Get Mystery Box with random crypto!

ወንድማችን አርበኛ ዘመነ ካሴን በጠዋት ሰባታሚት ተገኝተን ጎበኘነው። ከሁሉም አካባቢዎች የተሰባሰቡ | Christian Tadele Tsegaye

ወንድማችን አርበኛ ዘመነ ካሴን በጠዋት ሰባታሚት ተገኝተን ጎበኘነው። ከሁሉም አካባቢዎች የተሰባሰቡ ወጣቶች አርበኛውን ለመጠየቅ ወረፋ ተሰድረዋል። ፍተሻውን አልፈን ወደ ውስጥ ስንገባ አርበኛው ልክ እንደባለቅኔ ቀደምቶቹ ወንበር ዘርግቶ ጠያቂዎቹን ፈገግታ እየመገበ ወኔ ያስዘርፋል።

የአርበኝነት መዓዛውን ታጥነው የሚወጡ ውርዝው ሁሉ ፊታቸው ወዝቶ ሲወጡ ተመልክተናል። ስንገባ እንደሁልጊዜው በፈገግታ ተቀበለን። በርቱ ብሎን በርትተን ተመለስን። ከወጣን በኋላ አንድ ወቅት ለእንዲህ ዓይነት «ደግ ቀን» የከተብናትን አስታውሰን ፈገግ አልን። አብረን ፈገግ እንበል

የሚስቅ ሰው…
ብፁዕ ነው፣
እግዜር የቀደሰው፣
ጥርሱ ያከበረው፡፡
በድቅድቅ ጨለማ…
ሳቁን እየሞቀ፣
ብሶቱን ያመቀ፡፡
በመከራ መሀል…
በፈገግታ ምሽግ፣
ሀዘኑን ‘ሚሸሽግ፡፡
በፈተና ጊዜ…
በጥርሱ ብልጭታ፣
ክፉን ድል ሚመታ፡፡
የሚስቅ ሰው…
ፃድቅ ነው!

መልካም ቅዳሜ!