Get Mystery Box with random crypto!

Christian Tadele Tsegaye

የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye C
የቴሌግራም ቻናል አርማ marheirgebrye — Christian Tadele Tsegaye
የሰርጥ አድራሻ: @marheirgebrye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.97K
የሰርጥ መግለጫ

This channel serves as a platform to reflect political and socio-economic views of Christian Tadele Tsegaye.

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-08-18 06:56:02 https://vm.tiktok.com/ZMNt7b28M/
6.4K views03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 06:46:29
የቤተሰብ ስምምነትን የሕዝብ ፍላጎት አድርጎ ሕግና መዋቅር ለበስ አድርጎ ማቅረብና ያለሕዝብ ይሁንታ የአዲስ አበባንና ኦሮሚያን ወሰን ማካለል ነውርም ወንጀልም ነው!
6.2K views03:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 15:36:02 ጀልባዎቻችን እናቃጥል!
****
«ሂድና ጀልባችንን አቃጥለው!»

ይኼ ለሚወዳት አገሩ ስፔን አዲስ ግዛት ለማስገኘት እ.ኤ.አ በ1519 በአገረ ሜክሲኮ ቬራክሩዝ (Veracruez) ባሕር ወሽመጥ ከጦር ጓዶቹ ጋር የነበረ ኼርናንዶ ኮርቴስ ከሥሩ ለነበረው ኮሎኔል ያስተላለፈው አስገራሚ ትዕዛዝ ነው።

የጦር ጀነራሉ ኮርቴስ ከፊት ለፊታቸው እስከ አፍንጫቸው የታጠቀ ጠላት፣ የስንቅ መመናመን እንዲሁም ከዚያ በፊት የማያውቋቸው በሽታዎች ሰራዊቱን እየፈተነው መሆኑን ቢያውቅም ወደ ባሕር ወሽመጡ ያመጧቸውን ጀልባዎች ለማምለጫነት ከመጠቀም ይልቅ ወታደሮቹን ለዓላማቸው እስከመጨረሻው እንዲፋለሙና ኅልውናቸውን በማሸነፍ ላይ ብቻ የተመረኮዘ እንደሆነ የሚያስረግጠውን ቀጭን ውሳኔ አሳለፈ፤ ጀልባዎቹ እንዲቃጠሉ! በኮርቴስ ትእዛዝ መሰረትም ጀልባዎቹ በእሳት ተንቀለቀሉ። የቃጠሎው እሳት በወታደሮቹ ልብና መንፈስ ላይ የቆራጥነት ፍሙን ጣለ። ነበልባሉም ወደ ድል መንገድ የሚመራ ችቦ ተደርጎ ተቆጠረ። በሕይወት ለመቀጠል ያላቸው ብቸኛ ምርጫ ማሸነፍ መሆኑን የተረዱት ወታደሮቹ በጀግንነት ተዋጉ። ኅልውናቸውንም በድላቸው አፀኑ።

አማራ እንደሕዝብ ያጋጠመውን ፈተና ተሻግሮ ኅልውናው የሚቀጥለው ሲያሸንፍ የመሆኑን መሪር ኃቅ ደጋግመን ማሳሰባችን አሁናዊ ትውስታ ነው። እውነታው ይህ ከሆነ ታዲያ ለምን አሁን ላለንበት ታሪካዊ ውርደት ተዳረግን? መልሱ ግልፅ ነው፤ ጀልባዎቻችንን ስላላቃጠልን ነው።

«አማራና አማራነት እየተጎዳ፤ ኅልውናውም አደጋ ላይ ነው» እያልን ... ዞር ብለን በአውራጃዊነት ጀልባችን ተሳፍረን እንገኛለን። አማራነትን ከተወለድንበት መንደር ከተቀበረ እትብታችን አንፃር እየለካን የሩቅና የቅርብ አማራ በሚል ወንዜ ጀልባችን ላይ መፈናጠጥ ያምረናል።

