Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @leyumerga
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.90K
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-03-08 17:05:52
በነፃ ተሰናብቷል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ችሎት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን በነፃ አሰናብቷል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰበት የሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ወንጀል ነው ፍርድ ቤት በነጻ ያሰናበተው።

የችሎቱን ፍርድ በንባብ ያሰሙት ዳኛ " ተከሳሹ የቀረበበትን ወንጀል በመከላከሉ በነጻ ሊሰናበት ይገባል በማለት በሙሉ ድምጽ ፍርድ ሰጥተናል " ማለታቸውን ' ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ' አስነብቧል።
1.6K viewsedited  14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 11:33:08
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ አደረገ።

በአየር መንገዱ የዓለም የሴቶች ቀን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እና የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ በተገኙበት ተከብሯል።

አየርመንገዱ ወደ ዛንዚባር የሚያደረገውን በረራ ከዋና አብራሪዋ ጀምሮ ረዳት አብራሪ፣ የበረራ አስተናጋጆች እና ቴክኒሽያኖች ሴቶች ናቸው።

ከዚህም ባለፈ የአየር ትራፊክ፣ የበረራ ደህነነትና የጭነት ቁጥጥር፣ የበረራ መለኪያ እስከ አውሮፕላኑ መነሻ ድረስ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የተመራ ነው።

ይህ ሴቶች ያላቸው አቅም ሳይገደብ ማህበረሰብን ማነፅ የሚችል አቅም እንዳላቸው ማረጋገጫ መሆኑን የአየርመንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

የአለም የሴቶች ቀንን በማስመልከት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ በሴቶች የተመሩ በረራዎችን ሲያደርግ ይህ ለ7ኛ ጊዜ ሲሆን በረራው የአየርመንገዱ የመጀመሪያ ሴት አብራሪ በሆኑት ካፒቴን አምሳል ጓሉ የተመራ ነው።
2.1K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 14:24:09 #EOTC

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አባቶች ጋር በወቅታዊ የቤተክርስትያን ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተገልጿል።

በዚህም ውይይት ወቅት ችግሮችን ለመፍታት ቃል የገቡ ቢሆንም አሁንም ችግሮች አልተፈቱም ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ያቋቋመችው የሕግ ኮሚቴ አባል የሆኑት የሕግ ባለሙያና ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለአዲስ ማለዳ የሰጡት ቃል ፦

" ፕሬዝዳንቱ በቤተክርስያን ጉዳይ የታሰሩ ሰዎች እስከ ዛሬ ማክሰኞ ድረስ ይፈታሉ ብለው ቃል የገቡ ቢሆንም፣ ሽንገላ የሚመስል ነገር እየተከናወነ ነው።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥትና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሕግን የማስፈጸም ግዴታ እያለባቸው ያለባቸውን ኃላፊነት ባለመወጣታቸው ምክንያት አሁንም በርካታ የሕግ ጥሰቶችና የንብረት ውድመቶች እየደረሱ ነው።

ትናንት ሰኞ በፍርድ ቤት እግድ የተጣለባቸውና ከቤተክርስትያኗ ቀኖና ውጭ የተሾሙ ግለሰቦች በአሰላ የአቡነ ያሬድ መንበረ ጵጵስናን ሰብረው የገቡ ሲሆን፣ ይህም በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ድጋፍ የሚደረግ ሕገ-ወጥ ድርጊት ነው።

ሻሸመኔና አርሲ ነገሌን ጨምሮ በበርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች አሁንም በርካታ ካህናትና ምዕመናን ያለምንም ጥፋት ታስረው ይገኛሉ።

ከዚህ በፊትም በመንግሥት በሁለት ቀን ውስጥ ይፈታሉ ተብለው የነበሩ ታሳሪዎች ሳይፈቱ በርካታ ቀናት ተቆጥረዋል።

ይህንንም ተከትሎ መንግሥት ራሱ ለገባው ቃል ተገዢ እየሆነ አይደለም። በዚህም ምክንያት ካህናትና ምዕመናን ለበርካታ ችግሮች ተጋልጠዋል ቤተክርስትያኗም ጉዳት እየደረሰባት ይገኛል።

