Get Mystery Box with random crypto!

የአድዋ ድል የዓለምን ታሪክ ስርነቀል በሆነ መንገድ የቀየረ አባቶቻችን ያስመዘገቡት ገድል ነው። ድ | Christian Tadele Tsegaye

የአድዋ ድል የዓለምን ታሪክ ስርነቀል በሆነ መንገድ የቀየረ አባቶቻችን ያስመዘገቡት ገድል ነው። ድሉ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የፀረ ቅኝ ግዛት ተጋድሎ ላደረጉ መላው የሰው ልጆች ሁሉ ነው። ድሉ የሰብአዊ እኩልነትን በደም ማኅተም ያረጋገጠ በዚህ መንፈስ ውስጥ ላሉ የዓለም ሰዎቸ ሁሉ ድላችን ብለው ክብርና ድምቀት የሚሰጡት ነው። በዚህም መላው ኢትዮጵያውያን ስለአድዋ ድል ቀደምቶቻችንን በትውልድ ሁሉ ልንዘክራቸውና ልናመሰግናቸው ይገባል።

በመሪዎቻችን ስብእና ዙሪያ ክርክር ሊኖረን ይችል ይሆናል። አድዋን አንስተን ግን ዳግማዊ አጤ ምኒሊክን አለማውሳት አይቻለንም። አጤውን መጥላት ይቻል ይሆናል፤ ያለ ምኒሊክ ግን አድዋ የሚባል ድል የለም። የንጉሰ ነገስቱን ምስል ከአድዋ ድል በዓል አከባበር ምስሎች ዝርዝር ፍቆ፤ በቦታው ያልነበሩ አሁን በሥልጣን ላይ ያሉ ግለሰቦችን ምስል መተካት፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው ራት በሰበሰባቸው ሐዋሪያት ምስል ውስጥ የራስን ምስል በጌታችን ኢየሱስ ቦታ በአርትዖት የመተካት ያህል ነውር ነው። ወይንም ትንሳኤን ለማክበር በተሰቀለው ኢየሱስ ምስል ፋንታ የየራሳችንን ፎቶ የመደረት ያህል ኑፋቄ ነው።

በዚህ ረገድ የማዝነውም የማፍረውም ይህን በሚያደርጉ ሰዎች አይደለም፤ ይልቁንም በአጤ ምኒሊክ ፋንታ ምስላቸው የአድዋን ድል እንዳስገኙ ተቆጥሮ ሲታተም በዝምታ የተባበሩትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ክፉኛ አዝኜባቸዋለሁ። እንዴት በሳቸው ደረጃ ያለ ሰው መሰለ ነውሮችነ በዝምታ ይተባበራል? ከበዓሉ አከባበር ጋር ተያይዞ በፀጥታ አካላት በኩል በዜጎች ላይ የሚፈፀመውን አፈና፣ ውርክቢያና እንግልትስ ለምን ማስቆም አቃተቸው? የአድዋን ድል በእስር፣ ድብድብና እንግልት ማክበርስ በዓሉን የማክበር ትሩፋቱን አያሳጣውም ወይ? በዚህ መልኩ የሚከበር የድል ቀንስ ከባርነት በምን ይለያል?

ልቦና ይስጠን፤ ልቡና ይስጣችሁ!