴራሉ መንግስት በብቸኝነት (ከክልሎች የማይጋራው) የሚይዘው ሥልጣንና ኃላፊነት ነው። ይሁንና የአንዳንድ ክልሎች አመራሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፌዴራል የሥልጣን እርከን ሥር የሚወድቀውን የውጭ ግንኙነት ሥራ ሲያከናውኑ በዜናዎች መስማት ብርቅ አይደለም። (ምናልባት እንድለማመደው የተፈለገ ጉዳይ ይኖር ይሆን? )

መሰል ግራጫ ሁኔታዎች እስኪፈጠሩ ድረስ የውጭ ጉዳይ ተልእኮ ለክልሎች በውክልና የሚሰጥ አልነበረም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚመራው ስምሪት በሆነ አጋጣሚ የክልል አመራሮች የጉዞው/ተልእኮው አካል ቢሆኑ እንኳን ከታች ፋና ብሮድካስቲንግ በዘገበው መልኩ የውጭ ጉዳይ ሥራን የክልል አመራሮች መሪ ተዋናይ በሚሆኑበት መንገድ ሊከወን አይችልም። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመስሪያ ቤታቸውን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት መሰል ያልተገቡ ጉዳዮችን በተመለከተ ከምክርቤት አባላት ማብራሪያ እንዲሰጡ ሲጠየቁ «ከአሁን በኋላ ክልሎች ቀጥታ የውጭ ግንኙነት እንዳያደርጉ መመሪያ ሰጥተናል» የሚል ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

በአንድ አገር ሁለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይኖርምና፥ መሰል አገር አከል የክልል መንግስታት እና አመራሮቻቸው ተሳትፎ በእንቁላል ዘመናቸው ሊቆረቆቡ ይገባል።
2.2K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 20:19:02 «አላህንም እመን፥ ግመልህንም እሰር።»
ነብዩ መሐመድ (ሰዐወ)

ግመልን ለጅብ፣ ቀበሮና ተኩላ ፈተው ከለቀቁ በኋላ ፈጣሪን ማማረር ዋጋ የለውም። ባይሆን የግመሉ ማሰሪያ ምንድን ይሁን በሚለው ላይ መወያየቱ በጎ ነው። ከአንድነት በላይ ብርቱ ገመድ የለምና፥ ሕዝቤ ሆይ፥ አንድነትህን አጥብቅ!
2.5K views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 15:39:10 በሕዝባዊ ትግላችን ውስጥ የተከፈለልልን ዋጋ በወጉ በማስታወስ፥ በልኩም ድምቀት ሰጥተን፥ ለቀጣዩ ትውልድ የየራሳችንን በጎ አሻራ ልናሳርፍይገባል። የትግል ሀሁው ደግሞ ዋጋ የከፈሉልንን መዘከር ነው።

ከዚህ አንፃር የማይካድራ ጭፍጨፋ በሕዝባችን የፍትሕ፣ እኩልነትና ነፃነት ትግል ውስጥ የሚሰጠው ቦታ ከፍ ያለ ነው። ዛሬ ጥቅምት 30፣ 2015 ዓ/ም የማይካድራ ጭፍጨፋ ከተፈፀመ 2 ዓመታት ሆነው። ቀን የወጣለታ የተሟላ ፍትሕ መስፈኑ አይቀርም። በትንሹ ግን ሰማእትነታችሁን እንዘክረዋለን።

ዘላለማዊ ክብር ለማይካድራ ጭፍጨፋ ሰማእታት ሁሉ!
854 views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 18:13:09 ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው!
****
ታኅሣሥ 2012 ዓ/ም በሕግ ጥላ ሥር መዋሉ የተነገረ ግለሰብ፤ ጥቅምት 2015 በጭካኔ ተገድሎ አስከሬኑ ቱቦ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱን ሰማን። «ገዳይ ነን» ባይ ግለሰቦችም በማኅበራዊ ሚዲያ ፎቶዎችን ለጥፈው ተመለከትን። በወቅቱ አስከሬኑን ተጥሎ ያገኘው የመቄት ወረዳ በወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን የፌስቡክ ገጽ በኩል «ቤተሰብ ነኝ ባይ ቀርቦ አስከሬኑን እንዲወስድ» ማስታወቂያ ካስነገረ በኋላ ማስታወቂያውን አንስቶታል። የጭካኔ ሰለባው ድሬዳዋ ላይ መታሰሩን የነገሩን ሰዎችም ዜናውን በተመሳሳይ መንገድ ማንሳታቸው የሚታወስ ነው።

ከመቄት መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ማስታወቂያ እና «ገዳይ ነን» ከሚሉ ሰዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ግርግር በኋላ ሟች ሻምበል ማማር ጌትነት መሆኑን፤ ግለሰቡ ከሰኔ 15 የአማራ ክልል አመራሮች ጋር በተያያዘ በሕግ ሲፈለግ የነበረ ተጠርጣሪ እንደነበረ ታውቋል። ይኼ መረጃም ለመቄት ወረዳ አስተዳደር በወቅቱ ደርሷል። ይሁንና መረጃው እንደታወቀ አስከሬኑን ለቤተሰቦቹ በመስጠት ፋንታ ወረዳው «ቄሶች መቀበር አለበት ብለው ስላስቸገሩን ገብርኤል ቤተክርስቲያን ቀበርነው» የሚል ምላሽ ሰጥቷል። መቄት ገብርኤል ቀብሩ የተፈፀመው ሻምበል ማማር ጌትነት እነሆ አስከሬኑ ከመቃብር ወጥቶ ለድጋሚ ቀብር መርዓዊ መሸኜቱን እየሰማን ነው።

