Get Mystery Box with random crypto!

ድሩፃ! ደመራው ሲቃጠል፤ ጠላትን እንደጠል፤ ከፊታችን ያርግፍ፣ ደሞ እንደደቦቱ፤ ተቃጥሎ በእሳቱ | Christian Tadele Tsegaye

ድሩፃ!

ደመራው ሲቃጠል፤
ጠላትን እንደጠል፤
ከፊታችን ያርግፍ፣
ደሞ እንደደቦቱ፤
ተቃጥሎ በእሳቱ፤
መከራችን ይለፍ።

እንጎሮጎባሽ ትግራይ!
እንጎሮጎባሽ አማራ!
ድሩፃ ድሩፃ ኢትዮጵያ!

የመስቀሉ ጌታ፤
አንድም ሳይቀንሰን፣
በፍቅር በጤና፤
ዓመቱን ያድርሰን!