Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ። የኢት | ልዩ መረጃ ®

ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት አስቸኳይ ሰበር መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫውን ባወጣች ፵፰ ሰዓታት ውስጥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት፤ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ባልጣሰ መልኩ ከመንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያየት መንፈሳዊ በሯ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ጥሪ ማስተላለፏን አስታውሷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢፌዳሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይህንን የቤተ ክርስቲያን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይት ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጿል።

በዚህም መሰረት ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ።

#eotc