Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @leyumerga
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.90K
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-19 12:39:57
ፕሬዝዳንት ፑቲን በሩሲያ በተያዘችው የዩክሬኗ ማሪፖል ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ!!

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሩሲያ በተያዘችው የዩክሬኗ ማሪዮፖል ድንገተኛ ጉብኝት አድርገዋል።

የሩሲያ ብሄራዊ ሚዲያ እንደዘገበው ጉብኝቱ የመጣው ፑቲን ክሬሚያ ከዩክሬን ተገንጥላ ሩሲያን የተቀላቀለችቀትን ዘጠነኛ ዓመት ለማክበር ባደረጉት ድንገተኛ ጉብኝት ማግስት ነው።

ጉብኝቱ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ ካወጣ ከሁለት ቀናት በኋላ የተደረገም ነ። ፑቲን በሄሊኮፕተር በመብረር ወደ ማሪፖል እንደደረሱ የሩሲያ የዜና ምንጮች ክሬምሊንን ጠቅሰው ዘግበዋል። ፑቲን ለአንድ ዓመት በዘለቀው ጦርነት ወደ ጦር ግንባር ሲቀርቡ የመጀመሪያ ነውም ተብሏል።

ፑቲን መኪና እያሽከረከሩ በከተማዋ በሚገኙ በርካታ ወረዳዎች እየተዘዋወሩ ነዋሪዎችን አነጋግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የወታደሮቻቸውን ሞራል ለማሳደግ እና የጦር ስልታቸውን ለማጎልበት ወደ ጦር ሜዳው ብዙ ጉዜ ተመላልሰዋል።

ፑቲን ግን ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ "ልዩ ወታደራዊ ተልዕኮ" በምትለው ጦርነት በዋነኛነት በክሬምሊን ውስጥ ቆይተዋል።ጦርነቱ 13ኛ ወሩን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ኪየቭና አጋሮቿ "የመሬት ዘረፋ" ይሉታል። ጦርነቱ በዩክሬን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀለ ነው።
2.1K views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 22:10:55 #መተሐራ

በትላንትናው ዕለት በ #መተሐራ_ከተማ በደረሰ ጥቃት 6 የጎዳና ተዳዳሪዎችን ጨምሮ 8 ሰዎች ተገደሉ።

በመተሐራ እና አካባቢው ያሉ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሁንም በታጣቂዎች እየደረሰ ያለው ጥቃት መቀጠሉን ገልጸዋል።

በትላንትናው ዕለትም ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 6 የጎዳና ተዳዳሪዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 8 ሰዎች መገደላቸውን ጠቅሰዋል።

ጥቃቱ ትላንት ሐሙስ መጋቢት 07 ቀን 2015 ምሽት 3:00 አካባቢ መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን ህይወታቸው ካለፉ ሰዎች በተጨማሪ በ4 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ነው የገለጹልን።

ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከልም ወደ አዳማ ሪፈር የተጻፈላቸው መኖራቸውንም ነው የጠቆሙት።

አንድ የቤተሰባችን አባል ፦ " ሌሊት ላይ መጥተው ሰው ገድለው ነው የሚሄዱት፤ ከ6 ወር በፊት 15 ሰዎች ገድለዋል፤ ከአንድ ወር በፊት ደግሞ እንዲሁ 4 ሰዎች ተገድለው ነበር። ትላንትና ደግሞ የጎዳና ልጆችን ጨምሮ 8 ሰዎችን ገድለዋል ፤ ማን እንደገደላቸው አይታወቅም፤ ያው ሁል ጊዜ ሸኔ ነው የሚባለው እንደዛ እየተባለ ነው እስካሁን መለየት አልቻልንም። ...መከላከያ በተደጋሚ ይመጣል፤ እነርሱ ሲመጡ እነዚ ይሸሻሉ ከዚያ ደግሞ ትንሽ መከላከያ ራቅ ሲልላቸው መጥተው ሰዎች ይገላሉ። " ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።

