Get Mystery Box with random crypto!

በፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አስወስኖ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ተደራዳሪ ቡድን በማቋቋም፥ በ | Christian Tadele Tsegaye

በፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አስወስኖ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ተደራዳሪ ቡድን በማቋቋም፥ በአገሪቱ ፓርላማ በአሸባሪነት ከተፈረጀ አካል ጋር፥ ለመወያየት ውሳኔ ያሳረፈ፤ ብሎም በተግባር በድርድር ሂዲት ውስጥ እያለፈ ያለ አካል፤ ከእርሱ ሀሳብ ጋር የማይጣጣም እና/ወይም የሚቃረን አስተያየት የሚሰጡ ግለሰቦችን «ከአሸባሪው ቡድን ጋር ተገናኝታችኋል» በሚል መወንጀሉ በእጅጉ አስገራሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

በሽብር ቡድኖች በኩል የሚሰነዘሩ የዜጎችን ደኅንነት አደጋ ላይ የጣሉ እርምጃዎችን በተገቢው ሁኔታ መመከትና ማስቀረት ያልቻሉ አመራሮች ቢያንስ ከሽብር ቡድኑ ርቀው ባሉ ንፁኃን ዜጎች ላይ ራሳቸው የደኅንነት ስጋት ከመሆን ቢቆጠቡ መልካም ነበር።

(በተቃዋሚ ማልያ የምትጫዎቱ ከቅርብም ከሩቅም ያላችሁ ግለሰቦች ትናንት በእናንተ አይዞህ ባይነትና ገፋፊነት ጭምር በላሊበላ፣ በሞጣ፣ በአማኑኤል እና በቢቡኝ ያስገደላችኋቸው ንፁኃን ደም አንሷችሁ፥ ዛሬም ድረስ ንፁኃን በግፍ እንዲታሰሩ ከምታደርጉት ውትወታ ብትወጡ መልካም ነው። በዚህ ድርጊታችሁ ነገ ታፍሩበታላችሁ። ንፁኃን በኢመደበኛነት ተፈርጀው እንዲሳደዱና እንዲገደሉ የነበራችሁን ሚና ሕዝብ እንዲያውቀው የምናደርግ መሆኑንም ማስታወስ እንፈልጋለን።)