Get Mystery Box with random crypto!

ወባን በፓራስታሞል ማከም ከፍተኛ የሆነውን ሙቀት እንዲቀንስ ያግዛል። ሕመሙንም ያስታግሰዋል። ይሁን | Christian Tadele Tsegaye

ወባን በፓራስታሞል ማከም ከፍተኛ የሆነውን ሙቀት እንዲቀንስ ያግዛል። ሕመሙንም ያስታግሰዋል። ይሁንና ፓራስታሞሉ የወባ ጥገኛ ተዋሕሱን በመደበቅ ለማስወገድ የሚደረገውን የሕክምና ጊዜ ያራዝማል። ተዋሕሱን ለማስወገድ የሚወስደው የተራዘመ ጊዜም ሕመምና ሞትን ያስከትላል።

ከሰሜኑ ጦርነት አኳያ በመፍትሔነት የተወጡኑና እየተደረጉ ያሉ ነገሮች ሁሉ ወባን በፓራስታሞል እንደማከም እንዳይሆኑ ስጋት አለኝ።

የግርጌ ማስታዎሻ፦
1) ፓራስታሞል በተለይ በወባ የታመሙ ሕፃናትን ከፍተኛ ሙቀት ለመቀነስ ጥቅም ላይ ይውላል። ከላይ የቀረበው አብነት የፓራስታሞል ሕክምናውን ጨርሶ ለማጣጣል አይደለም።
2) ወባ እና የወባ በሽታ ተምሳሌትነታቸው ለፖለቲካ ቀውሱ እንጂ የትኛውንም አካል በጋራም ይሁን በተናጠል በተለዋጭ ዘይቤ የሚወክሉ አይደሉም።

ሰላም ለኢትዮጵያና ልጆቿ፥ ሰላም ለሰው ልጆች ሁሉ!