Get Mystery Box with random crypto!

#MOE ሚኒስቴሩ ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳሰበ የካቲት 2/ | ልዩ መረጃ ®

#MOE

ሚኒስቴሩ ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አሳሰበ

የካቲት 2/2015 (ዋልታ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ከተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ጋር የተወያዩ ሲሆን የመውጫ ፈተና በመጪው ሐምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ ለመሆንም ተማሪዎች በየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን ሴሚስተር ፈተና መውሰድና ኮርሶችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ለፈተናው በሁሉም የትምህርት መስኮች ላይ የተመረጡ ኮርሶች የብቃት ልየታ ተደርጎላቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲያውቁት መደረጉን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በአሁኑ ወቅት የፈተና ንድፈ ማሳያና የፈተና ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች በቀሪዎቹ አምስት ወራት ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሳቸውን ለፈተናው ብቁ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችም ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ሲመለሱ ተማሪዎች ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንቶች መገኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#Walta_tv
@leyumerga