Get Mystery Box with random crypto!

የክልል መንግስት አመራሮች በምን አገባብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆኑ? * አሁን በሥራ ላይ ባለው ሕ | Christian Tadele Tsegaye

የክልል መንግስት አመራሮች በምን አገባብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆኑ?
*
አሁን በሥራ ላይ ባለው ሕገመንግስት የውጭ ጉዳይ ሥራ የፌዴራሉ መንግስት በብቸኝነት (ከክልሎች የማይጋራው) የሚይዘው ሥልጣንና ኃላፊነት ነው። ይሁንና የአንዳንድ ክልሎች አመራሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፌዴራል የሥልጣን እርከን ሥር የሚወድቀውን የውጭ ግንኙነት ሥራ ሲያከናውኑ በዜናዎች መስማት ብርቅ አይደለም። (ምናልባት እንድለማመደው የተፈለገ ጉዳይ ይኖር ይሆን? )

መሰል ግራጫ ሁኔታዎች እስኪፈጠሩ ድረስ የውጭ ጉዳይ ተልእኮ ለክልሎች በውክልና የሚሰጥ አልነበረም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚመራው ስምሪት በሆነ አጋጣሚ የክልል አመራሮች የጉዞው/ተልእኮው አካል ቢሆኑ እንኳን ከታች ፋና ብሮድካስቲንግ በዘገበው መልኩ የውጭ ጉዳይ ሥራን የክልል አመራሮች መሪ ተዋናይ በሚሆኑበት መንገድ ሊከወን አይችልም። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት የመስሪያ ቤታቸውን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት መሰል ያልተገቡ ጉዳዮችን በተመለከተ ከምክርቤት አባላት ማብራሪያ እንዲሰጡ ሲጠየቁ «ከአሁን በኋላ ክልሎች ቀጥታ የውጭ ግንኙነት እንዳያደርጉ መመሪያ ሰጥተናል» የሚል ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

በአንድ አገር ሁለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይኖርምና፥ መሰል አገር አከል የክልል መንግስታት እና አመራሮቻቸው ተሳትፎ በእንቁላል ዘመናቸው ሊቆረቆቡ ይገባል።