ቤተክርሰትያኗ ከመንግስት ጋር የደረሰችው ስምምነት በመንግሥት በኩል  ሊደረግ ታስቦ የነበረውን ሰልፍ የማስቀረት ጉዳይ ብቻ ተደርጎ መታየት የለበትም።

አሁን ባለው ሁኔታ ችግሩ እየከፋ ነው እየሄደ ያለው።

ምዕመናኑ ምንም እንኳን በሚፈጸሙ ድርጊቶች ያዘኑ ቢሆንም የቤተክርስትያን አባቶችን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

መንግስት የገባውን ቃል አልመፈጸሙ፣ በሕግ እንዲያስፈጽም የተሰጠውን ኃላፊነት አለመወጣቱና የያዘው አካሄድ ሕዝብና አገርን ዋጋ የሚያስከፍል ነው።

ለዚህም እስከ ዛሬ ማክሰኞ ድረስ ሁሉንም ጉዳዮችና የሕግ ጥሰቶች ለማስተካከል በኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ሽመልስ አብዲሳ የተገባው ቃል እንዲፈጸም እንጠይቃለን።

የቤተክርስትያን ጉዳይ ወደ ከፋ ነገር ሳያመራ መንግስት ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል። "

በሌላ በኩል ፤ በአዋሽ ሰባት ከታሰሩ ወጣቶች መካከል ከ300 በላይ የሚሆኑት መለቀቃቸው የተሰማ ሲሆን ወጣቶቹ ብጹአን አባቶች በቦታው ሊያደርጉት የታሰበው ጉብኝት መሰማቱን ተከትሎ መፈታታቸው ተነግሯል፡፡

ይሁንና አሁንም ድረስ በቦታው ታስረው የሚገኙ ወጣቶች እንዳሉ የታወቀ ሲሆን፣ ከሰላሳ የማይበልጡት ታሳሪዎች እንዲፈቱ ጊዜያዊ የሕግ ኮሚቴው እየሰራ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

(አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)
1.7K views11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 11:39:45
የአማራ ክልል ምክርቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ ይጀመራል

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት 6ኛው ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባዔውን በነገው እለት ይጀምራል፡፡

ምክርቤቱ በ5ኛ መደበኛ ጉባዔው የክልሉን የሴክተር መሥሪያ ቤቶች እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ይመክራል። መረጃው የአማራ ኮሙኒኬሽን ነው።
1.9K viewsedited  08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 08:48:05 የTPLF እና TDF ፍጥጫ

የትግራይ ሕዝብ ዛሬም ካለፉት ችግሮች አዙሪት እንዳይወጣ የተማማሉ በሚመስሉ አካላት አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ ያለ ይመስላል፡፡ ከሰሞኑ ከክልሉ የሚሰራጩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በክልሉ ከሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በተያያዘ በቲፒኤልኤፍ/ ህወሓት እና በቲዲኤፍ መካከል ያለው ውዝግብ እያደገ መጥቷል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዙሪያ ያላቸውን ተቃውሞ በማስተጋባት ላይ ይገኛሉ፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ከምንጮቼ አገኘሁት ብሎ ባወጣው ዘገባ አንድ የክልል ፕሬዝዳንት፣ ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶችና በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ አራት የዘርፍ አመራሮች የሚኖሩት ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ይቋቋማል፡፡ ጊዜያዊ አስተዳደሩ 17 የቢሮ ኃላፊዎችን ጨምሮ በጠቅላላው 28 አባላት ያሉት ካቢኔ እንደሚኖረው ዘገባው ጠቅሷል። 50 በመቶው የካቢኔ አባላትና የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ክህወሓት እንዲሁም ሁለቱ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ደግሞ ከትግራይ ታጣቂ ኃይሎችና ከሲቪል ማኅበራት እንዲመረጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል ተብሏል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች 21 በመቶ የካቢኔ ድርሻ ይኖራቸዋል መባሉን ዜና ምንጩ አመልክቷል።

