Get Mystery Box with random crypto!

Christian Tadele Tsegaye

የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye C
የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye
የሰርጥ አድራሻ: @marheirgebrye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.97K
የሰርጥ መግለጫ

This channel serves as a platform to reflect political and socio-economic views of Christian Tadele Tsegaye.

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-09-22 07:55:56
አርበኛ ዘመነን በተመለከተ የመንግስት አመራሮች በሰከነና በተጀመረው መንገድ በሽምግልና እንዲያልቅ ቢያደርጉ ጥቅሙ በዋናነት ለመንግስት መሆኑን ማስታወስ እፈልጋለሁ። ከዚህ ያለፈው ነገር የሽምግልና ወግና ሥርዓቱንም ዋጋ የሚያሳጣ ነው። በተከበረው የአማራ ሕዝብ የሽምግልና እሴት ላይም መዘባበት ይሆናል።

ወንድማችን ዘመነ የማንደራደርበት የሕዝብ ልጅ መሆኑን ግን ሁሉም ሊያውቀው ይገባል።
4.7K views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 20:55:22 የራሔልን እንባ የተመለከትህ አምላክ ሆይ፤ የነሉባባና ተስፋነሽንም እንባ ተመልከት!
****
ደቡብ ኦሞን ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ በሥራ አጋጣሚ አውቀዋለሁ። ሕዝቡ እንግዳ ተቀባይና ብዝኃነትን የኩራቱ ምንጭ አድርጎ የሚኖር እንደነበር በተደጋጋሚ ጊዜ በነበረኝ የመስክ ጉዞዎች ያረጋገጥሁት እውነታ ነው። ይሁንና በፊደላውያን ምክንያት ያ ቱባ ገራገርነት…ያ ኅብራዊነት ውበቱ የነበረ ደግ ሕዝብ…በአፍለኞች ክፉኛ ተፈተነ። አፍለኞች የለኮሱት እሳት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችም የሚተርፉ ወገኖች ነጥፎ የማያውቀውን ማጀታቸውን ወደ ፍርስራሽነት ቀየረው። አፈር ስሆን…ብሉልኝ…ጠጡልኝ…ሲሉ የነበሩ እርብትብት አንደበቶች ስንቱን ፈትፍተው ያጎረሶች መዳፎችን ተመርኩዘው ፈጣሪን ና ውረድ ይላሉ። …።

ግን ለምን? መቼስ ነው የግፍ ጽዋው የሚሞላው? ሁላችንም ለየራሳችን ጠይቀን ለአገርና ለሕዝብ ስንል የግድ በጋራ ልንመልሰው የሚገባን ጥያቄ ነው።

የራሔልን እንባ የተመለከትህ አምላክ ሆይ፥ የእነሉባባና ተስፋነሽንም እንባ ተመልከት!

(ሉባባና ተስፋነሽ ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው የተቀየረ ናቸው።)
8.2K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 10:34:13 የግእዝ ቁጥር ከግሪክ የተወሰደ ነው እንደማለት ከሀዲነትና ድንቁርና በዘመኔ ገጥሞኝ አያውቅም፤ ወደፊትም የሚገጥመኝ አይመስለኝም። ያዘንኩት ግን በአላዋቂዎች ድፍረት አይደለም፤ በአዋቂዎች የፍርኃት ዝምታ እንጂ!
11.5K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 06:39:15 የብልጽግና ፓርቲ ኢመንግስታዊነት እና ኢመደበኝነት!
****
በአገር ጉዳይ ገዥው ፓርቲ ለብቻው ውሳኔ እንዲያሳርፍ እና ከአሸባሪው ትሕነግ ጋር ለብቻው እንዲደራደር መፍቀድ አገርን የፖለቲከኞች የግል ንብረት እንድትሆን መፍቀድ ነው። ለመንግስታዊ ስነስርዓቱ እንኳን ቢያንስ ጉዳዩ ወደ ፓርላማ ቀርቦ በምክርቤቱ በኩል ማለቅ የሚኖርባቸው ጉዳዮች መከናወን ነበረባቸው። ፓርላማው አሸባሪ ብሎ ከፈረጀው ማናቸውም ቡድን ጋር መገናኘት ወንጀልና በሕግ የሚያስጠይቅ ነው። መሰል ነገሮች ካሉ የፍትሕ ሚኒስቴር ክስ የመመስረት ሥልጣን ተሰጥቶታል። የፀጥታ ተቋማትም የፀረ ሽብር አዋጁ እንዲከበር በሕግ የተጣለባቸው ግዴታዎች አሉ።

