Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @leyumerga
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.90K
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-02-10 21:20:52 #ቅዱስ_ሲኖዶስ

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት አጭር መግለጫ ከተናገሩት የተወሰደ ፦

" ... ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በደንብ አውርተናል።

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችን መሪነት በመንፈሳዊ ግርማ ፣ በቤተክርስቲያኒቱ ታላቅ ክብር ሆነን እግዚአብሔርም አክብሮን ብዙ ጥያቄዎቻችን ተመልሰዋል እነዛን አጠቃላይ ነገ ነው የምንገልፀው።

የነበረን ጥያቄ አጠቃላይ በመንግስት ፣ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንዲሁም በሌሎች እዛ ባሉት ተገቢ ጥያቄ እንደሆነ ተገንዝበዋል።

ስለዚህ ጉዳይ ነገ በሰፊው እንገልፃለን። የተገኘውን ውጤትም አጠቃላይ ነገ በሰፊው እንገልፃለን።

ዛሬ ይሄን አጭር መግለጫ ለመስጠት የወደድነው ምእመናኖቻችን ህዝባችን ስለሚጠብቅ ፤ ህዝባችን ምንም ከቆምንበት ዓላማ ወደኃላም ሆነ ወደፊት እንዳላልን ሁል ጊዜ የህገ ቤተክርስቲያን አቋም የፀና እንደሆነ፣ የቀኖና ቤተክርስቲያን የፀና እንደሆነ ይሄንን ለማረጋገጥ ነው።

ይሄ መፍትሄ እስካላገኘ ድረስ ተጋድሏችን ይቀጥላል። ስለዚህ ምእመናንን ወገኖቻችን ስለምታደርጉ የፀሎት ፣ የምክር አጠቃላይ የሞራል ድጋፍ በቤተክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፤ እግዚአብሔር ይስጥልን።

በፀሎት ትጉ፣ በምዕላ ትጉ ፤ እግዚአብሔር ፀሎታችንን ሰምቷል ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው አንዳንድ የምሰማቸው እና የምናያቸው ነገሮች ስላሉ ነው ዛሬ ጠቅላላ መግለጫ ያላወጣነው።

ነገ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ መግለጫ እንሰጣለን። "

@leyumerga
848 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 14:00:09
ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት አስቸኳይ ሰበር መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫውን ባወጣች ፵፰ ሰዓታት ውስጥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት፤ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ባልጣሰ መልኩ ከመንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያየት መንፈሳዊ በሯ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ጥሪ ማስተላለፏን አስታውሷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢፌዳሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይህንን የቤተ ክርስቲያን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይት ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጿል።

በዚህም መሰረት ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ።

#eotc
1.8K views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 13:56:50 የዛሬው የክልል መንግስታት መግለጫ !

ዛሬ የክልል መንግስታት #ተመሳሳይ_አይነት ይዘት ያላቸው መግለጫዎችን አውጥተዋል።

እስካሁን ድረስ መግለጫቸውን ለህዝብ ያሰራጩት ፦

- የሶማሌ ክልል
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል
- የደቡብ ክልል
- የሐረሪ ክልል
- የጋምቤላ ክልል መንግስታት
ሲሆኑ በመግለጫቸው " በተገቢው አካል ያልተፈቀደ እና የደህንነት ስጋት የሚፈጥር ሰላማዊ ሰልፍ " የተከለከለ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

የየክልሉ መንግስታት ባወጡት ተመሳሳይ አይነት ይዘት ባለው መግለጫ ፦  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተከሰተው ችግር የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖና መሰረት ባደረገ ውስጠ ደንብ / ውስጣዊ አሰራር ሊፈታ ይገባል የሚል አቋማቸውን ገልጸዋል።

" በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ከሃይማኖት ጉዳይነት አልፎ እየተወሳሰበና በርካታ እኩይ ዓላማ ያላቸው የሀገር ውስጥና የውጭ የፓለቲካ ኃይሎች ተቀናጅተው ኢትዮጵያን ለማዳከም ርብርብ እያደረጉ ናቸው " ያሉት የየክልሉ መንግስታት " ይህንንም በመረጃና በማስረጃ አረጋግጠናል ብለዋል።