አክለውም ፤  " በከተማችን ጥቃቱ በተደጋጋሚ የሚፈጸም ሲሆን የዚህኛው ዙር ጥቃት እጅግ ሰብዓዊነት በጎደለው መልኩ በጎዳና ላይ የነበሩ ልጆች ላይ የተፈጸመ በመሆኑ በጣም አሳዛኝ ነው። ይህ ምንም ዓላማ የሌለውና ህብረተሰቡን ለማሸበር የተደረገ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ጥቃቱ ከመድረሱ በፊት መብራት እንዲሁም ኔትዎርክ ጠፍቶ እንደነበር የገለጹልን የመተሀራ ቤተሰቦች "ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ ፊሽካ ነፍተው ከከተማው ሸሹ፤ ይህ ከዚህ በፊት በነበሩት ጥቃቶችም በተደጋጋሚ የተደረገ ነው። " ሲሉ መረጃቸውን አድርሰዋል።

ስለደረሰው ጥቃት እንዲሁም ጥቃቱን ተከትሎ የመንግስት የጸጥታ አካላት ስለወሰዱት እርምጃ ከከተማው ከአስተዳደር አካላት መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
1.5K views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 08:43:21
አብነት ገብረመስቀል በአላሙዲ ላይ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ሆነ

"ስለሚፈለግ ከሃገር ሸሽቶ ጠፍቷል" በሚል በፍርድ ቤት የተነገረበት የአላሙዲ የረዥም ጊዜ ሠራተኛ አብነት ገብረመስቀል፤ ከሼኩ ጋር በገባበት ውዝግብ ከአሜሪካ ሆኖ በጠበቆች አማካኝነት በፍርድ ቤት ይግባኝ ቢጠይቅም ውድቅ እንደተደረገበት ዘ-ሐበሻ እጅ የገባው የፍርድ ቤት ሠነድ አመልክቷል።
የቀድሞ የአዲስ አበባ ከንቲባ እና የማዕድን ሚኒስትር ከነበሩት ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአሜሪካ ተቃውሞ ሲያጋጥማቸው፤ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ካፌ ውስጥ ተቀምጦ በቪድዮ የታየው አብነት በቅርቡ ፍርድ ቤት ከቦሌ ታወርስ ጋር በተያያዘ ከአላሙዲ ጋር በገባው ውዝግብ ከስራ አስኪያጅነት እንዲነሳ እና በ እጁ ያለውን የድርጅቱን ዶኩመንት እንዲያስረክብ ፈርዶበት እንደነበር ዘግበን ነበር። ሆኖም አብነት ከአሜሪካ ሆኖ በጠበቃው አማካኝነት ፍርድ ቤቱን ይገባኝ ቢጠይቅም፤ ፍርድ ቤቱ ከሳሽ አላሙዲ ወይም ጠበቆቻቸው መቅረብ ሳያስፈልጋቸው የአብነትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎበታል።
1.5K viewsedited  05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 23:15:57 ግብፅ ኃላፊነት ከጎደለው ንግግር እና ማስፈራሪዎቿ እንድትታቀብ ኢትዮጵያ አሳሰበች!

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የህዳሴ ግድብን በተመለከተ “ሁሉም አማራጮች ክፍት ናቸው” በማለት የሰጡትን መግለጫ ኃላፊነት የጎደለው ንግግር ሲል ውድቅ አደረገ።ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ፥ ግብጽ የዓባይ ግድብን አስመልክታ ለኢትዮጵያ ማስፈራሪያ የታከለበት መግለጫ ሰጥታለች ብሏል፡፡

ይህም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር እና የአፍሪካ ህብረት ድንጋጌን በግልጽ የሚጥስ መሆኑን ገልጿል፡፡በተጨማሪም ይህ ድርጊት በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ራሷኑ ግብጽና ሱዳን በፈረንጆቹ መጋቢት 2015 ያደረጉትን ስምምነት የጣሰም ነው ብሏልሚኒስቴሩ በመግለጫው፡፡

በዚህም ግብጽ ተገቢ ያልሆኑና ህገወጥ መግለጫዎችን ከማውጣት እንድትቆጠብ አሳስቧል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘም የሚመለከታቸው አካላት ግብጽ የዓለም አቀፉ ግንኙነት ደንብን እየጣሰች መሆኗን ልብ ሊሉ ይገባልም ነው ያለው።ግብፅ በማስፈራራትና ከህግ ውጭ ነገሮችን በማድረግ ፍላጎቷን ልታሳካ እንደማትችልም ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡

