Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 39

2023-03-23 11:13:01
የሕወሃት ከሽብርተኝነት መሰረዙ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ሲሉ ዶ/ር ደብረጺዮን ተናገረ

የሕወሃት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካዔል የፌደራሉ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕወሃትን ከአሸባሪነት ፍረጃ ማንሳቱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማዋቀር ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል በማለት መናገራቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ደብረጺዮን፣ በትግራይ ክልል በጀት ዝግጅት እና በእስረኞች ዙሪያ ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ግንኙነት እንደተጀመረ እና አዲስ የሚዋቀረው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እደረጃጀት ለፌደራሉ መንግሥቱ እንደተላከ መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ደብረጺዮን ይህን የተናገሩት፣ ትናንት በመቀሌ ለክልሉ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.9K views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 10:05:55 ጌታቸው ረዳ

የሕወሃት ከፍተኛ አመራር ጌታቸው ረዳ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ሰሞኑን ያነሷቸው ቅሬታዎች በከፍተኛ ትኩረት እንደሚታዩ እና ማጣራት እንደሚደረግባቸው መናገራቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

የጦር ጉዳተኞቹ ለእነሱ ተብሎ የተገዛ የሕክምና አቅርቦት እየተሸጠ ስለመሆኑ ነግረውኛል ያለው ዜና ምንጩ፣፣ የጦር ጉዳተኞቹ የጉዳት ካሳ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውንም ጠቅሷል።

የጦር ጉዳተኞቹ ከፍተኛ የሆነ የምግብ፣ የሕክምናና የንጽሕና መጠበቂያ አቅርቦት እጥረት እንዳለባቸው በሰላማዊ ሰልፍና ከጌታቸው ጋር ባደረጉት ውይይት መናገራቸው ተዘግቦ ነበር።

የጦር ጉዳተኞቹ፣ በመቀሌ አካባቢ ኩዊሃ እና ደጀን ሆስፒታል በተባሉ ሁለት ማገገሚያ ማዕከሎች የሚገኙ ናቸው።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.9K views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 08:38:48 የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን እና ሌሎች ዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች ከሱማሊያ ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ ስደተኞች ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብ 116 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።

ድርጅቶቹ የሰብዓዊ ዕርዳታ ልገሳ ጥሪውን ያቀረቡት፣ በሱማሌላንድ መንግሥት ወታደሮች እና በጎሳ ታጣቂዎች መካከል ከሚካሄደው ግጭት ሸሽየው ወደ ኢትዮጵያው ሱማሌ ክልል ለገቡ ሕጻናትና ሴቶች ለበዙባቸው ስደተኞች ነው።

ከግጭቱ የሸሹ ከ100 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ ሱማሌ ክልል ዶሎ ዞን መግባታቸውን የተመድ መረጃዎች ያመለክታሉ።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.9K views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 07:50:31
ሜሱት ኦዚል ጫማውን ሰቅሏል !

ጀርመናዊው የቀድሞ አርሰናል እና ሪያል ማድሪድ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሜሱት ኦዚል ራሱን ከ እግር ኳስ ማግለሉን ይፋ አድርጓል።

የ 34ዓመቱ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሜሱት ኦዚል በተደጋጋሚ ያጋጠሙት ከባድ ጉዳቶች አስራ ሰባት አመታትን ካሳለፈበት የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ህይወት እንዲርቅ እንዳስገደዱት ተናግሯል።

ሜሱት ኦዚል ባስተላለፈው መልዕክትም " የ ፕሮፌሽናል እግርኳስ ህይወቴን ያሳለፈኩባቸውን ክለቦችን ፣ አሰልጣኞች እና የቡድን አጋሮቼን በጣም አመሰግናለሁ።

በሄድኩበት ክለብ ሁሉ ለእኔ ድጋፍ ለሚያደርጉ አድናቂዎቼ ትልቅ አክብሮት አለኝ ፣ ባለፉት ወራት እና ሳምንታት ያጋጠሙኝ ጉዳቶች ከ እግርኳስ እንድርቅ ይበልጥ ገፋፍተውኛል።"ሲል ተደምጧል።
@Leyu_News
@Leyu_News
1.9K viewsedited  04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 07:19:50
የምድራችን ኃያላኑ ሩሲያና ቻይና መሪዎች “አዲስ የዓለም ስርአት” እንፈጥራለን አሉ፡፡ 

መሪዎቹ ይህን ያሉት የቻይናው መሪ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በሞስኮ በነበራቸው የሁለት ቀናት ጉብኝት በነበረው ዘለግ ያለ ውይይት ላይ ነው፡፡

