Get Mystery Box with random crypto!

የሕወሃት ከሽብርተኝነት መሰረዙ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ሲሉ ዶ/ር ደብረጺዮን ተናገረ የሕወሃት | LEYU NEWS

የሕወሃት ከሽብርተኝነት መሰረዙ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ሲሉ ዶ/ር ደብረጺዮን ተናገረ

የሕወሃት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካዔል የፌደራሉ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕወሃትን ከአሸባሪነት ፍረጃ ማንሳቱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማዋቀር ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል በማለት መናገራቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ደብረጺዮን፣ በትግራይ ክልል በጀት ዝግጅት እና በእስረኞች ዙሪያ ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ግንኙነት እንደተጀመረ እና አዲስ የሚዋቀረው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እደረጃጀት ለፌደራሉ መንግሥቱ እንደተላከ መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ደብረጺዮን ይህን የተናገሩት፣ ትናንት በመቀሌ ለክልሉ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

@Leyu_News
@Leyu_News