Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @leyumerga
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.90K
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-02-07 21:05:39 በቱርክ እና ሶርያ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ5 ሺኅ በላይ ሆኗል

በደቡብ ምስራቅ ቱርክ በጋዚያንቴፕ ከሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በተከሰተዉ ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በቱርክ ብቻ ከ3,549 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል።የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን በሰኞው አሰቃቂ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በከፋ ጉዳት በደረሰባቸው 10 ግዛቶች ዉስጥ ለሦስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።በ10 ከተሞች ከ13 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሀገሪቱ ከ1939 ዓ.ም ወዲህ ባጋጠሟት ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጎድተዋል።

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በመሬት መንቀጥቀጡ ወደተመቱ አካባቢዎች የፍለጋ እና የነፍስ አድን ቡድን የሚሰሩ ባለሙያዎች ወዲያውኑ መላኩን ገልጸዋል። በጉዳዩ ላይ መረጃ ለማሰባሰብ ከተጎዱት የስምንት ግዛቶች አስተዳዳሪዎች ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የጽህፈት ቤታቸው መግለጫ አስታውቋል።ፕሬዝዳንቱ አክለዉ አሜሪካ፣ እንግሊዝን እና ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ እርዳታ ላደረጉ 70 ሀገራት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ኳታር 10,000 ተንቀሳቃሽ ቤቶችን በቱርክ እና ሶሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ አካባቢዎች ከ120 የነፍስ አድን ሰራተኞችን ጋር ልካለች፡፡ከ11 ዓመታት በላይ በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት ክፉኛ በተጎዳችው ሶሪያ፣ ከ1,602  በላይ ሰዎች መሞታቸውንና 3,500የሚያህሉ ሰዎች መቁሰላቸውን የሶርያ የመንግስትና ወዶ ገቡ የነጭ ቆብ የረድኤት ተቋም አስታዉቋል። የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው በሶርያ ሐማ፣ አሌፖ እና ላታኪያ ግዛቶች በርካታ ሕንፃዎችን አውድሟል።የዩናይትድ ስቴትስ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በጋዚያንቴፕ ከተማ አቅራቢያ 17.9 ኪሜ ያለው ጥልቀትና  በሬክተር  ስኬል 7.8 የተለካ አደጋ መድረሱን ይፈ አድርጓል።

የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው የተሰማው በዋና ከተማዋ አንካራ እና በሌሎች የቱርክ ከተሞች እንዲሁም በሰፊው የሀገሪቱ ክልል መሆኑን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።በአደጋው በርካታ ሕንፃዎች የፈረሱ ሲሆን በዲያርባኪር ከተማ አንድ ሰፊ የገበያ አዳራሽ ወድሟል።

አንድ እማኝ  እንደተናገሩት እኔ ያረፈኩበት ቤት ለ45 ሰከንድ ያህል መንቀጥቀጡን ተናግረዋል። የቱርክ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪዎች አደጋው በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 4 የተለካ እንደሆነ ገምተዋል። ከደቂቃዎች በኋላ ሁለተኛ መንቀጥቀጥ አካባቢውን እንደመታ ተናግረዋል።ቱርክ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከሚደርስባቸው ዞኖች ውስጥ አንዷ ነች። እ.ኤ.አ. በ 1999 በቱርክ ሰሜን ምዕራብ ክፍል በደረሰ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ17,000 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።


@leyumerga
4.3K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 22:04:28
#MoE

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ እንድታስተካክሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና #የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች፣ ነፍሰጡር የሆናችሁ፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ያለባችሁ ተማሪዎች፣ ...) ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ አለባችሁ፦ https://student.ethernet.edu.et

@leyumerga
1.7K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 15:10:57
በጉራጌ ዞን በዛሬዉ እለት የስራ ማቆም አድማ ተደረገ!!

በዛሬዉ እለት በጉራጌ ዞን መዲና በሆነችዉ ወልቂጤ ከተማ እና ሌሎች አካባቢዎች ላይ የስራ ማቆም አድማ መመታቱን ተሰምቷል። አድማዉ ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ መሆኑንም ተገልጿል።

ከትናንት በስቲያ የክልሉ መንግስት ህብረተሰቡ የስራ ማቆም እድማ ቅስቀሳ የሚያደርጉ አካላትን ጥቆማ እንዲሰጡት ጠይቆ ነበር።

የጉራጌ ዞንን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚል በአዲስ መልኩ ለማደራጀት ዉሳኔ መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን የዞኑ መንግስትም ይህንን ተግባራዊ ወደ ማድረጉ ገብቻለሁ ብሏል።ሆኖም የዞኑ ነዋሪዎች አሁንም ጥያቄዎች እንዳሏቸዉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እያንጸባረቁ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት እየተደረገ ያለዉ የስራ ማቆም አድማ ለአራተኛ ዙር መሆኑም ታውቋል።

@leyumerga
3.5K viewsedited  12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 12:35:39
★ ሂጅራ ባንክ አዲስ የስራ ማስታወቂያ
[ 80 ክፍት መደቦች]

Deadline: Feb 15, 2023

Hijra is looking for dynamic, energetic, conscious and service oriented individuals to make part of its team.