ይህ አካታች አይደለም ተብሎ ትችት ሲሰነዘርበት የነበረው የጊዜያዊ አስተዳደር መዋቅር በፌዴራል መንግሥትና በህወሓት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት ይቋቋማል የተባለው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳልሆነ በድርድሩ የተሳተፉት አቶ ጌታቸው ረዳ መናገራቸውን ቢቢሲ አማርኛ  የዘገበ በሆንም፤ በክልሉ የሚታየውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መረጃ ያላቸው አካላት ግን በህወሓት፣ ቲዲኤፍ/TDF በሚባለው ወታደራዊ ክንፍና በክልሉ በሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ያለው ልዩነትና ሽኩቻ እያደረገ መምጣቱን ይጠቁማሉ።

ትግራይን እንወክላለን በሚሉት አካላት መካከል የተፈጠረው  አለመግባባትና ሽኩቻ ስልጣን ለመያዝ ካለ ፍላጎት የመነጨ ነው የሚሉት ምንጮች፤ የትግራይ ሕዝብ በእነዚህ ኃይሎች በሚደረግ እሰጣ ግባ በድጋሚ ተጎጂ እንዳይሆን ጉዳዩን በጥንቃቄ መመልክ እንደሚገባ መክረዋል፡፡
2.0K views05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 22:36:28 የሳውዲ አረቢያ መንግስት ከ13 ሽህ በላይ ለሚሆኑ የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል መፍቀዱን የዞኑ ስራና ስልጠና መምሪያ ገለጸ፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ ሐላፊ አቶ ፀሐይ ቦጋለ እንደተናገሩት ሀገራችን ከውጭ ሀገራት ጋር ያላት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ለ 13 ሽህ 78 የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ እድል ፈቅዷል፡፡

የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት እድሉ በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ስራ ፈላጊዎች ተከፋፍሎ የተሰጠ ነው ያሉት አቶ ፀሐይ ምዝገባው ከየካቲት 27/2015 እስከ መጋቢት 3/2015 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የእድሉ ተጠቃሚ ስራ ፈላጊዎች ለ20 ቀናት አጫጭር ስልጠናዎችን በኮሌጆች ከወሰዱ በኋላ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናውን ያለፉት መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ሳውዲ አረቢያ በረራ ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

የእድሉ ተጠቃሚ ዜጎች ሴቶች ሲሆኑ ሙሉ ጤነኛና መልካም ስነምግባር ያላቸውን ስራ ፈላጎዎች ሁሉ በወቅቱ በመመዝገብ ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባ ሓላፊው አሳስበዋል፡፡

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ከሀገራችን ጋር ካላት ጠንካራ ዲፕሎማሲ አኳያ በሀገር ደረጃ ለ500 ሽህ እንዲሁም በክልላችን ደግሞ ከ150 ሽህ በላይ ስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ እድሉን እንደፈቀደ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
2.3K views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 22:19:45
ከባድ አደጋ

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ወደአርባ የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች አውራ ጎዳና ላይ ተጋጭተው በርካታ ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተዘገበ፡፡
2.3K views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 21:53:11 በኢትዮጵያ አሁን ያለው አሰራር ከቀጠለ፤ ሁሉም የገጠር ከተሞች ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ ብቻ 20 ዓመት ያስፈልጋል ተባለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሁን ባለው አሰራር የሚቀጥል ከሆነ፤ ሁሉም የገጠር ከተሞች ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ 20 ዓመት እንደሚፈጅበት ገለጸ። መንግስታዊው ተቋም በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ለመተግበር የያዘውን ስትራቴጂክ እቅድ ለማስፈጸም ከሚያስፈልገው 2.76 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ፤ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን በ“ጉድለት” (deficit) የተመዘገበ መሆኑን አስታውቋል።