ይህ ሁሉ ሲሆን በሕግ ጥላ ሥር ዋለ የተባለ ግለሰብ በምን መልኩ ለመሰል የግፍ ግድያ እንደበቃ አንድም የመንግስት አመራር በሚዲያ ማብራሪያ አልሰጠም። ስለግፍ ግድያው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የፎረንሲክ ምርመራ እንዲደረግም አንዳችም ጥረት እየተደረገ አይደለም።

በግሌ ማንም ግለሰብ ተጨባጭ መረጃና ማስረጃ እስከተገኘበት ድረስ ተገቢውን የፍትኅ ቅጣት ማግኘት አለበት ብዬ አምናለሁ። ይሁንና ማንም በየጁ እንደእድር ንፍሮ ፍትኅን ለየራሱ መዝገን ከጀመረ መንግሰትነትን ተጠየቅ ውስጥ የሚያስገባ፤ መጠራጠርን የሚያሰፍን፤ ለወደፊት የጋራ አብሮነት የማይበጅ እንዲሁም በተለይ በፍትኅና ፀጥታ ተቋማት ላይ ዜጎች ያላቸውን እምነት የሚሸረሽር እንደሆነ ይሰማኛል። መሰል ልምምዶችም በጎ አይደሉም። በተለይ ደግሞ «ገዳይ ነኝ» ለሚል የበለጠ በጎ አይሆኑም።

በክብር እረፍ ሻምበል ማማር ጌትነት!
2.7K views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-29 07:24:25 የትኛው ሰልፍ ላይ ነን?
*
ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር ማለት በውሸት መስማማት ማለት አይደለም። ይልቁንም አንድ በሚያደርጉን የጋራ ጉዳዮች ላይ የበለጠ ትኩረት አድርጎ፤ ጊዜ የሚሰጡ ጉዳዮችን በይደር እያቆዩ ለጋራ ግብ በአንድነት መቆም ማለት ነው። ለምሳሌ የቱንም ያህል የአቀራረብና ታክቲክ ልዩነት ቢኖር በሕዝብ ደኅንነትና የአገር አንድነት ላይ የግድ አንድ ልንሆን ይገባል። ፉክክራችን፣ መተጋገላችን፣…ሁሉ፥ አገርና ሕዝብን የበለጠ እጠቅማለሁ በሚል እንጂ በሌላ ሊሆን አይገባም።

የጋራ ግብ የሌለው እንዴት በጋራ ሊቆም ይችላል? ይኼ ከባድ ነው። ለምንድን ነው የምታገለው? ምን ለማሳካት ነው የምታገለው? የምታገልለት ሕልም የማን ሕልም ነው? ሕልሙ እንዲሳካስ የኔ ድርሻ ምንድን ነው? የሚሉ ቀላል የሚመስሉ ግን ደግሞ የግድ ራሳችንን ጠይቀን የግድ ምላሽ ልናገኝባቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። ተመሳሳይ ምላሾች ሳይኖሩን በተመሳሳይ ሰልፍ ውስጥ ከተገኘን ትርፉ መጓተት ነው። ድካም ነው። መቋጫውም ሽንፈትና ውድቀት ነው። አብሮ ለመውደቅ አብሮ አይቆምም። በመሰል ሰልፍ ውስጥ የጋራ ቅዠት እንጂ የጋራ ሕልም ብሎ ነገር አይኖርም። የትኛው ሰልፍ ላይ ነን?
4.2K views04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 07:15:01 ወባን በፓራስታሞል ማከም ከፍተኛ የሆነውን ሙቀት እንዲቀንስ ያግዛል። ሕመሙንም ያስታግሰዋል። ይሁንና ፓራስታሞሉ የወባ ጥገኛ ተዋሕሱን በመደበቅ ለማስወገድ የሚደረገውን የሕክምና ጊዜ ያራዝማል። ተዋሕሱን ለማስወገድ የሚወስደው የተራዘመ ጊዜም ሕመምና ሞትን ያስከትላል።

ከሰሜኑ ጦርነት አኳያ በመፍትሔነት የተወጡኑና እየተደረጉ ያሉ ነገሮች ሁሉ ወባን በፓራስታሞል እንደማከም እንዳይሆኑ ስጋት አለኝ።

የግርጌ ማስታዎሻ፦
1) ፓራስታሞል በተለይ በወባ የታመሙ ሕፃናትን ከፍተኛ ሙቀት ለመቀነስ ጥቅም ላይ ይውላል። ከላይ የቀረበው አብነት የፓራስታሞል ሕክምናውን ጨርሶ ለማጣጣል አይደለም።
2) ወባ እና የወባ በሽታ ተምሳሌትነታቸው ለፖለቲካ ቀውሱ እንጂ የትኛውንም አካል በጋራም ይሁን በተናጠል በተለዋጭ ዘይቤ የሚወክሉ አይደሉም።

ሰላም ለኢትዮጵያና ልጆቿ፥ ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ!
5.5K views04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