ይሁንና የብልጽግና ፓርቲ በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው ከአሸባሪው ትሕነግ ጋር የሚደራደር ቡድን መሰየሙን ሁላችንም በዜና መልክ ነው የሰማነው። ይህ ውሳኔ የፀረ ሽብር አዋጁን የጣሰ ነው። ሲቀጥልም መሰል ውሳኔዎች በመንግስት አካላት እንጂ በፓርቲ የሚወሰኑ ጉዳዮች አይደሉም። ብልጽግና ፓርቲ የሰራውን ነውር አብን ወይ ኢዜማ ቢፈጽመው ኖሮ ምን የሚከሰት ይመስላችኋል? መገመት አይከብድም። ፓርቲዎቹ በሕግ እንዲፈርሱ የመደረግ እድላቸው ይሰፋል፤ የፓርቲ አመራሮቹም በሽብር ወንጀል ተከሰው ዘብጥያ ይወርዳሉ። መሰል የሕግ ማስከበር ስራዎችም በፍትሕ ሚኒስቴርና በፀጥታ አካላት ትብብር ይፈፀማሉ። የብልጽግና ወንጀልስ? «ውኃ ቢያንቅ በምን ይውጡት፤ ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡት» ነው ነገሩ። የፍትሕ ሚኒስትሩና የመረጃና ደሕንነት ዳይሬክተሩ አዋጁ እንዲከበር የተጣለባቸውን የሕዝብ አደራ ወደ ጎን ትተው አዋጁን ሽረው በሽብር ከተፈረጀ አካል ጋር ለመደራደር በተሰየመ ቡድን ውስጥ በአባልነት ታቅፈዋል። ከዚህ የበለጠ ኢመንግስታዊነትና ኢመደበኝነትስ ይኖር ይሆን?

በኢትዮጵያ ጉዳይ የበለጠ የሚያገባው የለም፤ እኩል ያገባናል! ተናጠላዊና የሕግ ስነስርዓቶችን ያልተከተለ ድርድር የሕግ፣ የሞራልና ማሕበራዊ ቅቡልነቶች አይኖሩትም።
10.7K views03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 15:22:41 እስኪ እንጠያየቅ!
*
የፌዴሬሽኑ አባል የክልል መንግስታትና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የፌዴራሉ መንግስት ከትሕነግ ጋር የሚደረገውን ጦርነት ለአማራ (አልፎ አልፎ ለአፋር ጭምር) እንደሚደረግ ውለታ እንጂ የአገርን አንድነትና የሕዝብን ደኅንነት የመጠበቅ መንግስታዊ ግዴታ አድርገው በሙሉ ልባቸው ተቀብለውታል ለማለት እቸገራለሁ። ይህን አስተያየቴን የሚያጠናክሩ ሃሳቦች በትልልቅ መድረኮች ጭምር አመራሮች ማንፀባረቃቸው የአደባባይ እውነታ ነው።