የተሰባሰብነውና የተደራጀነው መሰባሰባችን የኅልውናችን እርሾ የሚጣልበት በመሆኑ ነው። የምንሰባሰበውና የምንደራጀው የተጋረጠብንን የኅልውና አደጋ በብቃት እንዳንመክት ትግላችንን እንደጭቃ ግድብ ውሽልሽል ያደረጉብንን ጎታች «ጀልባዎቻችንን» በማቃጥል አማራ በሚለው ኃላችን በክብር ለመገለጥ ነው። የተሰባሰብነው ከሕይወት እጅግ የሚልቅ ዋጋ ያለውን ነፃነት ለሕዝባችን ለማቀዳጀት ነው። የምንሰባሰበው በእኩልነት መሶብ ለሁሉም የሚበቃ የፍትሕ እንጀራን ለማቅረብ ነው። ከጅሩ እስከ ባሕር ዳር፤ ከወልድያ እስከ ጎንደር በአደባባይ ደማቸው የፈሰሰ ወገኖቻችን ሰማእትነትን የተቀበሉት ፍትሕ ለተጠማ ሕዝባችን ሲሉ ነው።

«ታላቁ አማራ ተዋርዷል፤ እንዲህ ተዋርዶ ከምናይ ሞት በስንት ጠዓሙ» ብለን ምለን ተገዝተን ለሕዝባችን ነፃነት ሁለመናችንን አሳልፍን ልንሰጥ ወደ ትግል ሜዳው ከገባን በኋላ... «ታሰርን፤ ተገፋን፤ ስማችን ጠፋ፤ ምቾታችን ተጓደለ፤ ወዘተርፈ» በሚል ወልካፋ የሙሾ ጀልባችን መሳፈር ይዳዳናል። በዚህ ሁሉ መሐል ደግሞ እራሳችንን የአማራነት መስፈሪያ ቁና አድርገን ነቃፊ አደናቃፊ በመሆን በራስ አምልኮ የመታበይ ጀልባችን ላይ ለመምነሽነሽ ልባችን ይቋምጣል። ይህን ሁሉ ሆነን ድል እንናፍቃለን። ድል በትግል እንጂ በምኞት የምንቋደሰው መጎምዠት አይደለምና እነሆ የሆንነውን ሁሉ ለመሆን ተገደናል። ጀልባችንን እናቃጥል!
11.0K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 16:19:17
8.4K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 16:19:05 በቋሪት ምርጫ ክልል በጎንጂ ቆለላ ወረዳ እንዘግድም ቀጠና ከሚገኘው መራጭ ሕዝባችን ጋር በዋሸራ ትርጉም ያለው የሕዝብ ውይይት አድርገናል። ሕዝባችን በፍትኃዊ የመሰረተ ልማት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት፣ በመልካም አስተዳደርና ሰላም እንዲሁም በሌሎች የማኅበራዊ ልማት፣ የኢኮኖሚ መሻሻል እንዲሁም የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በርካታ ጥያቄዎችን አቅርቧል። መጠየቅ ብቻ ሳይሆን እንዴት መፈታት እንደሚችሉም የመፍትሔ ኤቅጣጫዎችን አመላክቷል።

የምርጫ ክልሉ ተመራጮችና የጎንጂ ቆለላ ወረዳ አመራሮችም የሕዝባችን ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ አደራ ተቀብለናል። ዝርዝር ውይይቶችንና የተቀመጡ አቅጣጨዎችን በምስል በቅርብ በዚሁ ገጽ እናደርሳችኋለን።

ለእንዘግድም ቀጠና ወገናችን በተለይም ለዋሸራ ከተማ ነዋሪዎችና ለጎንጂ ቆለላ ወረዳ አመራሮች ለተደረገልን አቀባበልና ለሰጣችሁን ልዩ ፍቅር እጅ እንነሳለን።



8.3K viewsedited  13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 08:57:23 በአማራ ላይ የተፈፀመውን የማያባራ የግፍ ጭፍጨፋ ለዓለምአቀፍ ማኅበረሰቡ በውል ለማስገንዘብ በለንደን የአደባባይ የርኃብ አድማ እያደረጋችሁ ለምትገኙ ወገኖቼ ያለኝን ክብር መግለጽ እወዳለሁ። እያደረጋችሁት ስላለው ተጋድሎም በአማራ ሕዝብ ስም ምስጋናዬ ይድረሳችሁ!
10.5K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 11:36:27 የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራብ በማድረግ በየጊዜው የምናደርጋቸውን የፖለቲካና ሌሎች ጉዳዮች ይከታተሉ።
10.1K views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 11:36:27 https://youtube.com/user/ChristianTadeleTsega
9.9K views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