Professions: Accounting, Business, Economics, Marketing, management, Banking and finance, Accounting and Finance, Business Administration and related fields.

• Position 1: Customer Service Officer
• Position 2: Senior Customer Service  Officer
• Position 3: Branch Operation Supervisor
• Position 4: Branch Manager

How to Apply??

https://abyssinajob24.com/hijra-bank-job-vacancy-2023

@leyumerga
3.6K viewsedited  09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 20:36:16
#eotc

ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ፡፡

በጾመ ነነዌ  የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን መግለጫ ሰጥቷል፤ በዚህም የምእመናን ድርሻ ምን እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ሁሉም ምእመናን እና ምእመናት በጾመ ነነዌ በሦስቱም ቀናት ጥቁር ልብስ መልበስ፣ በጸሎት መርሐ ግብሩ ተገኝቶ ጸሎት መጸለይ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና የአባቶችን መልእክት ሰምቶ መተግበር እንደሚገባው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡

የጸሎት መርሐ ግብሩም ጠዋት ኪዳን እና ምሕላ፣ ቅዳሴ፣ የሰርክ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር እንዲሁም ማታ የቤተሰብ ጸሎት ናቸው፡፡
በመጨረሻም ምእመናን ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላም ምንም ዓይነት መፈክር ይዞ መምጣት የማይቻል መሆኑን አስረድተዋል።

@leyumerga
1.3K viewsedited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 14:42:46
በሻሸመኔ ከተማ ሁለት ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ተገደሉ።

በዛሬዉ እለት በሻሸመኔ ከተማ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በተቀሰቀሰው ግጭት የሞቱ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት የደረሰ ሲሆን በአራቱ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።

አብያተ  ክርስቲያናት ውስጥ ያሉት ምእመናን እስካሁን ድረስ በቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳሉ ናቸው ያለዉ ዘገባዉ፤ ነገር ግን አሁን ላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣውን የጸጥታ ኃይል አባላት በዱላ እያባረሩ ይገኛሉ ብሏል።

በዚህ ሰዓትም የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከሻሸመኔ እስከ አርሲ ነገሌ ድረስ ያለውን ቦታ ተቆጣጥሯል ሲል ዘገባዉ አክሏል።

@leyumerga
3.7K views11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 21:57:02
★ ኦሮሚያ ባንክ አዲስ የስራ ማስታወቂያ በ 0 አመት [ 0 experience]

Deadline: Feb 11, 2023

Bank of Oromia invites fresh applicants for the following banking vacancies.

Professions: Accounting, Accounting  &  Finance, Management, BusinessManagement, Marketing Management, Economics, Banking & Finance, Information Technology, Computer Science or any other related field of studies.

How to Apply??

https://abyssinajob24.com/oromia-bank-vacancy-fresh-graduates-2023

@leyumerga
4.4K viewsedited  18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 13:14:32 #EOTC

ጾመ ነነዌን ምእመናን ጥቁር ልብስን ብቻ በመልበስ በጸሎትና በምሕላ እንዲጾሙ  ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ!

ሙሉ መግለጫው ከታች ቀርቧል!

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን! ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የጾምና የምሕላ አዋጅ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

"የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ!
ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።"
       ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮቿን በመጣስ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥር 18 ቀን 2015ዓ.ም. ቃለ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ካለመቻላቸውም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ከመሆኑም በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል፡፡ መንግሥትም ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር ስላልቻለ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል።

በመሆነም ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ጥቁር ልብስ  የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልከት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን፡፡"

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ጥር 26 ቀን 2015ዓ.ም. አዲስ አበባ
   

@leyumerga
2.1K viewsedited  10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 12:42:51
#MOE

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ዛሬ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ያበቃል።

@leyumerga
2.2K viewsedited  09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 19:11:55
" ተፈታኞች የቅሬታቸውን ምላሽ ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት እንደሚያበቃ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

አገልግሎቱ ፤ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያው ቀን ነገ 11:30 እንደሚያበቃ አውቀው በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አለን የሚሉትን ቅሬታ እንዲያቀርቡ መልዕክት አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ፤ ቀድመው ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የቅሬታቸውን መልስ www.neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ቅሬታዎች ሁሉም ተጣርተው ሲጠናቀቁ በቀጣይ ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጾ የቅሬታ ምላሽ ያልደረሳቸው ተፈታኞች በትዕግስት እንዲትጠባበቁ አሳስቧል።

በተጨማሪ ባልተሟላ ወይም በተሳሳተ ወይም በሌላ ሰው መለያ ቁጥር ያመለከቱ የስም ዝርዝራቸው ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ አድራሻ ላይ እንደሚያሳውቅ የገለፀው አገልግሎቱ ተፈታኞች ቅሬታቸውን በድጋሚ በተስተካከለ መለያ ቁጥራቸው ማመልከት እንደሚችሉ ገልጿል።

@leyumerga
1.5K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