Get Mystery Box with random crypto!

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ከ13 ሽህ በላይ ለሚሆኑ የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል | ልዩ መረጃ ®

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ከ13 ሽህ በላይ ለሚሆኑ የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራ ፈላጊዎች የስራ እድል መፍቀዱን የዞኑ ስራና ስልጠና መምሪያ ገለጸ፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ ሐላፊ አቶ ፀሐይ ቦጋለ እንደተናገሩት ሀገራችን ከውጭ ሀገራት ጋር ያላት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ለ 13 ሽህ 78 የምስራቅ ጎጃም ዞን ስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ እድል ፈቅዷል፡፡

የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት እድሉ በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ስራ ፈላጊዎች ተከፋፍሎ የተሰጠ ነው ያሉት አቶ ፀሐይ ምዝገባው ከየካቲት 27/2015 እስከ መጋቢት 3/2015 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን የእድሉ ተጠቃሚ ስራ ፈላጊዎች ለ20 ቀናት አጫጭር ስልጠናዎችን በኮሌጆች ከወሰዱ በኋላ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናውን ያለፉት መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ሳውዲ አረቢያ በረራ ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

የእድሉ ተጠቃሚ ዜጎች ሴቶች ሲሆኑ ሙሉ ጤነኛና መልካም ስነምግባር ያላቸውን ስራ ፈላጎዎች ሁሉ በወቅቱ በመመዝገብ ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባ ሓላፊው አሳስበዋል፡፡

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ከሀገራችን ጋር ካላት ጠንካራ ዲፕሎማሲ አኳያ በሀገር ደረጃ ለ500 ሽህ እንዲሁም በክልላችን ደግሞ ከ150 ሽህ በላይ ስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ እድሉን እንደፈቀደ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