Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ መረጃ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyumerga — ልዩ መረጃ ®
የሰርጥ አድራሻ: @leyumerga
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 50.90K
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-03 15:49:20
ታሪኩ እንዲነው
ልጁ ከዋሻው ስር እባብ እንዳለ አላወቀም፤ሴቷ ደግሞ ልጁ ላይ የተጫነው ከባድ ድንጋይ እንዳለ አታውቅም
ሴቷ እንዲህ አሰበች.....
340 views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 15:28:04
የ2015 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆኗል።

በዚህ አመት የተዘጋጀው መቁረጨ ነጥብ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሰላ በመሆኑ የሚያገለግለው ለ2015 ዓ.ም የስልጠና ዘመን ብቻ መሆኑን ተገልጿል።

በ2013/2014 የሥልጠና ዘመን በተለየየ ምክንያት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ያልገቡ ተማሪዎች የሚስተናገዱት በ2014 ዓ.ም በነበረው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ይሆናል ተብሏል።

(የ2015 ዓ/ም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ከላይ ተያይዟል)

ምንጭ፦ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር

@leyumerga
187 views12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 08:42:25 አስቸኳይ ክፍት የ ስራ ማስታወቂያ

ቀን 25/05/2015 የወጣ

Ethio Job Consultancy

የስራ መደብ ፡ #N.G.O በማንኛዉም
★የት ደረጃ ፡ any degree /diploma
★የስራ ልምድ ፡ 0 አመት
★ደሞዝ ፡  10000 - 15,000

የስራ መደብ:- #ሁለገብ
★የት/ት ደረጃ :- 12
★ደሞዝ: 5500
★ፆታ :- ወንድ
★የስራ ልምድ: 0 አመት

የስራ መደብ ፡ out door sales
★የት ደረጃ : 10 +
★የስራ ልምድ ፡ 0 አመት
★ፆታ:ሴት 
★ደሞዝ ፡ በስምምነት

የ ስራ መደብ: Management
★የትምህርት ደረጃ :diploma/degree
★ደሞዝ : በስምምነት
★ፆታ: Female
★ብዛት: 3

የ ስራ መደብ ፡ #ሴልስ ጫማ ቤት ላይ
★የት ደረጃ ፡- 12
★የስራ ልምድ ፡- 0 አመት
★ደሞዝ :- በስምምነት + ኮሚሽን
★ፆታ ፦ሴት
★ብዛት:- 4

የስራ መደብ ፡ #Marketing
★የት ደረጃ ፡- degree
★ፃታ:- ሴ/ወ
★የስራ ልምድ ፡- 0_1 አመት
★ደሞዝ ፡- 5000-7000

የስራ መደብ ፡ #Accountant
★የት ደረጃ ፡ Degree
★ፆታ: ሴ/ወ
★የስራ ልምድ ፡ 0 - 1
★ደሞዝ ፡  5000-7000

የስራ መደብ ፡ # IT/IS
★የት/ደረጃ ፡-  degree /dip
★የስራ ልምድ ፡- 0 -2አመት
★ፆታ:- ሴ/ወ
★ደሞዝ:- 5500-7000

የስራ መደብ #መረጃ እና መዝገብ አያያዝ
★የት ደረጃ ፡ዲፕ/ ዲግሪ
★የስራ ልምድ ፡ 0 አመት
★ደሞዝ ፡ በስምምነት
★የስራ ቦታ ፡ አ አ

የስራ መደብ፦#ሲቪል ኢንጂነር
★የት/ደረጃ፦ዲግሪ
★ደሞዝ:- በስምምነት
★ፆታ፦ወ/ሴ

የስራ መደብ፦#ካሸር ለቤቲንግ ቤት
★የት/ደረጃ፦10+
★የስራ ልምድ:-0 አመት
★ደሞዝ:- በስምምነት
★ፆታ፦ሴት
★ብዛት:- 15

የስራ መደብ፦ትኬተር
★የት/ደረጃ፦  diploma
★የስራ ልምድ: 0 አመት
★ደሞዝ:- በስምምነት
★ፆታ፦ሴት

የስራ መደብ፦NGO መዝገብ ቤት
★የት/ደረጃ፦በማንኛዉም ዲግሪ
★የስራ ልምድ፦ 0
★የ ስራ ቦታ፦  አ/አ
★ደሞዝ፦10000
★ብዛት፦15
★ፆታ፦ሴ/ወ

የስራ መደብ #ሴልስ ለ ሱፐርማርኬት
★የት ደረጃ ፡10+
★የስራ ልምድ ፡ 0
★ደሞዝ ፡ በስምምነት
★የስራ ቦታ ፡ ብስራተ ገብርኤል



አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት የት/ት ማስረጃችሁን  በመያዝ to ethio job vacancy ቢሮአችን በአካል መተው ያመልክቱ

tel:0966088808
     0985725012

ethio job vacancy office

አድራሻ ጀሞ 1 ሀውዲ ሞል 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15
894 views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 22:08:32
የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር።


የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website:

https://placement.ethernet.edu.et

SMS: 9444

@leyumerga
2.2K views19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 10:34:29
መልካም ዜና ለ ስራ ፈላጊዎች በ       ሙሉ የትም መሄድ ሳይጠበቅባችሁ በ የ ቀኑ የ ሚወጡ ከ 100 በላይ አዳዲስ የ ስራ ማስታወቂያዎችን ይመልከቱ
1.5K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 14:38:08 በኦሮሚያ ክልል በአዲሱ "ሸገር ከተማ አስተዳደር" በርካታ ነዋሪዎች የክልሉ መንግሥት መኖሪያ ቤታችን "ያለ ማስጠንቀቂያ" እያፈረሰብን ነው ማለታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