በዚህም " ሐይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሀገርና የህዝብ ደህንነትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ማናቸውንም እንቅሳቃሴ እንቃወማለን " ሲሉ ገልጸዋል።

በተገቢው አካል ያልተፈቀደና የደህንነት ስጋት የሚፈጥር የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ማድረግም ተገቢነት ያለው ጉዳይ አይደለም ሲሉም አክለዋል።

የየክልሉ መንግስታት ባወጡት ተመሳሳይ አይነት ይዘት ባለው መግለጫቸው ፤ ህገ መንግስቱንና የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ውሳኔን መሰረት በማድረግ ማንኛውንም ሕገወጥ እንቅስቃሴ በመከላከልና በመቆጣጠር ህግ የማስከበር ኃላፊነታችንን እንወጣለን  ሲሉ አስገንዝበዋል።

@leyumerga
1.4K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 11:47:17 መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያዎችን አገልግሎት አቋርጧል

መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎቶችን በኢትዮጵያ የገደበው፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ችግር ጋር በተገናኘ መሆኑን “ኔት ብሎክስ” የተሰኘ የኢንተርኔት ግንኙነት አጥኚ ድርጅት ይፋ አድርጓል፡፡

አገልግሎቱ የተቋረጠባቸው የማኅበራዊ ሚዲያዎች ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ እና ሜሴንጀር ሲሆኑ፣ አገልገሎቱ መቋረጥ የጀመረው ትናንት ምሽት ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መከፋፈል ምክንያት በጸረ-መንግሥት ተቃውሞ በቀጠለበት ወቅት፣ የማኅበራዊ ሚዲያ እና የመልዕክት መላላኪያ መድረኮች ፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ቲክቶክ እና ቴሌግራም መዘጋታቸውን የኔትወርክ መለኪያዎች ያሳያሉ።

እንደ “ኔት ብሎክስ” ሪፖርት፣ በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መንግሥት የአገልግሎት ዕቀባ የጣለው በመንግሥት በሚተዳደረውና የኢንተርመኔት አገልግሎት አቅራቢ በሆነው በኢትዮ ቴሌኮም በኩል ነው ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ መንግሥት ያቋረጠውን አገልግሎት፣ የመንግሥት የኢንተርኔት ሳንሱር እርምጃዎችና ገደቦችን ማለፍ በሚችሉ ቨርቹዋል ፕራይቬት ኔትዎርክ (ቪፒኤን) አገልግሎቶችን መጠቅም እንደሚቻል ድርጀቱ ጠቁሟል፡፡ አሁን ላይ ብዙዎች ይህንኑ አግልገሎት ተጠቅመው የማኅበራዊ ሚዲያዎችን አገለግሎት እየተጠቀሙ መሆኑን የሚያመላክቱ መረጃዎች አሉ፡፡
https://t.me/proxy?server=cheha-ba-jan-khod-door-az-rokh-janan-khod-kardam.sbs&port=443&secret=7vQ1mpsyX_HR5QhN8OD3U3ttc24uY29t

@leyumerga
1.5K viewsedited  08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 19:08:24
የዩኒቨርስቲ  ምርጫ ማስተካከያ ቀን እስከ የካቲት 03/2013 ዓ.ም መራዘሙን ስለማሳወቅ

በ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ እንዲሁም በመንግስት ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን እስከ የካቲት 03/2015 ዓ.ም 12፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያስተካክሉ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን እያሳወቅን በየትምህርትቤቱ በተወከሉ መምህራን በኩል ምርጫችሁን ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማስታወሻ፤

1. ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደማህበራዊ ሳይንስ ቀይራችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች መቀየር የምትችሉት ዩኒቨርስቲ ከገባችሁ በኋላ ዩኒቨርስቲዎቹ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑ ብቻ መሆኑን አዉቃችሁ የምርጫ ማስተካከያችሁን በጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳዉቃለን፡፡

2. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የትምህርት የልህቀት ማዕከል ሆኖ መደራጀቱን ግንዛቤ እንዲወሰድ።

ትምህርት ሚኒስቴር

@leyumerga
1.1K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 18:53:08 ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትላንት ምሽት የመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል " ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ " ን አስመልክቶ የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ እንደማይቀበል አሳውቋል።

" መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል " ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ፦

- ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር

- በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣

- ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣

- ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤

- በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ ጠይቋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ መንግሥት #በዚሁ_አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት 5/2015 ዓ/ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን አሳውቋል።

መንግሥት ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን ያሳሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ " ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ ፣ ቀኖናዊ እና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑን እናሳውቃለን " ብሏል።

ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም ሲል አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በህገመንግስቱ የተደነገገ መሰረታዊ መብት መሆኑን ገልጾ ቤተክርስቲያን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን ብሏል። 

@leyumerga
1.5K views15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 14:36:07
ወለቴ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ከባድ ተኩስ ተከፍቷል፣ በጥይት ተመተው ጉዳት የደረሰባቸውም እንደሚገኙ ተሰምቷል

ወለቴ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ህገወጥ ቡድኖች ተደራጅተው ሰብረው ለመግባት እየሞከሩ እንደሚገኙ ከስፍራው የደረሱን የምስል መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል። ምእመናኑ ባላቸው አቅም ቤተክርስቲያና ቅጥር ግቢ ውስጥ በመሆን የተቻላቸውን እያረጉ ይገኛሉ። የኦሮሚያ ልዩ ሀይል በቀጥታ ቤተክርስቲያኗን ወደ ሚጠብቁ ወጣቶች ላይ ተኩስ ከፍተዋል፣ ብዙ ወጣቶች በጥይት ተመተው ጉዳት እንደደረሰባቸው ተሰምቷል።

ትኩረት ያሻቸዋል።

@leyumerga
2.6K views11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 11:06:15
#MOE

ሚኒስቴሩ ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳሰበ

የካቲት 2/2015 (ዋልታ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ከተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ጋር የተወያዩ ሲሆን የመውጫ ፈተና በመጪው ሐምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ ለመሆንም ተማሪዎች በየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን ሴሚስተር ፈተና መውሰድና ኮርሶችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ለፈተናው በሁሉም የትምህርት መስኮች ላይ የተመረጡ ኮርሶች የብቃት ልየታ ተደርጎላቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲያውቁት መደረጉን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በአሁኑ ወቅት የፈተና ንድፈ ማሳያና የፈተና ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች በቀሪዎቹ አምስት ወራት ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሳቸውን ለፈተናው ብቁ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችም ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ሲመለሱ ተማሪዎች ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንቶች መገኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#Walta_tv
@leyumerga
3.2K viewsedited  08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 23:04:53
★ፀደይ ባንክ የስራ ማስታወቂያ 100 ክፍት ቦታዎች

Deadline: February 14, 2023

Tsedey Bank invites qualified applicants for the Branch Manager job positions.

● Professions: ሹፌር, Accounting, Business, Economics, Marketing, management, Banking and finance, Business Administration, Human Resource Management, Secretarial Science,  Office Management, Law, Computer Science, Information Science, Information Systems, Information Technology or related fields.

How to Apply Online??

https://abyssinajob24.com/tsedey-bank-vacancy-2023

@leyumerga
907 viewsedited  20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 21:29:38 ከፀጥታና ደኅነት  የጋራ ግብረ–ኃይል ወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ወቅታዊ ሁኔታ የገመገመው የፀጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አለመግባባቱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም የጸና እምነት አለው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋራ ግብረኃይሉ በተለያዩ ሚዲያዎች ከሚሰራጩ ዘገባዎችና በመረጃ ስምሪቱ ባሰባሰባቸው ግብዓቶች መሠረት በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ሕገወጥ የሰልፍ ጥሪ በማድረግ የዜጎች ህይወት የሚቀጠፍበት አጋጣሚ እንዲፈጠር ቅስቀሳዎች እየተደረጉና ሌሎችም ግጭት ቀስቃሽተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

ይህ አካሄድ ክስተቱን እንደ ሽፋን በመጠቀም ከውስጥና ከውጭ ተቀናጅተው ሀገራችንን ለማፍረስለሚሰሩ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በር እየከፈተ መሆኑን መላው የሀገራችን ሕዝብና የዕምነቱ ተከታዮች ግንዛቤ ሊወስዱ እንደሚገባ የጋራ ግብረ-ኃይሉ አመልክቷል።

@leyumerga
2.0K viewsedited  18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