ባለፈው ዓመት በተቋቋመው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር የሚገኘው ይህ የልማት ድርጅት፤ የኤሌክትሪክ ኃይል በጅምላ ገዝቶ ለደንበኞች የመሸጥ ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም ነው። ተቋሙ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ መስመሮችንም ያስተዳድራል። ይህ  መንግስታዊ ድርጅት ከዘንድሮ ዓመት ጀምሮ እየተገበረው በሚገኘው ስትራቴጂክ እቅድ፤ የኤሌክትሪክ ስርጭት መሰረተ ልማት ሽፋንን ለመጨመር፣ ያረጁ መሰረተ ልማቶችን ለመጠገን እና የፋይናንስ አቅሙን ለማሳደግ ወጥኗል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በስትራቴጂክ እቅዱ የመጨረሻ ዓመት በሆነው በ2017፤ የደንበኞቹን ቁጥር አሁን ካለበት 4.5 ሚሊዮን ወደ 7.9 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱንም አስታውቋል። ተቋሙ ይህን ያስታወቀው፤ የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱን አስመልክቶ ዛሬ ሰኞ የካቲት 27፤ 2015  ከ“ቁልፍ ደንበኞች” ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያለበት የፋይናንስ ውስንነት፤ በ2022 ዓ.ም በሀገሪቱ ሙሉ ለሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ የተያዘውን እቅድ ጥያቄ ውስጥ እንደከተተውም በዛሬው ውይይት ላይ ተነስቷል። ባለፉት 12 ዓመታት በአማካይ 423 ከተሞች በየዓመቱ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ መደረጉን የጠቀሱት የተቋሙ የለውጥ እና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ እሱባለው ጤናው፤ በዚህ አካሄድ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ኤሌክትሪክ ለማዳረስ 20 ዓመት እንደሚፈጅ ተናግረዋል። 

via Ethiopiainsider
2.3K views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 20:36:01
ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት በመንገድ ላይ የዘረፋ ወንጀል ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደቡብ ክልል በደራሼ ልዩ ወረዳ ሆልቴ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ከፌደራል ፖሊስ  በክህደት ተቋሙን ለቀዋል የተባሉ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ተሽከርካሪ በኃይል በማስቆም ፈፅመውታል በተባለ ዘረፋና፤ የዘረፋ ወንጀል ሙከራ ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ፖሊስ አስታዉቋል።

ከአርባምንጭ ወደ ኮንሶ የሚወስደዉ አዉራጎዳና ድንጋይ ደርድረዉ በመዝጋት ተሽከርካሪ በማስቆም በተደጋጋሚ በተፈፀሙ ዘረፋዎችና የዘረፋ ሙከራ ወንጀል ሁለቱ የፖሊስ አባላት እጃቸዉ እንዳለበት ከህብረተሰቡ ለልዩ ወረዳዉ ፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ መነሻ ተጠርጣሪዎች የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በፖሊስ መያዛቸዉ ነዉ የተነገረዉ።

ፖሊስ በአካባቢያዊ ማስረጃ ተመርኩዞ የያዛቸዉ ሁለቱ የቀድሞ ፖሊስ አባላት ላይ በአፋጣኝ ምርመራ አጣርቶ ለህግ በማቅረብ የቅጣት ዉሳኔ ሊያሰጥ የሚችል ፖሊሳዊ ስራ አየሰራ መሆኑን ከደቡብ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል
2.7K viewsedited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 13:09:02
"የአማራን ሕዝብ የመብት፣የማንነትና ወሰን ጉዳዮችን ለማስከበር ኢትዮጵያዊነት መሰባሰቢያ ጥላችን ነው።ወቅታዊ የፖለቲካ ችግሮቻችን ቅቡልነት ያለው የሀገረ መንግሥት ምስረታ ሥራችን ካለመጠናቀቁ የመነጩ ናቸው"
ር/መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)


@leyumerga
961 viewsedited  10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