በለገጣፎ አካባቢ ቤታቸው እየፈረሰባቸው የሚገኙ ነዋሪዎች፣ ድርጊቱ "የብሄር ማንነትን የለየ" መሆኑን መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

የአዲሱ ሸገር ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፣ አስተዳደሩ እያፈረሰ ያለው የግንባታ ፍቃድ የሌላቸውን ቤቶች" መሆኑን እንደገለጸና ድርጊቱ "ብሄርን የለየ ነው" መባሉን እንዳስተባበለ ዘገባው አመልክቷልል።

@leyumerga
280 viewsedited  11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 14:35:07
የእነ አባ ሳዊሮስ እግድ ተነሳ።

የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ ሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት በሕገ ወጥ መንገድ በተፈጸመው ሹመት ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ላይ እግድ ማስተላለፉ ይታወሳል።

በቅርቡ የተፈጸመውን ዕርቅ ተከትሎ ፦

- የአባ ሳዊሮስ፣
- የአባ ኤዎስጣቴዎስ
- የአባ ዜና ማርቆስ #ዕግድ_መነሳቱን የቤተክርስቲያና መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ቀሪዎቹ 26 ግለሰቦች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳይገቡ የተጣለው ዕግድ እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ተገልጿል።

@leyumerga
303 views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 14:34:28
#ማስታወቂያ

በስመአብ ወወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን መርጌታ ላቀው
የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
እነሆ የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን
  0912468657
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ሀብት
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት

ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል
               እንዲሁም የተለያዩ
      መድኀኒቶችን እንቀምማለን
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
     መድሀኒቱን ባሉበት ቦታ ሰርተን  መላክ እንችላለን
ይደውሉ
ለጥያቄወ 0912468657 ይደውሉልን 
ቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል https://t.me/+mecfU3N6TwNmNTk0
https://t.me/+mecfU3N6TwNmNTk0
288 views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 13:29:08
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሩሲያን ለማዉገዝ በተደረገ ስብሰባ ኢትዮጲያን ጨምሮ 15 የአፍሪካ ሀገራት ድምፀ ተአቅቦ አደረጉ

በትላንትናዉ እለት በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከአንድ አመት ገደማ በፊት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችውን ወረራ የሚያወግዝ ውሳኔን 15 የአፍሪካ ሀገራት ድምፁን ተአቅቦ ሲያደርጉ 28 ሀገራት ደግፈዋል።የውሳኔ ሃሳቡ ወታደሮቹ ከዩክሬን እንዲወጡ እና ጦርነቱ እንዲቆም የሚጠይቅ ነዉ፡፡

መለኪያው በህጋዊ መንገድ አስገዳጅ ሳይሆን ፖለቲካዊ ክብደትን ይይዛል።ዉሳኔዉ በህጋዊ መንገድ አስገዳጅ ሳይሆን ፖለቲካዊ ክብደት ያለዉ ነዉ፡፡በዉሳኔ ላይ በተሰጠዉ ድምጽ 141 የዓለም ሀገራት ሩሲን ሲያወግዙ፣ በ32 ድምፀ ተአቅቦ እና በሰባት ድምጽ ተቃውሞ ቀርቧል።ድምጸ ተአቅቦ ካደረጉ ሀገራት መካከል ግማሽ ያህሉ ከአፍሪካ ናቸዉ፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ፣ አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ ብሩንዲ፣ ናሚቢያ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ጋቦን፣ ጊኒ፣ ሞዛምቢክ፣ ሱዳን፣ ቶጎ፣ ኡጋንዳ እና ዚምባብዌ ድምጽ ተአቅቦ ያደረጉ ሀገራት ናቸዉ፡፡ኤርትራ እና ማሊ ዉሳኔዉን የተቃወሙ ብቸኛ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው።ሴኔጋል፣ቡርኪናፋሶ፣ካሜሩን፣ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ኤስዋቲኒ እና ጊኒ ቢሳው በምርጫው አልተሳተፉም።

ናይጄሪያ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ግብፅ፣ ጋና እና ኬንያ ሩሲያን ከሚያወግዘዉ ድምጸ ዉሳኔዉን ከደገፉት የአፍሪካ ሀገራት መካከል ይገኙበታል።የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የውሳኔ ሃሳቡን በደስታ መቀበላቸዉን በማንሳት ይህም የአለም አቀፍ ድጋፍ ትልቅ ምልክት ነው ብለዋል።

@leyumerga
1.8K views10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 11:52:51
#MoE

106 ሺህ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ የትምህርት ፕሮግራም ተካተዋል
፡፡

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው #ከ50_በመቶ በታች ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለአራት ወራት ያህል በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ይሳተፋሉ፡፡

የ #Remedial ፕሮግራሙ ከአ/አ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ባሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች እና ፕሮፌሰሮች ኮሚቴ በማዋቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉት የትምህርት አይነት ይዘቶችን መለየቱን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራሙ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ እንግሊዘኛ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ሂሳብ የትምህርት አይነቶችን የሚወስዱ ሲሆን፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ እንግሊዘኛ፣ ማህበራዊ ሳይንስና ሂሳብ ትምህርት አይነቶችን እንደሚወስዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ይዘቶቹን መሰረት አድርጎ በተቋማት የሚዘጋጅ (ከ30 በመቶ) እና በማዕከል የሚዘጋጅ (ከ70 በመቶ) የሚያዝ ፈተና በመፈተን በድምሩ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሚያገኙ ተማሪዎች መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል ይችላሉ ብለዋል፡፡ #EPA

@leyumerga
2.0K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