Get Mystery Box with random crypto!

የአብን ዳግም ልደት! * የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጅግ ዘግይቶም ቢሆን የወሰነው ውሳኔ ንቅ | Christian Tadele Tsegaye

የአብን ዳግም ልደት!
*
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጅግ ዘግይቶም ቢሆን የወሰነው ውሳኔ ንቅናቄያችንን የሚታደግና ወደ ትክክለኛው መስመር የመለሰ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

በዚህ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ መሰረት አብን ወደ መስራች ጉባዔው ውሳኔዎች በመመለስ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ 1162/2011 የሚጠይቀውን ፎርማሊቲ ለማሟላት አዲስ ጠቅላላ ጉባኤ የሚጠራ ይሆናል።

የምርጫ ቦርድ ውሳኔ በተለይም በየደረጃው ላሉ ለውጥ ናፋቂ የንቅናቄያችን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ፓርቲውን ወደፊት በማስቀጠል ለአገርና ሕዝብ የሚያደርገውን ትግል በአዲስ ተስፋ እና በጽኑ ቁርጠኝነት እንዲነሳሱ የሚያስችል ነው።