በእርግጥም ለአገር አንድነትና ሕዝብ ደኅንነት በተደረገ ተጋድሎ የአማራና የአፋር ክልሎች የካፒታል በጀታቸውን አዙረው ጥቅም ላይ ሲያውሉ፤ በጦርነቱ ምክንያት በሁለቱ ክልሎች እስከ ግማሽ ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ ሀብትና ንብረት ሲወድም እንዲሁም የሁለቱ ክልሎች የማኅበራዊ አገልግሎትና የጤና ተቋማት መደበኛ ሥራቸውን አቋርጠው በጦርነቱ የቆሰሉትን ለማከሚያና ለማገገሚያ ማዕከልነት ሲውሉ በፌዴራሉም ሆነ በፌዴሬሽኑ አባል የክልልና የከተማ መንግስታት በእኩል ኃላፊነት እና በእኩል ግዴታ የየድርሻቸውን ማካካሻ ማድረግ ለምን አቃታቸው?
7.3K views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 21:11:09 በፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አስወስኖ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ተደራዳሪ ቡድን በማቋቋም፥ በአገሪቱ ፓርላማ በአሸባሪነት ከተፈረጀ አካል ጋር፥ ለመወያየት ውሳኔ ያሳረፈ፤ ብሎም በተግባር በድርድር ሂዲት ውስጥ እያለፈ ያለ አካል፤ ከእርሱ ሀሳብ ጋር የማይጣጣም እና/ወይም የሚቃረን አስተያየት የሚሰጡ ግለሰቦችን «ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተገናኝታችኋል» በሚል መወንጀሉ በእጅጉ አስገራሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

በሽብር ቡድኖች በኩል የሚሰነዘሩ የዜጎችን ደኅንነት አደጋ ላይ የጣሉ እርምጃዎችን በተገቢው ሁኔታ መመከትና ማስቀረት ያልቻሉ አመራሮች ቢያንስ ከሽብር ቡድኑ ርቀው ባሉ ንፁኃን ዜጎች ላይ ራሳቸው የደኅንነት ስጋት ከመሆን ቢቆጠቡ መልካም ነበር።

(በተቃዋሚ ማልያ የምትጫዎቱ ከቅርብም ከሩቅም ያላችሁ ግለሰቦች ትናንት በእናንተ አይዞህ ባይነትና ገፋፊነት ጭምር በላሊበላ፣ በሞጣ፣ በአማኑኤል እና በቢቡኝ ያስገደላችኋቸው ንፁኃን ደም አንሷችሁ፥ ዛሬም ድረስ ንፁኃን በግፍ እንዲታሰሩ ከምታደርጉት ውትወታ ብትወጡ መልካም ነው። በዚህ ድርጊታችሁ ነገ ታፍሩበታላችሁ። ንፁኃን በኢመደበኛነት ተፈርጀው እንዲሳደዱና እንዲገደሉ የነበራችሁን ሚና ሕዝብ እንዲያውቀው የምናደርግ መሆኑንም ማስታወስ እንፈልጋለን።)
7.7K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 05:41:53 እንቁጣጣሽ ኢትዮጵያ፥ እንቁጣጣሽ ወገን!
*
በአገር ውስጥና በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2015 ዓ/ም የዘመን መለወጫ በዓል አደረሰን፤ አደረሳችሁ!

