Get Mystery Box with random crypto!

የራሔልን እንባ የተመለከትህ አምላክ ሆይ፤ የነሉባባና ተስፋነሽንም እንባ ተመልከት! **** ደቡብ | Christian Tadele Tsegaye

የራሔልን እንባ የተመለከትህ አምላክ ሆይ፤ የነሉባባና ተስፋነሽንም እንባ ተመልከት!
****
ደቡብ ኦሞን ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ በሥራ አጋጣሚ አውቀዋለሁ። ሕዝቡ እንግዳ ተቀባይና ብዝኃነትን የኩራቱ ምንጭ አድርጎ የሚኖር እንደነበር በተደጋጋሚ ጊዜ በነበረኝ የመስክ ጉዞዎች ያረጋገጥሁት እውነታ ነው። ይሁንና በፊደላውያን ምክንያት ያ ቱባ ገራገርነት…ያ ኅብራዊነት ውበቱ የነበረ ደግ ሕዝብ…በአፍለኞች ክፉኛ ተፈተነ። አፍለኞች የለኮሱት እሳት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችም የሚተርፉ ወገኖች ነጥፎ የማያውቀውን ማጀታቸውን ወደ ፍርስራሽነት ቀየረው። አፈር ስሆን…ብሉልኝ…ጠጡልኝ…ሲሉ የነበሩ እርብትብት አንደበቶች ስንቱን ፈትፍተው ያጎረሶች መዳፎችን ተመርኩዘው ፈጣሪን ና ውረድ ይላሉ። …።

ግን ለምን? መቼስ ነው የግፍ ጽዋው የሚሞላው? ሁላችንም ለየራሳችን ጠይቀን ለአገርና ለሕዝብ ስንል የግድ በጋራ ልንመልሰው የሚገባን ጥያቄ ነው።

የራሔልን እንባ የተመለከትህ አምላክ ሆይ፥ የእነሉባባና ተስፋነሽንም እንባ ተመልከት!

(ሉባባና ተስፋነሽ ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው የተቀየረ ናቸው።)