Get Mystery Box with random crypto!

ጌታቸው ረዳ የሕወሃት ከፍተኛ አመራር ጌታቸው ረዳ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ሰሞኑን ያነሷቸው ቅ | LEYU NEWS

ጌታቸው ረዳ

የሕወሃት ከፍተኛ አመራር ጌታቸው ረዳ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ሰሞኑን ያነሷቸው ቅሬታዎች በከፍተኛ ትኩረት እንደሚታዩ እና ማጣራት እንደሚደረግባቸው መናገራቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

የጦር ጉዳተኞቹ ለእነሱ ተብሎ የተገዛ የሕክምና አቅርቦት እየተሸጠ ስለመሆኑ ነግረውኛል ያለው ዜና ምንጩ፣፣ የጦር ጉዳተኞቹ የጉዳት ካሳ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውንም ጠቅሷል።

የጦር ጉዳተኞቹ ከፍተኛ የሆነ የምግብ፣ የሕክምናና የንጽሕና መጠበቂያ አቅርቦት እጥረት እንዳለባቸው በሰላማዊ ሰልፍና ከጌታቸው ጋር ባደረጉት ውይይት መናገራቸው ተዘግቦ ነበር።

የጦር ጉዳተኞቹ፣ በመቀሌ አካባቢ ኩዊሃ እና ደጀን ሆስፒታል በተባሉ ሁለት ማገገሚያ ማዕከሎች የሚገኙ ናቸው።

@Leyu_News
@Leyu_News