Get Mystery Box with random crypto!

በቋሪት ምርጫ ክልል በጎንጂ ቆለላ ወረዳ እንዘግድም ቀጠና ከሚገኘው መራጭ ሕዝባችን ጋር በዋሸራ | Christian Tadele Tsegaye

በቋሪት ምርጫ ክልል በጎንጂ ቆለላ ወረዳ እንዘግድም ቀጠና ከሚገኘው መራጭ ሕዝባችን ጋር በዋሸራ ትርጉም ያለው የሕዝብ ውይይት አድርገናል። ሕዝባችን በፍትኃዊ የመሰረተ ልማት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት፣ በመልካም አስተዳደርና ሰላም እንዲሁም በሌሎች የማኅበራዊ ልማት፣ የኢኮኖሚ መሻሻል እንዲሁም የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በርካታ ጥያቄዎችን አቅርቧል። መጠየቅ ብቻ ሳይሆን እንዴት መፈታት እንደሚችሉም የመፍትሔ ኤቅጣጫዎችን አመላክቷል።

የምርጫ ክልሉ ተመራጮችና የጎንጂ ቆለላ ወረዳ አመራሮችም የሕዝባችን ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ አደራ ተቀብለናል። ዝርዝር ውይይቶችንና የተቀመጡ አቅጣጨዎችን በምስል በቅርብ በዚሁ ገጽ እናደርሳችኋለን።

ለእንዘግድም ቀጠና ወገናችን በተለይም ለዋሸራ ከተማ ነዋሪዎችና ለጎንጂ ቆለላ ወረዳ አመራሮች ለተደረገልን አቀባበልና ለሰጣችሁን ልዩ ፍቅር እጅ እንነሳለን።