ጉብኝቱ ትልቅ ትርጉም ያለውና የቻይናው መሪ ዓለም የእስር ማዘዣም ጭምር በማውጣት ጫና ለመፍጠር እየተረባረባበቸው ላሉት የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን ያላቸውን አጋርነት ያሳዩበት እንደሆነ እየተዘገበ ነው፡፡ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር፣ ዓለምን በበላይነት ለመቆጣጠር አሜሪካ የምትደርገው እንደቅስቃሴ ማስቆም እንዲሁም ዩክሬን ጉዳይ መሪዎቹ በነበራቸው ቆይታ ከመከሩባቸው አንኳር ጉዳዮች ናቸው፡፡

"መሪዎቹ ይህ ግንኙነት ከሁለትዮሽ ያለፈና ለዓለም አቀፋዊ ገጽታ እና ለሰው ልጅ የወደፊት ህይወት ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው መክረዋል" ስትል ባወጣቸው መግለጫ ገልጻለች፡፡“ዓለምን በበላይነት ለመቆጣጠር የሚደረገው ሙከራ” አንቀበልም የሚል ጠንካራ የጋራ አቋም ያላቸው መሪዎቹ፤ በቀጣይ “አዲስ የዓለም ስርአት” እንፈጥራለንም ብለዋል፡፡

ፑቲን በበኩላቸው “የተባበሩት መንግስታት ዋና ሚና ፣ የጸጥታው ምክር ቤት፣ ዓለም አቀፍ ህግ እንዲሁም የተመድ ቻርተር አላማ እና መርሆች ላይ የተመሰረተ ይበልጥ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ የሆነ ሁሉን አቀፍ የዓለም ስርአት መፍጠር ላይ በትብብር እየሰራን ነው" ሲሉ መናገራቸው የክሬምሊን ድህረ-ገጽ አስነብቧል፡፡

ቻይና ፕሬዝዳንት ሺ “አሁን በ100 ዓመታት ውስጥ ያልተከሰቱ ለውጦች አሉ። አንድ ላይ ስንሆን እነዚህን ለውጦች እንመራለን” ሲሉ ለፑቲን መናገራቸውም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የቻይናው አቻቻው ሃሳብ የሚጋሩት ፑቲንም “እስማማለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
2.0K views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 22:26:48 ሩሲያ በዩክሬን በርካታ ከተሞች ላይ ጥቃት ፈጸመች

የሩስያ ሃይሎች በኪየቭ ክልል የመኖሪያ አከባቢዎች ላይ በፈጸሙት የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ቢያንስ ሶስት ሰዎች ሲገደሉ በበርካታ የዩክሬን ከተሞች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።በዛሬዉ እለት የመጀመሪያዉ ጥቃት የሁለት የመኖሪያ ሕንፃዎች በዩክሬን ዋና ከተማ ዳርቻ ራሂሽቺቭ ላይ ተሰንዝሯል፡፡

ከተጎጂዎቹ መካከል የ11 አመት ታዳጊ እንደሚገኝ የነፍስ አድን አገልግሎት ገልጿል።በሌላ በኩል ሩሲያን በተቀላቀለችው ክራይሚያ ግዛት የሚገኙ ባለስልጣናት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች መርከቦቻቸውን ማጥቃቱን ተናግረዋል ።

በሴባስቶፖል የወደብ ከተማ ነዋሪዎች ከባድ ፍንዳታ እንደነበር ተናግረዋል፡፡የሩሲያ ከፍተኛ የጦር ባለስልጣን ሚካሂል ራዝቮዛይቭ በጥቁር ባህር መርከቦች ላይ ያነጣጠሩ ሶስት ጥቃቶችን ዩክሬን መፈጸሟንና ንብረት መዉደሙን ገልጸዋል፡፡ የሩሲያ የጦር መርከቦች ላይ ግን ጉዳት እንዳልደረሰ አክለዋ፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንዳሉት ሩሲያ ከ20 በላይ “ገዳይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን” እንዲሁም ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን ተናግረዋል።የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ከሰዓታት በፊት ከሩሲያ መውጣታቸውን በመጥቀስ "በሞስኮ አንድ ሰው 'ሰላም' የሚለውን ቃል ለመስማት በሚሞክርበት ጊዜ በሌላ በኩል ጥቃት እንዲሰነዝር ትዕዛዝ ይሰጥ ነበር" ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
2.2K views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 21:36:53
ሁለቱ አስከሬን ተገኝቷል

ለህንጻ ግንባታ የተቆፈረ አፈር ተንዶ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፋን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታዉ መነን  ሰፈር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ  ለህንጻ ግንባታ መሰረት የተቆፈረ አፈር ተንዶ የሁለት ሰራተኞች ሕይወት ማለፋን የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል።

አደጋው በዛሬው ዕለት ከቀኑ 8:59 ላይ ልዩ ቦታው መነን ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መከሰቱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ለህንጻ ግንባታ ስራ የተቆፈረው አፈር ተንዶ በስራ ላይ የነበሩ ሁለት ሰራተኞች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን የአንደኛው አስከሬን አስቀድሞ ተገኝቷል።

