Get Mystery Box with random crypto!

በወረኢሉ ከ2 ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ በከርሰምድር እንደሚገኝ በጥናት መታወቁ ተገለጸ | ልዩ መረጃ ®

በወረኢሉ ከ2 ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ በከርሰምድር እንደሚገኝ በጥናት መታወቁ ተገለጸ

በአማራ ክልል የአባይ ተፋሰስ አካል በሆነው ወረኢሉ በተደረገ የነዳጅ ፍለጋ ጥናት ከ2 ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ በከርሰምድር እንደሚገኝ በጥናት መታወቁን ኢንጅነር ታከለ ኡማ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

ወረኢሉ አካባቢ ከዚህ ቀደም አንድ ኩባንያ የፍለጋ ስራ እያከናወነ የነበረ ቢሆንም በአቅም እጥረት ምክንያት ስራውን ለማቋረጥ መገደዱን የማዕድን ሚኒሰትሩ ኢ/ር ታከለ የገለጹ ሲሆን ይህንን ጨምሮ በኢትዮጵያ አራት ተፋሰሶች ላይ የነዳጅ ፍለጋ ጥናት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

አሁን መንግስት የነዳጅ ሀብቱ በአፋጣኝ ጥቅም ላይ የሚውልበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ እንደሚገኝ ኢ/ር ታከለ ኡማ በጹሑፉቸው ገልጸዋል።

@leyumerga