Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @leyumerga
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.90K
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2023-01-25 16:13:03
★ አዋሽ ባንክ አዲስ የስራ ማስታወቂያ
[ 66 ክፍት ቦታዎች]

Deadline: February 01, 2023

Awash Bank invites competent and qualified candidates for the Positions.

Qualification: Accounting, Business Administration, Banking, Finance, Marketing, , Management & Economics, Business and other related fields.

Required: 66 Positions

Term of Employment: Permanent

How to Apply Online??

https://abyssinajob24.com/awash-bank-vacancy-2923

share to your friends

@leyumerga
7.8K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 13:59:05
አቶ በረከት ስምዖን ከእስር ተለቀቁ

ላለፉት ዓመታት በባህር ዳር ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የቆዩት አቶ በረከት ስምዖን ዛሬ ማለዳ ከእስር መፈታታቸው ታውቋል።

አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጵያ ፖለቲካ በተለይ በኢህአዴግ ዘመን ጉምቱ ፖለቲከኞች ከሚባሉት ተርታ የሚመደቡ ሲሆን ለውጥ መጣ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል።

አቶ በረከት ስምዖን ለአራት ዓመታት በእስር ላይ እንደቆዩም የአዲስ ዘይቤ ዘገባ ያመለክታል። ፖለቲከኛው ከእስር በፊት በኢትዮጵያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸውም አይዘነጋም፡፡

@leyumerga
7.2K viewsedited  10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 23:47:31
የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በነገው ዕለት ይጀመራል

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በነገው ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በሚደረግ ሥርዓተ ጸሎት እንደሚጀመር ተገለጸ።

በወሊሶ አካባቢ በብፁዕ አባ ሳዊሮስ መሪነት በተፈፀመው ኢ-ቀኖናዊ "የኤጲስ ቆጶሳት" ሢመትን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባደረጉት አስቸኳይ ጥሪ መሠረት፤ ከእሁድ ጥር 14 ቀን 2015 ጀምሮ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት የሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ወደ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እየገቡ ይገኛሉ።

በዚህም መሰረት፤ የቅዱስ ሲኖዶሱ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በነገው ዕለት አመሻሽ ላይ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በሚደረግ ሥርዓተ ጸሎት የሚጀመር መሆኑን ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

በርካታ አህጉረ ስብከት የተፈፀመውን የቀኖና ጥሰት አስመልክቶ እንደማይቀበሉት እየገለጹ የሚገኙ ሲሆን፤ መላው ኦርቶዶክሳውያንም በአሁኑ ሰዓት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

በሕገ ወጥ መንገድ "ኤጲስ ቆጶሳት" ተብለው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመውረር የተላኩት መነኮሳት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ሆቴሎች በመዘዋወር እየኖሩ እንደሚገኙም ለማረጋገጥ መቻሉን የተ.ሚ.ማ መረጃ አመላክቷል።
   

@leyumerga
7.4K views20:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 10:27:57
Fully Funded Turkey Burslari Scholarship

Course Level: Bachelors, Master & PhD
Financial Support: Fully Funded
Institute: Turkish Universities
Host Country: Turkey
Deadline: February 20/2023

How to Apply Online
https://abyssinajob24.com/fully-funded-turkey-burslari-scholarship

share to your friends
@leyumerga
729 viewsedited  07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 00:18:56
እንኳን አደረሳችሁ!!! በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር ፣ የበረከት እና የስርየት ሃጢያት ይሁንላችሁ!
286 views21:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 12:15:58
በወረኢሉ ከ2 ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ በከርሰምድር እንደሚገኝ በጥናት መታወቁ ተገለጸ

በአማራ ክልል የአባይ ተፋሰስ አካል በሆነው ወረኢሉ በተደረገ የነዳጅ ፍለጋ ጥናት ከ2 ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ በከርሰምድር እንደሚገኝ በጥናት መታወቁን ኢንጅነር ታከለ ኡማ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

ወረኢሉ አካባቢ ከዚህ ቀደም አንድ ኩባንያ የፍለጋ ስራ እያከናወነ የነበረ ቢሆንም በአቅም እጥረት ምክንያት ስራውን ለማቋረጥ መገደዱን የማዕድን ሚኒሰትሩ ኢ/ር ታከለ የገለጹ ሲሆን ይህንን ጨምሮ በኢትዮጵያ አራት ተፋሰሶች ላይ የነዳጅ ፍለጋ ጥናት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

