Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬው የክልል መንግስታት መግለጫ ! ዛሬ የክልል መንግስታት #ተመሳሳይ_አይነት ይዘት ያላቸው መ | ልዩ መረጃ ®

የዛሬው የክልል መንግስታት መግለጫ !

ዛሬ የክልል መንግስታት #ተመሳሳይ_አይነት ይዘት ያላቸው መግለጫዎችን አውጥተዋል።

እስካሁን ድረስ መግለጫቸውን ለህዝብ ያሰራጩት ፦

- የሶማሌ ክልል
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል
- የደቡብ ክልል
- የሐረሪ ክልል
- የጋምቤላ ክልል መንግስታት
ሲሆኑ በመግለጫቸው " በተገቢው አካል ያልተፈቀደ እና የደህንነት ስጋት የሚፈጥር ሰላማዊ ሰልፍ " የተከለከለ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

የየክልሉ መንግስታት ባወጡት ተመሳሳይ አይነት ይዘት ባለው መግለጫ ፦  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተከሰተው ችግር የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖና መሰረት ባደረገ ውስጠ ደንብ / ውስጣዊ አሰራር ሊፈታ ይገባል የሚል አቋማቸውን ገልጸዋል።

" በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ከሃይማኖት ጉዳይነት አልፎ እየተወሳሰበና በርካታ እኩይ ዓላማ ያላቸው የሀገር ውስጥና የውጭ የፓለቲካ ኃይሎች ተቀናጅተው ኢትዮጵያን ለማዳከም ርብርብ እያደረጉ ናቸው " ያሉት የየክልሉ መንግስታት " ይህንንም በመረጃና በማስረጃ አረጋግጠናል ብለዋል።

በዚህም " ሐይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሀገርና የህዝብ ደህንነትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ማናቸውንም እንቅሳቃሴ እንቃወማለን " ሲሉ ገልጸዋል።

በተገቢው አካል ያልተፈቀደና የደህንነት ስጋት የሚፈጥር የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ማድረግም ተገቢነት ያለው ጉዳይ አይደለም ሲሉም አክለዋል።

የየክልሉ መንግስታት ባወጡት ተመሳሳይ አይነት ይዘት ባለው መግለጫቸው ፤ ህገ መንግስቱንና የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ውሳኔን መሰረት በማድረግ ማንኛውንም ሕገወጥ እንቅስቃሴ በመከላከልና በመቆጣጠር ህግ የማስከበር ኃላፊነታችንን እንወጣለን  ሲሉ አስገንዝበዋል።

@leyumerga