Get Mystery Box with random crypto!

ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው! **** ታኅሣሥ 2012 ዓ/ም በሕግ ጥላ ሥር መዋሉ የተነገረ ግለሰብ፤ | Christian Tadele Tsegaye

ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው!
****
ታኅሣሥ 2012 ዓ/ም በሕግ ጥላ ሥር መዋሉ የተነገረ ግለሰብ፤ ጥቅምት 2015 በጭካኔ ተገድሎ አስከሬኑ ቱቦ ውስጥ ተጥሎ መገኘቱን ሰማን። «ገዳይ ነን» ባይ ግለሰቦችም በማኅበራዊ ሚዲያ ፎቶዎችን ለጥፈው ተመለከትን። በወቅቱ አስከሬኑን ተጥሎ ያገኘው የመቄት ወረዳ በወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን የፌስቡክ ገጽ በኩል «ቤተሰብ ነኝ ባይ ቀርቦ አስከሬኑን እንዲወስድ» ማስታወቂያ ካስነገረ በኋላ ማስታወቂያውን አንስቶታል። የጭካኔ ሰለባው ድሬዳዋ ላይ መታሰሩን የነገሩን ሰዎችም ዜናውን በተመሳሳይ መንገድ ማንሳታቸው የሚታወስ ነው።

ከመቄት መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ማስታወቂያ እና «ገዳይ ነን» ከሚሉ ሰዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ግርግር በኋላ ሟች ሻምበል ማማር ጌትነት መሆኑን፤ ግለሰቡ ከሰኔ 15 የአማራ ክልል አመራሮች ጋር በተያያዘ በሕግ ሲፈለግ የነበረ ተጠርጣሪ እንደነበረ ታውቋል። ይኼ መረጃም ለመቄት ወረዳ አስተዳደር በወቅቱ ደርሷል። ይሁንና መረጃው እንደታወቀ አስከሬኑን ለቤተሰቦቹ በመስጠት ፋንታ ወረዳው «ቄሶች መቀበር አለበት ብለው ስላስቸገሩን ገብርኤል ቤተክርስቲያን ቀበርነው» የሚል ምላሽ ሰጥቷል። መቄት ገብርኤል ቀብሩ የተፈፀመው ሻምበል ማማር ጌትነት እነሆ አስከሬኑ ከመቃብር ወጥቶ ለድጋሚ ቀብር መርዓዊ መሸኜቱን እየሰማን ነው።

ይህ ሁሉ ሲሆን በሕግ ጥላ ሥር ዋለ የተባለ ግለሰብ በምን መልኩ ለመሰል የግፍ ግድያ እንደበቃ አንድም የመንግስት አመራር በሚዲያ ማብራሪያ አልሰጠም። ስለግፍ ግድያው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የፎረንሲክ ምርመራ እንዲደረግም አንዳችም ጥረት እየተደረገ አይደለም።

በግሌ ማንም ግለሰብ ተጨባጭ መረጃና ማስረጃ እስከተገኘበት ድረስ ተገቢውን የፍትኅ ቅጣት ማግኘት አለበት ብዬ አምናለሁ። ይሁንና ማንም በየጁ እንደእድር ንፍሮ ፍትኅን ለየራሱ መዝገን ከጀመረ መንግሰትነትን ተጠየቅ ውስጥ የሚያስገባ፤ መጠራጠርን የሚያሰፍን፤ ለወደፊት የጋራ አብሮነት የማይበጅ እንዲሁም በተለይ በፍትኅና ፀጥታ ተቋማት ላይ ዜጎች ያላቸውን እምነት የሚሸረሽር እንደሆነ ይሰማኛል። መሰል ልምምዶችም በጎ አይደሉም። በተለይ ደግሞ «ገዳይ ነኝ» ለሚል የበለጠ በጎ አይሆኑም።

በክብር እረፍ ሻምበል ማማር ጌትነት!