አሁን መንግስት የነዳጅ ሀብቱ በአፋጣኝ ጥቅም ላይ የሚውልበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ እንደሚገኝ ኢ/ር ታከለ ኡማ በጹሑፉቸው ገልጸዋል።

@leyumerga
1.3K viewsedited  09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 11:48:55
በ ዛሬው እለት በመላው አዲስ አበባ ት/ቤቶች ዝግ ሆነው ይውላሉ።

በ ዛሬው እለት በሚከበረው የከተራ በዓል ምክንያት መንገዶች ስለሚዘጉ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ትምህርት የማይኖር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
1.4K viewsedited  08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 15:31:55
ጠ/ ሚ ዐቢይ በአቡ ዳቢ በግንባታ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአቡ ዳቢ በግንባታ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎብኝተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ዛሬ በአቡዳቢ በመሠራት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎብኝቻለሁ ብለዋል።

ለመስሪያ ቦታም 17 ሺህ 682 ካሬ ሜትር መሬት ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች መንግሥት የተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ለዚህም በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም ምስጋና ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ለጊዜው መገልገያ የሚሆነው ቤተ ክርስቲያን እየተጠናቀቀ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የጥምቀት በዓል በቦታው እንዲከበር የሚቻለው ሁሉ እንደሚደረግ ከሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ቃል መገባቱንም አስረድተዋል፡፡“ይሄንን መሰል ቦታዎች የታሪክና የዲፕሎማሲያችን ትእምርቶች ናቸው፤ እነርሱ ለእኛ ይሄንን ሲያደርጉ፣ እኛ ለገዛ ወገኖቻችን ከዚህ በላይ እንድናደርግ ትምህርት ይሆነናል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

@leyumerga
1.3K viewsedited  12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 09:07:06
★ የገቢዎች ሚኒስቴር አዲስ የስራ ማስታወቂያ በ0 አመት እና በልምድ

Deadline: Jan 21, 2023

Ethiopian Ministry of Revenue invites fresh and qualified applicants for the following Professions.

Professions: accounting, banking, business administration, computer engineering, computer science, cooperative accounting, economics, electrical engineering, finance management, information science, information technology, management, office administration, public administration, public finance management, secretary, software engineering and more…

ሙሉ የስራውን ዝርዝር መረጃ ለማየት ከስር ሊንኩን ይጠቀሙ

https://abyssinajob24.com/minster-of-revenue-fresh-graduates

share to your friends
https://t.me/leyumerga
2.3K viewsedited  06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 21:39:55
ሊዮኔል ሜሲ በኢትዮጵያ አይነ-ስውራንን ለመደገፍ የሚደረገውን ዘመቻ ተቀላቀለ

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በኢትዮጵያ የሚገኙ አይነ-ስውራን ዜጎችን  ለመደገፍ የሚደረገውን ዘመቻ መቀላቀሉን አስታውቋል፡፡ሜሲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት÷ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አይነ ስውራን  ዜጎችን  ለመደገፍ ከኦርካም ቴክኖሎጂጋር በትብብር ለመስራት በመስማማቴ ክብር ይሰማኛል ብሏል፡፡

የኦርካም ቴክኖሎጂ በሺህዎች የሚቆጠሩ አይነ ስውራንን ሕይወት እያሻሻለ መሆኑን ያነሳው ሜሲ ቴክኖሎጂው አይነ ስውራን ህልሞቻቸውን እንዲያሳኩ ይረዳቸዋል ብሏል፡፡የቀዳማዊ እመቤት ጽህፈት ቤት በቅርቡ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነ ኦርካም ማይ አይ የተሰኘ አይነ ስውራንን የሚያግዝ መነጽር ለ2 ሺህ አይነ ስውራን ማስረከቡ ይታወሳል፡፡

ይህ ዘመናዊ መርጃ መሳሪያ አማርኛም ሆነ እንግሊዝኛ ያነባል፤ የገንዘብ ኖቶችን ይነግራል፤ ቀለም ይለያል ከፊት ለፊት ምን እንዳለ እና ማን እንደመጣ መዝግቦ በመያዝ መረጃ ይሰጣል፡፡ኦርካም አይነ ስውራን በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ታግዘው የተሻለ ህሕወት እንዲመሩ ለማድረግ የራሱን አስተዋጽኦ የሚያበረክት ተቋም ነው፡፡
https://t.me/leyumerga
1.1K viewsedited  18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