Get Mystery Box with random crypto!

መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያዎችን አገልግሎት አቋርጧል መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎቶችን በ | ልዩ መረጃ ®

መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያዎችን አገልግሎት አቋርጧል

መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎቶችን በኢትዮጵያ የገደበው፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ችግር ጋር በተገናኘ መሆኑን “ኔት ብሎክስ” የተሰኘ የኢንተርኔት ግንኙነት አጥኚ ድርጅት ይፋ አድርጓል፡፡

አገልግሎቱ የተቋረጠባቸው የማኅበራዊ ሚዲያዎች ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ እና ሜሴንጀር ሲሆኑ፣ አገልገሎቱ መቋረጥ የጀመረው ትናንት ምሽት ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መከፋፈል ምክንያት በጸረ-መንግሥት ተቃውሞ በቀጠለበት ወቅት፣ የማኅበራዊ ሚዲያ እና የመልዕክት መላላኪያ መድረኮች ፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ቲክቶክ እና ቴሌግራም መዘጋታቸውን የኔትወርክ መለኪያዎች ያሳያሉ።

እንደ “ኔት ብሎክስ” ሪፖርት፣ በእነዚህ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መንግሥት የአገልግሎት ዕቀባ የጣለው በመንግሥት በሚተዳደረውና የኢንተርመኔት አገልግሎት አቅራቢ በሆነው በኢትዮ ቴሌኮም በኩል ነው ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ መንግሥት ያቋረጠውን አገልግሎት፣ የመንግሥት የኢንተርኔት ሳንሱር እርምጃዎችና ገደቦችን ማለፍ በሚችሉ ቨርቹዋል ፕራይቬት ኔትዎርክ (ቪፒኤን) አገልግሎቶችን መጠቅም እንደሚቻል ድርጀቱ ጠቁሟል፡፡ አሁን ላይ ብዙዎች ይህንኑ አግልገሎት ተጠቅመው የማኅበራዊ ሚዲያዎችን አገለግሎት እየተጠቀሙ መሆኑን የሚያመላክቱ መረጃዎች አሉ፡፡
https://t.me/proxy?server=cheha-ba-jan-khod-door-az-rokh-janan-khod-kardam.sbs&port=443&secret=7vQ1mpsyX_HR5QhN8OD3U3ttc24uY29t

@leyumerga