ሆኖም በመከባበርና በመተማመን እንዲሁም የዓለም አቀፉን ህግ ባከበረ መልኩ ከሆነ ሀገራቱ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር መግባባት ላይ ይደረሳሉ የሚል ጽኑ እምነት እንዳለውም ነው የገለጸው፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞም ኢትዮጵያ አሁንም ሁሉም ወገን አሸናፊ እንዲሆን የሚል አቋማ ላይ እንደሆነችም አስታውቋል።
368 views20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 22:21:26
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነት እንደምታጠናክር ተናገሩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጡ ነው።
በመግለጫቸውም÷ በፕሪቶሪያ እና በናይሮቢ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተፈጻሚነት ላይ በሁለቱም ወገን የተጠናከረ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አንስተዋል።
ዘላቂ ሰላም ለማምጣትም የሽግግር ፍትህን አጠናክሮ መተግበር እና ሃገራዊ ምክክር ማከናወን ተገቢ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
790 views19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 15:26:22 ኢዜማ ከመንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት “መልሶ ለማጤን” የሚያስችል ጥናት ሊያካሄድ ነው ተባለ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ከመንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት “መልሶ ለማጤን” የሚያስችል ጥናት የሚያደርግ ግብረ ኃይል ማቋቋሙን የፓርቲው የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ገለጹ። የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በበኩላቸው፤ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የፓርቲውን የአምስት ዓመት ጉዞ ትንተና የሚያደርግ ነው ብለዋል።

የፓርቲው ብሔራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ግብረ ኃይሉን ያቋቋመው፤ ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 2፤ 2015 ባካሄደው ስብሰባ መሆኑን የፓርቲው ምንጮች ተናግረዋል። ብሔራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በዚሁ ስብሰባው፤ የፓርቲውን የስድስት ወራት አፈጻጸም የገመገመ ሲሆን እና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይም ውይይት አድርጓል።

በወይይቱ ላይ የመሪው ክንፍ ሪፖርት ማቅረቡን የተናገሩት የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ፤ ፓርቲው ከመንግስት ጋር ያለው ግንኙነት ላይ ውይይት እንደተደረገበት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል። “ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን ስንገመግም አንድ አብረን ያየነው አጀንዳ [እንጂ]፤ ለብቻው የቀረበ አጀንዳ አይደለም” ሲሉም ጉዳዩ ውይይት የተደረገበትን አውድ አስረድተዋል።

የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ግን ፓርቲው “ከመንግስት ጋር ያለውን አብሮ የመስራት ግንኙነት፤ እንደገና ማጤን እንደሚያስፈልገው” ውሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል። ኢዜማ ከመንግስት ጋር ያለውን ግንኙት ለመፈተሽ የወሰነው፤ “መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከሰቱ ችግሮች የሚሰጣቸው ምላሾች ችግሮችን የሚያባብሱ እና ሌሎች አዳዲስ ችግሮችን የሚፈጥሩ በመሆናቸው ነው” ሲሉ የፓርቲው ምንጮች ምክንያቱን አብራርተዋል። 

ይህንንም በተመለከተ ጥናት የሚያደርግ ግብረ ኃይል መቋቋሙን እና የሁለት ሳምንት ጊዜ እንደተሰጠው እነዚሁ ምንጮች አስረድተዋል። ከግብረ ኃይሉ ግምገማ በኋላ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው፤ ጠቅላላ ጉባኤ ሊጠራ እንደሚችልም ጠቁመዋል። በኢዜማ መተዳዳሪያ ደንብ መሰረት፤ በየሶስት ዓመቱ የሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲው ከፍተኛ የስልጣን አካል ነው።  የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ፤ አስቸኳይ ጉባኤ የመጥራት ስልጣን እንዳለው መተዳደሪያ ደንቡ ይደነግጋል።

ኢዜማ ከመንግስት ጋር ለመስራት ሲወስን “በትብብር ለውጥ ማምጣት የሚቻልባቸው ጉዳዮች አሉ” ከሚል ትንተና መሆኑን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል። “በገዢው ፓርቲ ውስጥ ያሉ የብሄር መጓተቶች” እንዲሁም ከሰሞኑ ከአድዋ ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ክስተቶች “ኢዜማ ከመንግስት ጋር መስራቱ ላይ የራሱ ተጽዕኖ ይኖረዋል” የሚሉት ዶ/ር ሙሉዓለም፤ እንዲያም ቢሆን ግን ጉዳዩ የብሔራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው “ዋነኛ አጀንዳ አልነበረም” ሲሉ አስተባብለዋል።

