Get Mystery Box with random crypto!

የይልቃል ከፋለ መንግስት የአብን የምዕራብ ጎጃም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነውን አሸ | Christian Tadele Tsegaye

የይልቃል ከፋለ መንግስት የአብን የምዕራብ ጎጃም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነውን አሸናፊ አካሉ አስገድዶ ከሰወረው ከአስራ ምናምን ቀናት በኋላ ነገ በባሕር ዳር ከፍተኛ ፍርድቤት እንደሚያቀርበው ተሰምቷል። በዳኝነት ነፃነት ላይ ያለን የማይዛነፍ አክብሮት እንደተጠበቀ ሆኖ ችሎቱ በትግል ወንድማችን ላይ የተፈፀመበትን ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰትና የይልቃል ከፋለን መንግስት የፀጥታ መዋቅር የውንብድና ድርጊት አጽንዖት ሰጥቶ ተገቢው ማብራሪያ እንዲሰጥበት ማድረግ ይኖርበታል። የአብን አባላትና ደጋፊዎች ለትግል ወንድማችን ያላችሁን አጋርነት ታሳዩ ዘንድም ጥሪ እናቀርባለን።

(ለአባላቱና ደጋፊዎቹ ደኅንነት ግድ የሚለውን አብን በፍፁም መታደስ የሕዝብ፥ ለሕዝቡ፥ በሕዝቡ ሆኖ እንዲቀጥል በላቀ የኃላፊነት መንፈስ በአዲስ መነቃቃት እንድንቆምም ለንቅናቄው አባላትና ደጋፊዎች መልእክት እናስተላልፋለን።)

አብን፥ የአዲሱ ትውልድ የዴሞክራሲ አምበል!