አዲሱ ዓመት፦
★በኢትዮጵያ ሰላም ሰፍኖ በሐሳብ ልዩነት ምክንያት የጥይት ድምጽ የማይሰማበት፤ ኢትዮጵያውያንም በየትኛውም ልዩነቶቻቸው/ብዝኃነታቸው ምክንያት በጠላትነት የማይተያዩበት፣
★ሁሉም ፖለቲከኞች ከየራሳቸው ግለሰባዊና ቡድናዊ ፍላጎቶች በላይ ለአገር አንድነትና የሕዝብም ደኅንነት ቅድሚያ የሚሰጡበት፤ በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይም አንድ ልብ መካሪ፥ አንድ ቃል ነጋሪ ሆነው የሚቆሙበት፣
★ኢትዮጵያውያን በሙሉ በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባትን የምንፈጥርበት፤ ለኢትዮጵያዊነታችንም የበለጠ ድምቀትን የምንሰጥበት፣
★ፈጣሪን ለማመስገን ካልሆነ በስተቀር ለምሬትና ለልመና አንድም ኢትዮጵያዊ እጆቹን የማይዘረጋበት፣
★ነጋዴው ነግዶ የሚያተርፍበት፤ ተማሪው ያሰበው የሚሳካበት፤ ምሁሩ ለአዳዲስ ፈጠራዎች የሚተጋበት፣
★አርሶና አርብቶ አደሩ የሰብሉን እሸት፥ የከብቱን ወተት የሚያጣጥምበት፣
★ኑሮ የሚረክስበት፤ ሰው የሚወደድበት፣
★ያላገቡ አግብተው ወግ ማእረግ የሚያዩበት፥ የተጋቡትም ልጅ ወልደው የሚስሙበት፣
★የታመመው ተፈውሶ፤ የተሰደደው ወደ እናት አገሩ ተመልሶ፤ ያዘነም እንባው ታብሶ የሚደሰቱበት፣
★እስረኞች የሚፈቱበት፤ እረኞች የሚቦርቁበት፣
★በየደረጃው ያሉ የሕዝብ አስተዳዳሪዎችና መሪዎች ለአገራቸውና ለሕዝባቸው በቀናነት የሚተጉበት፣
★በተለይም የአማራ፣ አፋርና ትግራይ ወገኖች ከጦርነት ቀጠና ወጥተው እፎይ የሚሉበት፣
★የእምነት ተቋማት ከጉንጭ አልፋ ክርክር፣ ጥልና መለያየት ስብከት ወደ መልካም ትብብር፣ አብሮነትና የጽድቅ ማማ የሚቀየሩበት፣
★አእዋፍት የሚዘምሩበት፤ ምንጮች የማይደርቁበት፤ ዛፎች የሚለመልሙበት፣
★ድርቅና ቸነፈር የማይኖርበት፤ ደዌ የተወገደበት፣
★እንደግለሰብም ሆነ እንደአገር የተለምናቸው በጎ ውጥኖች ሁሉ የሚሳኩበት፣
★ሰውንም ሆነ እግዚአብሔርን የምናስደስትበት፤ ለወገን ጠቅመን እኛም የምንጠቀምበት፣
★እንደአገርና ሕዝብ የዓለሙ መሳቂያ እና መሳለቂያ ከመሆን ወጥተን ዳግም ላንወድቅ በክብር ተነስተን በአንድነት የምንቆምበት፣

እኒህንና እኒህን መሰል በጎ ነገሮች ሁሉ ይዞልን እንዲመጣ፤ ለዚህም የየድርሻችንን በጎ ነገር ሁሉ ያለገደብ የምናበረክትበት ይሆን ዘንድ እመኛለሁ። በድጋሜ መልካም አዲስ ዓመት!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ልጆቿን አብዝቶ ይባርክ!
8.2K viewsedited  02:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 19:13:45
መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን!
ክርስቲያን ታደለ
7.0K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 21:54:48
እንግጫ ነቀላ #ወምበርማ፣ ጎጃም፥ አማራ!
8.0K views18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 17:01:12 ይድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤
ይድረስ ለአብን መዋቅሮች፣ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፤
*
አብን እሁድ ነሐሴ 29/2014 ዓ/ም የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ምልዓተ ጉባዔው ባለመሟላቱ ስብሰባው ሳይካሄድ ቀርቷል። እውነታው ይኼ ሆኖ እያለ ባልተካሄደ ስብሰባ፣ ውይይት ባልተደረገበት አጀንዳና ተገቢ ፖለቲካዊ ምክክር ተደርጎ ባልተላለፈ ውሳኔ፤ ስብሰባ እንደተጠራ፣ አጀንዳ ተዘርግቶ ውይይት እንደተካሄደና ውሳኔዎች እንደተላለፉ ተደርጎ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ የስነስርዓት ጥያቄዎች የሚቀርቡበበት፣ ድርጅታዊ አሰራርንና መርኅን የጣሰ እንዲሁም ከዴሞክራሲ ልምምድ ያፈነገጠ የነውር ሥራ ነው። የስንስርዓታዊ ጉዳዮች መሟላት ስብሰባው ከመካሄዱና በስብሰባው ከሚወሰነው ውሳኔ እኩል ወይንም የበለጠ አስፈላጊ በመሆኑ ባልተሟላ ምልዓተ ጉባዔ ስብሰባዎች አይካሄዱም።

