Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @leyumerga
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.90K
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-01-27 22:01:32
በሀገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ባ1 ሺህ 161 መደበኛ ትምህርት ቤቶች አንድም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ብሔራዊ ፈተና አላለፈም።

- የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ካስፈተኑ 2 ሺህ 959 የመደበኛ ትምህርት ቤቶች መካከል ነው 1 ሺህ 161 የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪዎችን እንዳላሰለፉ የታወቀው።

- ከአጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 798 ትምህርት ቤቶች ቢያንስ አንድ ተማሪ አሳልፈዋል።

- 7 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች በሙሉ ያሳለፉ ሲሆን እነዚህም ትምህርት ቤቶች ፦

ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ ቤት፣
ኦዳ አዳሪ ልዩ ት/ቤት ፣
ባህርዳር ስቴም ት/ቤት  ፣
ወላይታ ሊቃ ት/ቤት፤
የጎንደር ማህበረሰብ አቀፍ ት/ቤት እና ከግል ትምህርት ቤት ደግሞ ለባዊ ት/ቤት ናቸው።

ምንጭ፦ WMCC
@leyumerga
6.5K viewsedited  19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 17:44:33
ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ።

ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ፤ የተሻለ ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል።

ይሁንና እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቁመዋል።

ተማሪዎቹ " የደከሙባቸው ትምህርቶችን” ለአንድ ዓመት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እየተማሩ ከቆዩ በኋላ፤ በዓመቱ መጨረሻ ፈተና ወስደው ካለፉ በዩኒቨርስቲዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር
#MoE

@leyumerga
7.4K views14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 15:26:26
ትምህርት ሚኒስቴር ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደማይቀላቀሉ ገለፀ

ነገር ግን የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት በውጤታቸው መሰረት ተጨማሪ ተማሪዎችን በመቀበል ለቀጣይ ዓመት ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት እንዲያገኙ ይሰራል መባሉን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግባል።

@leyumerga
7.4K viewsedited  12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 15:04:34 የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችን ይፋ አደረገ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት ዋና ዋና ግኝቶችን ይፋ አድርጓል ።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2014 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች በአዲስ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎች  መሰጠቱን አስታውሰው ይህ አዲስ አካሄድ ቀጣይ እርምጃዎቻችንን የሚለኩ ነበሩ ብለዋል።

ሀቀኛ እና ትክክለኛ የተማሪዎችን የትምህርት ክህሎት በመለካት  የፈተና ሂደቱ ከኩረጃ፣ የፈተና ስርቆት የፀዳ ነው ያሉት ሚኒስትሩ በዚህ ፈተና ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ የሚኮሩበት ነው ብለዋል።

በክልል ደረጃ ይህየ ነው የሚባል የውጤት ልዩነት እንደሌለ የተገለፀ ሲሆን አዲስ አበባ፣ ሀረሪ እና ድሬደዋ የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።

ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ ከ 700፤  666 ያስመዘገበ ሲሆን 650 ሴት ተማሪ አስመዝግባለች ።

በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 524 አስመዝግቧል።

እነዚህ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎይ በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል ተብሏል።

@leyumerga
7.4K views12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 11:03:36
የትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤት ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል።

የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ትላንት ለሊት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

ከውጤቱ ጋር በተያያዘ አጠቃላይ መግለጫ ዛሬ ከሰዓት 8:00 በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) እንደሚሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

" የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ውጤታቸው ከ50 በመቶ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከ28 ሺህ እንደማይበልጥ" በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እየተዘገበ ይገኛል

ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች አሐዝ ከ28 ሺህ " #ብዙም_እንደማይርቅ " ቲክቫህ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።

እስካሁን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ያልተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

@leyumerga
8.1K viewsedited  08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 00:53:54
Grade 12 Entrance Exam Results 2023

የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።
https://abyssinajob24.com/grade-12-entrance-exam-results

@leyumerga
8.9K viewsedited  21:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 00:10:50
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤታቸውን ፦

https://eaes.edu.et/
ባለው የኔትዎርክ_መጨናነቅ ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት እንደተቸገሩ እየገለፁ ሲሆን ተማሪዎች አማራጭ የውጤት መመልከቻ ዘዴዎችን በtelegram bot በቴሌግራም ላይ  https://t.me/eaesbot
ማየት ይችላሉ። or sms በ6284 አጭር የጽሑፍ
መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ መጠቀም ይችላሉ።

@leyumerga
9.1K viewsedited  21:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 19:50:21
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ተለቀቀ።

ተፈታኞች ከዛሬ ጥር18 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ፡-
• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ  https://t.me/eaesbot
ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል።

ማሳሰቢያ፡-

• ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ፡፡

• የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ ይጠቀሙ፡፡ ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት ራስዎን ይጠብቁ፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ጥር 18/2015 ዓ.ም
አዲስ አባባ - ኢትዮጵያ

@leyumerga
10.3K viewsedited  16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 09:54:34
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ቡድን ዛሬ ወደ ትግራይ መቐለ እንደሚጓዝ ተሰምቷል።

ይኸው ቡድን 5 አባላት ያሉት ሲሆን በትግራይ ትምህርት ለማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ለመምከር ነው ዛሬ ወደ መቐለ እንደሚያቀና ፋና ብሮክዳስት የዘገበው።

በትምህርት ሚኒስቴር  የአስተዳደር እና መሠረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ ፤ " ቡድኑ ወደ መቐለ የሚያቀናው በትግራይ ክልል የከፍተኛ እና አጠቃላይ ትምህርትን ለማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ለመምከር ነው " ብለዋል።

የሥራ ኃላፊዎቹ ቡድን በመቐለ ቆይታው ከመቐለ እና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች ጋር ትምህርት ዳግም መጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክር ገልፀዋል።

በተጨማሪ በትግራይ ክልል አጠቃላይ ትምህርትን ዳግም ለማስጀመር በሚቻልበባቸው ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ አቅንቶ በዩኒቨርሲቲው ዳግም የመማር ማስተማር ሥራ እንዲጀመር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር አድርገዋል።

@leyumerga
8.6K viewsedited  06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 09:37:48
★ [Urgent] አሀዱ ባንክ አዲስ የስራ ማስታወቂያ

Deadline: January 28, 2023

Ahadu Bank would like to invite qualified candidates for the following job positions.

Professions: Accounting, Management, Business, Finance, Marketing, Economics, Banking, Business administration, Marketing Management, Banking and Insurance, Banking and Finance or another related field of study.

• Position 1: Customer Services Officer-I
• Position 2:Customer Service Officer II
• Position 3: Senior Customer Services Officer 

How to Apply Online??

https://abyssinajob24.com/ahadu-bank-urgent-vacancy
share to your friends
@leyumerga
7.4K viewsedited  06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