Get Mystery Box with random crypto!

ውሎ አድሮም ቢሆን በአማራ ብሔርተኝነት ትግል ሰልፍ ውስጥ ባሉ ተዋናዮች ዘንድ ያለው ልዩነት የመስ | Christian Tadele Tsegaye

ውሎ አድሮም ቢሆን በአማራ ብሔርተኝነት ትግል ሰልፍ ውስጥ ባሉ ተዋናዮች ዘንድ ያለው ልዩነት የመስመር ልዩነት ሆኖ እንዲህ ፍጥጥ ብሎ መውጣቱን ወድጄዋለሁ። ሰው በሚያምንበት መስመር መታገሉን ትግላችን የሚያከብረውና እውቅና የሚሰጠውም ስለሆነ ከዚህ አንፃር ያሉ የአሰላለፍ ግራጫዎች እየጠሩ መሄዳቸው ለሕዝባችንም ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል።

በትግል መስመራችን ውስጥ ወንድማማችነትን ለሕግ ትርጉም፣ ዳኝነትና ብይን የምናቀርበው አልነበረም፤ አይደለም፤ አይሆንምም። የወንድማማችነት መንፈስና እሴት ላይ ጥያቄ ያለው አካል በአንድ የፖለቲካ ትግል መስመር በተለይም ደግሞ በብሔርተኝነት የትግል መስመር ላይ ሊገኝ ግን አይችልም። በየሰልፋችን እንሁን። ይኸው ነው!