Get Mystery Box with random crypto!

እስኪ እንጠያየቅ! * የፌዴሬሽኑ አባል የክልል መንግስታትና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የፌዴራሉ | Christian Tadele Tsegaye

እስኪ እንጠያየቅ!
*
የፌዴሬሽኑ አባል የክልል መንግስታትና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የፌዴራሉ መንግስት ከትሕነግ ጋር የሚደረገውን ጦርነት ለአማራ (አልፎ አልፎ ለአፋር ጭምር) እንደሚደረግ ውለታ እንጂ የአገርን አንድነትና የሕዝብን ደኅንነት የመጠበቅ መንግስታዊ ግዴታ አድርገው በሙሉ ልባቸው ተቀብለውታል ለማለት እቸገራለሁ። ይህን አስተያየቴን የሚያጠናክሩ ሃሳቦች በትልልቅ መድረኮች ጭምር አመራሮች ማንፀባረቃቸው የአደባባይ እውነታ ነው።

በእርግጥም ለአገር አንድነትና ሕዝብ ደኅንነት በተደረገ ተጋድሎ የአማራና የአፋር ክልሎች የካፒታል በጀታቸውን አዙረው ጥቅም ላይ ሲያውሉ፤ በጦርነቱ ምክንያት በሁለቱ ክልሎች እስከ ግማሽ ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ ሀብትና ንብረት ሲወድም እንዲሁም የሁለቱ ክልሎች የማኅበራዊ አገልግሎትና የጤና ተቋማት መደበኛ ሥራቸውን አቋርጠው በጦርነቱ የቆሰሉትን ለማከሚያና ለማገገሚያ ማዕከልነት ሲውሉ በፌዴራሉም ሆነ በፌዴሬሽኑ አባል የክልልና የከተማ መንግስታት በእኩል ኃላፊነት እና በእኩል ግዴታ የየድርሻቸውን ማካካሻ ማድረግ ለምን አቃታቸው?