Via Ethiopia Insider
409 views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 08:18:37
Washington post ከውስጥ አዋቂዎች አገኘሁት ባለው ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ የህወሃቱ ሊቀመንበር የሆነው ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ክልል አዲስ ለሚዋቀረው ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ አይፈልግም ሲል ዘግቧል።
1.2K views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 18:41:45
ባልደራስ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ እንዳላደርግ በጸጥታ ሀይሎች ተከለከልኩ ብሏል። ሆቴሉ ከላይ ያለውን መግለጫ አውጥቷል።
2.5K views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 17:54:50
በኬንያ 21 ኢትዮጲያውን ስደተኞች የረሃብ አድማ አድርገዋል መባሉን ተከትሎ መንግስት ዜጎቹን ወደ ሀገር ለመመለስ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም በመንግስት በኩል የተካሄዱ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያውን እንደሃገራቸው እንዲኖሩ የሚፈለግበት ሀገር አንዷ ኬንያ መሆኗን አምባሳደር መለሰ አለም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ህገወጥ ስደተኞች በተለያየ መልኩ ወደ ኬንያ እንደሚገቡ አክለዋል።

ሆኖም የትኛውም ሃገር ውስጥ የጉዞ ሰነድ ሳይዙ መገኘት የማይቻል ቢሆንም በኬኒያ የሚያዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንግልት ሳይደርስባቸዉ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ እንደሚደረግ መናገራቸው. ታውቋል

በአሁኑ ሰዓት በኬኒያ እስር ቤት ዉስጥ በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ  21 የሚሆኑት ህገወጥ ስደተኛ  ኢትዮጵያውያን በተመለከተ ለአምባሳደር መለሰ በቀረበላቸው ጥያቄ በተለመደው መልኩ ወደ ሀገር እንዲመለሱ እንደሚደረግ ገልፀዋል።

እንደ ሀገር ስደተኞችን የማስመለስ ስራ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራ ቢሆንም በተደጋጋሚ በህገወጥ መልኩ ጉዞ የሚያደርጉ ዜጎች መኖታቸው ስራውን አስቸጋሪ ማድረጉም አክለዋል።
803 views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 21:19:04
#AddisAbaba

" የቤት ኪራይ ዋጋ አከራዮች እስክ ሰኔ #እንዳይጨምሩ ተወስኗል "

የአዲስ አበባ አስተዳደር ካቢኔ 2ኛ አመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ካቢኔው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ፦

1. የመኖሪያ ቤቶችን በመንግስትና የግል አጋርነት በ70/30 አሰራር መቶ ሺህ የሚደርሱ ቤቶችን ለመገንባት የተዘጋጀውን 35 ሄክታር መሬት ላይ ተወያይቶ ወስኗል።

2. ሃገራዊ ፋይዳ ያላቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች እና የስራ እድል የሚፈጥሩ የ373 ፕሮጀክቶች  የመሬት  ጥያቄ እነሱም ፦
2.1. ለኢንዱስትሪ ልማት
2.2 ሆቴሎችና ሞሎች ፣
2.3 የሀይማኖት ተቋማት ፣ 
2.4 ቀደም ሲል በካቢኔ ተወስነው የመሬት ለውጥ የቀረበባቸው ቦታዎች ፣ ለተለያዩ የግንባታ ግባዓት ማስቀመጫ የሚሆኑ ጊዜያዊ መጠቀሚያ ቦታዎች ናቸው።

3. ወቅታዊ የኑሮ ውድነትና የገበያ መረጋጋት የዋጋ መናር መነሻ በማድረግ በአስቸኳይ ምርት ወደ ከተማ እንዲገባና እንዲሰራጭ ግብረ ኃይል አቋቁሟል።

4. ለተማሪዎች ምገባ የሚያቀርቡ እናቶች በአሁኑ ዋጋ ማቅረብ መቸገራቸውን መነሻ በማድረግ ለተማሪዎች ምገባ በወር 54,000,000 ብር (ሀምሳ አራት ሚሊየን) በዓመት 540,000,000 ብር (አምስት መቶ አርባ ሚሊየን) ተጨማሪ በጀት አጽድቋል፤ ይህ ማለት ለአንድ ተማሪ በቀን ሃያ ብር የነበረው ወደ የሀያ ሶስት ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል።

5. ከወቅቱ ዋጋ መናር እና የገበያ አለመረጋጋት ጋራ ተያይዞ የነበረው የቤት ኪራይ ዋጋ አከራዮች እስክ ሰኔ እንዳይጨምሩ ተውስኗል።

(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር)
1.0K viewsedited  18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