Get Mystery Box with random crypto!

ከፀጥታና ደኅነት  የጋራ ግብረ–ኃይል ወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ሰሞኑን | ልዩ መረጃ ®

ከፀጥታና ደኅነት  የጋራ ግብረ–ኃይል ወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተከሰተውን ወቅታዊ ሁኔታ የገመገመው የፀጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አለመግባባቱን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈጸም የጸና እምነት አለው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋራ ግብረኃይሉ በተለያዩ ሚዲያዎች ከሚሰራጩ ዘገባዎችና በመረጃ ስምሪቱ ባሰባሰባቸው ግብዓቶች መሠረት በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ሕገወጥ የሰልፍ ጥሪ በማድረግ የዜጎች ህይወት የሚቀጠፍበት አጋጣሚ እንዲፈጠር ቅስቀሳዎች እየተደረጉና ሌሎችም ግጭት ቀስቃሽተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

ይህ አካሄድ ክስተቱን እንደ ሽፋን በመጠቀም ከውስጥና ከውጭ ተቀናጅተው ሀገራችንን ለማፍረስለሚሰሩ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በር እየከፈተ መሆኑን መላው የሀገራችን ሕዝብና የዕምነቱ ተከታዮች ግንዛቤ ሊወስዱ እንደሚገባ የጋራ ግብረ-ኃይሉ አመልክቷል።

@leyumerga