Get Mystery Box with random crypto!

የTPLF እና TDF ፍጥጫ የትግራይ ሕዝብ ዛሬም ካለፉት ችግሮች አዙሪት እንዳይወጣ የተማማሉ በ | ልዩ መረጃ ®

የTPLF እና TDF ፍጥጫ

የትግራይ ሕዝብ ዛሬም ካለፉት ችግሮች አዙሪት እንዳይወጣ የተማማሉ በሚመስሉ አካላት አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ ያለ ይመስላል፡፡ ከሰሞኑ ከክልሉ የሚሰራጩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በክልሉ ከሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በተያያዘ በቲፒኤልኤፍ/ ህወሓት እና በቲዲኤፍ መካከል ያለው ውዝግብ እያደገ መጥቷል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዙሪያ ያላቸውን ተቃውሞ በማስተጋባት ላይ ይገኛሉ፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ከምንጮቼ አገኘሁት ብሎ ባወጣው ዘገባ አንድ የክልል ፕሬዝዳንት፣ ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶችና በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ አራት የዘርፍ አመራሮች የሚኖሩት ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ይቋቋማል፡፡ ጊዜያዊ አስተዳደሩ 17 የቢሮ ኃላፊዎችን ጨምሮ በጠቅላላው 28 አባላት ያሉት ካቢኔ እንደሚኖረው ዘገባው ጠቅሷል። 50 በመቶው የካቢኔ አባላትና የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ክህወሓት እንዲሁም ሁለቱ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ደግሞ ከትግራይ ታጣቂ ኃይሎችና ከሲቪል ማኅበራት እንዲመረጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል ተብሏል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች 21 በመቶ የካቢኔ ድርሻ ይኖራቸዋል መባሉን ዜና ምንጩ አመልክቷል።

ይህ አካታች አይደለም ተብሎ ትችት ሲሰነዘርበት የነበረው የጊዜያዊ አስተዳደር መዋቅር በፌዴራል መንግሥትና በህወሓት መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት ይቋቋማል የተባለው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳልሆነ በድርድሩ የተሳተፉት አቶ ጌታቸው ረዳ መናገራቸውን ቢቢሲ አማርኛ  የዘገበ በሆንም፤ በክልሉ የሚታየውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መረጃ ያላቸው አካላት ግን በህወሓት፣ ቲዲኤፍ/TDF በሚባለው ወታደራዊ ክንፍና በክልሉ በሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ያለው ልዩነትና ሽኩቻ እያደረገ መምጣቱን ይጠቁማሉ።

ትግራይን እንወክላለን በሚሉት አካላት መካከል የተፈጠረው  አለመግባባትና ሽኩቻ ስልጣን ለመያዝ ካለ ፍላጎት የመነጨ ነው የሚሉት ምንጮች፤ የትግራይ ሕዝብ በእነዚህ ኃይሎች በሚደረግ እሰጣ ግባ በድጋሚ ተጎጂ እንዳይሆን ጉዳዩን በጥንቃቄ መመልክ እንደሚገባ መክረዋል፡፡