በፍለጋ ላይ የነበረው ሁለተኛው አስከሬን የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን እንዲሁም ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር  ማውጣት መቻላቸውን ጠቁመዋል።በመዲናዋ በግንባታ ስራዎች ላይ መሰል ተደጋጋሚ አደጋዎች እየተከሰቱ በመሆኑ አሰሪዎችና ሰራተኞች አስፈላጊውን የደህንነት መስፈርት ጠብቀው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

ዳጉ_ጆርናል

@Leyu_News
@Leyu_News
2.3K viewsedited  18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 21:31:41 " ከአሸባሪነት መሰረዙን በፅኑ እቃወማለሁ " - ኢዜማ

ኢዜማ የህወሓትን ከአሸባሪነት መሰረዝ " በፅኑ እቃወማለሁ " አለ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የህ.ወ.ሓ.ት ከሽብርተኝነት መሰረዝን በተመለከተ ውሳኔውን በመቃወም መግለጫው  አውጥቷል።

በዚህ መግለጫው ፤ " ህወሓትን ከሽብርተኝነት መሰረዝ ዘላቂ ሰላምን፣ እፎይታንና ቅቡልነትን የሚያመጣ አይደለም " ብሏል።

ፓርቲው የ " ህወሓት " ን ከሽብርተኝነት መሰረዝ የተቃወመባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር ያሳወቀ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ፦

- ህወሓት በፕሪቶሪያው ስምምነት አንቀጽ 6 መሠረት ትጥቅ ሙሉ በሙሉ አልፈታም።

- በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የትግራይን የሽግግር መንግሥትን የፌደራሉ መንግሥት በበላይነት እንዲያቋቁም ስምምነት ላይ ቢደረስም አሁንም ህወሓት በብቸኝነት የሽግግር መንግሥቱ አውራ ሆኗል ፤ ይኽም ህወሓት ዳግም የሀገር ስጋት የሚኾንበትን ዕድል እንደመስጠት የሚቆጠር ነው።

- በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያዘዙ፣ ሰብዓዊ ቀውስ ያደረሱ፣ ዜጎችን በጦርነት እንዲማቅቁ ያደረጉ፣ የሀገር ኢኮኖሚና፣ በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ቀውስ ውስጥ የከተቱ የሕወሓት አመራሮች በሕግ አልተጠየቁም።

- በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ትግራይን እንዲቆጣጠር አልተደረገም።

- የተጨፈጨፉ የሰሜን ዕዝ አባላት የመስዋዕትነት ምልክት የሚኾን ሐውልት ወይም ማስታወሻ በሰሜን ዕዝ ዋና ማዘዣ አልተደረገም።

- በህወሓት ቆስቋሽነት ሀገራችን ላይ ለደረሰው ውድመትና ሰቆቃ ፍትሕ እና ካሣ አልተሰጠም የሚሉት ይገኙበታል።

ኢዜማ ህወሓት የሚለው የፖለቲካ ድርጅት ስም በሕግ እንዲታገድ አለመደረጉ ከላይ የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ቡድኑ ከሽብርተኝነት ሰርዞ ከተጠያቂነት ነፃ ማድረግ ሊቀለበስ የማይችል ጥፋት ነው ብሏል።

ከዚህ በኋላ በ " ህወሓት " አማካኝነት ለሚደርስ ሀገራዊ ጉዳትም ዋነኛ ተጠያቂዎች ገዢው " የብልጽግና ፓርቲ እና መንግሥት " እንደሚኾኑ ከወዲሁ እንገልጸለን ሲል አሳውቋል።

ምክር ቤቱ ሌላው ቢቀር በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ግዴታዎች አየተፈፀሙ መሆኑን በቅጡ ሳያረጋግጥ፣ ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ላይ ለፈጸመው የሀገር ክህደት ወንጀል ተጠያቂ ሳይሆን እና በህወሓት የእብሪት ጦርነት የግፍ ገፈት ቀማሽ ለሆኑ በተለይ በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ለሚገኙ ወገኖቻችን ፍትሕ ሳይሰጥ ቡድኑን ከሽብርተኝነት መዝገብ እንዲሰረዝ መወሰኑ ታሪክ ይቅር የማይለው ፍርደ ገምድልነት  ሲል ውሳኔውን አውግዟል።

ሕወሓት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላትን በመጨፍጨፍ የሀገር ክህደት ፈጽሟል ያለው ኢዜማ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተከሰተው ጦርነት እና እሱን ተከትሎ ለደረሰው ሀገራዊ ቀውስ ቁጥር አንድ ተጠያቂ ህወሓት ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.5K viewsedited  18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