Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ አደረገ። በ | ልዩ መረጃ ®

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ አደረገ።

በአየር መንገዱ የዓለም የሴቶች ቀን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እና የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄ በተገኙበት ተከብሯል።

አየርመንገዱ ወደ ዛንዚባር የሚያደረገውን በረራ ከዋና አብራሪዋ ጀምሮ ረዳት አብራሪ፣ የበረራ አስተናጋጆች እና ቴክኒሽያኖች ሴቶች ናቸው።

ከዚህም ባለፈ የአየር ትራፊክ፣ የበረራ ደህነነትና የጭነት ቁጥጥር፣ የበረራ መለኪያ እስከ አውሮፕላኑ መነሻ ድረስ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የተመራ ነው።

ይህ ሴቶች ያላቸው አቅም ሳይገደብ ማህበረሰብን ማነፅ የሚችል አቅም እንዳላቸው ማረጋገጫ መሆኑን የአየርመንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

የአለም የሴቶች ቀንን በማስመልከት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ በሴቶች የተመሩ በረራዎችን ሲያደርግ ይህ ለ7ኛ ጊዜ ሲሆን በረራው የአየርመንገዱ የመጀመሪያ ሴት አብራሪ በሆኑት ካፒቴን አምሳል ጓሉ የተመራ ነው።