ለውጥ ፈር በሆኑ ጥቂት የአብን ከፍተኛ አመራሮች እየተደረገ ያለው ሁኔታ ግን ለንቅናቄው አባላትና አመራሮች ብቻ ሳይሆንም ለስርዓት ግንባታም ደንታ የሌላቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው። ሰኞ ነሐሴ 30/2014 የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አድርገን ውሳኔዎችን አሳልፈናል ይበሉ እንጂ የሰኞ ስብሰባ ስለመኖሩ የትኛው የድርጅቱ አካል፣ መቼና በምን መንገድ ጥሪ አስተላለፈ? ጥሪውስ ለሁሉም የማዕከላዊ አባላት እኩል ተላልፎላቸው ነበር ወይ? የድጋሚ ስብሰባ ቀኑ ሲወሰን ከስብሰባ ቦታው ርቀው የሚገኙ አባላትን የመጓጓዣ ቀናት ታሳቢ ያደረገ ነበረ ወይ? ወዘተረፈ ቀላል ግን መሰረታዊ ጥያቄዎችን መመለስ የሚያስችል ተጨባጭ ነገር ማቅረብ አይቻላቸውም።

ባለፈው እነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ማኅተም ስለያዙ ብቻ የንቅናቄው የሥራ አስፈፃሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ ያልመከረባቸውንና ያላፀደቃቸውን የኦዲት ሪፖርት እና የሪፎርም ጉባዔ (የደንብ ማሻሻያና የአመራር አመላለመል እንዲሁም አወቃቀርን ጨምሮ) ውይይት ተካሂዶባቸው የጸደቁ በማስመሰል ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር የደብዳቤ ልውውጦች ማድረጋቸውን ስለታዘብን፤ጉዳዩ የወንጀል ተጠያቂነትን ጭምር የሚያስከትል ጉዳይ ያለው ስለሆነ ይህንንም የሚመለከታቸው ተቋማት በተለይም የንቅናቄው በየደረጃው ያሉ መዋቅሮች፣ አመራሮችና አባላት በልዩ ልዩ አማራጮች አሳውቀናል። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔው የተወሰነበት ቃለጉባዔ ይምጣልኝ የሚል ደብዳቤ ስለፃፈ፤ የቦርዱን ጥያቄ አሰነባብቶና ቀባብቶ ምላሽ ለመስጠት በሚል ከስነስርዓት ውጭ ስብሰባ ተደርጎ፥ ውሳኔ እንደተላለፈ መግለጫ ማውጣት፤ በተደጋጋሚ ጊዜ የተፈፀመ ነውር እና የምርጫ ቦርድን በተሳሳተ ደብዳቤ የተሳሳተ ውሳኔና ግንዛቤ ላይ እንዲደርስ የሚደረግ የወንጀል ተግባር ተደርጎ የሚቆጠር ነው። መሰል ስህተቶችን ነቅሰን ጉዳዩ ለሚመለከተው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ደብዳቤ አስገብተናል። ቦርዱ ተገቢውን ማጣራትና ምርመራ አድርጎ ተገቢ ውሳኔ ላይ እንደሚደርስም እምነት አለን። በተለይ ከኦዲት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ከንቅናቄው አመራሮች ጭምር ይመርመርልን ጥያቄ የቀረበበት በመሆኑ እና የምርጫ ቦርድም መሰል ጥርጣሬዎችና ጥያቄዎች ሲቀርቡለት የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትን ልዩ ኦዲት እንዲሰራለት የመጠየቅ መብት ስላለው፤ ይኽንኑ እንዲያደርግ ደግመን ማስታወስ እንፈልጋለን።

መላው የአብን መዋቅሮች፣ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ንቅናቄያችን የሚያደርገው የለውጥ እንቅስቃሴ ለግላዊ ጥቅማቸው ሲሉ ከገዥው ፓርቲ ጋር በተጣበቁ ጥቂት ግለሰቦች መታገቱን በውል በመረዳት፤ ፓርቲው የተሟላ ሪፎርም አድርጎ መላው ሕዝባችን የሰጠውን አደራ እንዲወጣ በተገቢው ሁኔታ ብርቱ ትግል ታደርጉ ዘንድ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።
3.9K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