Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-04 20:14:59 መምህርት መስከረም አበራን ጨምሮ 6 ግለሰቦች በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ

ፍርድ ቤቱ መስከረም አበራን ጨምሮ ስድስት ግለሰቦች በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል መዝገብ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፖሊስ ያቀረበውን የሽብር ወንጀል የጥርጣሬ መነሻን እና የተጠርጣሪዎችን የመከራከሪያ ነጥብ ተመልክቶ ነው ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀን የፈቀደው።

በሽብር ወንጀል ተጠርጠረው ዛሬ ከሰዓት ፍርድ ቤት የቀረቡ ተጠርጣሪዎችም መስከረም አበራ፣ ሳሮን ቀባው፣ ዮርዳኖስ አለሜ፣ ቢሰጥ ተረፈ፣  አሰፋ አዳነ  (ዶ/ር) እና ታደሰ መንግስቱ ይባላሉ።

ተጠርጣሪዎቹ ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን  በኃይል ለማፍረስ በማሰብ ኢ-መደበኛ አደረጃጀት በመፍጠር፣ ወጣቶችን በመመልመል፣ ለሽብር ወንጀል የሚውል ገቢ በማሰባሰብ ተግባር ተሳትፈዋል ሲል መርማሪ ፖሊስ የጥርጣሬ መነሻውን በዝርዝር ጠቅሶ  ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አቅርቧል።

በዚህ የሽብር ወንጀል የመነሻ ጥርጣሬ ተጨማሪ ማስረጃ ሰብስቦ ለመቅረብ 14 ቀን እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ÷ ሁሉም ተጠርጣሪዎች ከዚህ በፊት በሌላ ፍርድ ቤት በሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት ወንጀል ተጠርጥረው በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ እየቀረቡ ባለበት ሂደት ላይ ዛሬ  የሽብር ወንጀል ተብሎ መቅረባቸው ተገቢነት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል።

ስለሆነም የተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲከበር ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስም ከዚህ በፊት በተጠረጠሩበት ሁከትና ብጥብጥ አመጽ ማስነሳት ወንጀል ላይ በተደረገባቸው የማጣሪያ ምርመራ  የሽብር ወንጀል መፈፀሙን የሚያመላክቱ ተጨማሪ ማስረጃዎች በመገኘታቸው ምክንያት በሽብር ወንጀል መዝገብ እንዲቀርቡ ማድረጉን ጠቅሶ መልስ ሰጥቷል።

ዛሬ ከሰዓት የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡን የተመለከተው ችሎቱ ተጨማሪ ምርመራ መደረጉ አስፈላጊ ነው በማለት ለፖሊስ የ14 ቀን ጊዜ ፈቅዷል።

    ( ታሪክ አዱኛ )

@Leyu_News
@Leyu_News
2.1K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 20:14:39
2.1K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 20:10:37
የሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ አከፋፋዮች እና የችርቻሮ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በከተማዋ የሚታዩ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በዚህ መሰረት ቢሮው በሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ  በላይ በሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች ላይ ከማሸግ ጀምሮ ሌሎች ህጋዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስታውቋል።

ህብረተሰቡ በተለይም ሸማቾች ከተተመነው ዋጋ በላይ ከፍለው መሸመት የሌለባቸው ሲሆን፣ ጉዳዩ ሲያጋጥማቸው በነፃ የስልክ መስመር 8588 በመደወል ጥቆማ አድርሱኝ ሲል ቢሮው አሳውቋል፡፡

የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋን በተመለከተ ደርባ በ1067.36 ፣ ዳንጎቴ 1106.85፣ ሀበሻ በ1305 ብር፣ ሙገር በ1016 ብር፣ ኢትዮ 1056.80 ሳንቲም የመሸጫ ዋጋው መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.1K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 15:08:31
የጀርመን መራኄ መንግሥት አዲስ አበባ ገቡ!

የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። መራኄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ርእሠ ብሔር፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጋር በሁለትዮሽ ፣ አካባቢያዊ እና ዓለምአቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።DW እንደዘገበው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ እና ጀርመን ጠንካራ ግንኙነት ያላቸውና በብዙ የኢትዮጵያ ፈታኝ ወቅቶች ጀርመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን የቆየች አገር ናት ብለዋል።

የኢትዮጵያ እና የጀርመን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተጀመረ አንድ ምዕተ ዓመት ተሻግሯል። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ሲደርሱ የንግድ ተቋማት ባለቤቶችን እና ኃላፊዎች አስከትለው ነበር።ከጀርመን ሰፊ ቁጥር ያለው ባለሃብት የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስዓለም ጀርመን የኢትዮጵያ ሰፊ የልማት አጋር መሆኗን ጠቅሰዋል። በትምህርት እና በስልጠና ከምታደርገው ሰፊ ድጋፍ ባለፈ አሁን የሰላም ስምምነት ሒደቱ በላቀ እንዲሳካ ፣ ለመልሶ ግንባታ ሥራዎችም ድጋፍ ያደርጋሉ ብለዋል።

በሌላ በኩል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያ ላይ ችግር የሚፈጥር ነው የተባለው የሱዳን ቀውስ ክስተቱ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ነው ተብሏል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም እንዳሉት እስካሁን 61 አገሮች 7726 ዜጎቻቸውን በኢትዮጵያ በኩል ከሰዳን ማስወጣታቸውንና ከነዚህም 3517ቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ገልፀዋል።

[DW]

@Leyu_News
@Leyu_News
3.4K views12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 13:32:54 #update

የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ዩኤስአይዲ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በድርጅታቸው ድጋፍ ትግራይ ውስጥ የሚካሄደው የምግብ ዕርዳታ ሥርጭት ላልተወሰነ ጊዜ እንደቆመ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ድርጅቱ በክልሉ የዕርዳታ ሥርጭት ያቋረጠው፣ የዕርዳታ እህል ከመጋዘን ተዘርፎ ገበያ ውስጥ እየተሸጠ መኾኑን መረዳቱን ተከትሎ ምርመራ በመጀመሩ እንደኾነ ፓዎር ገልጸዋል። የአሜሪካ መንግሥት ጉዳዩን ለፌደራልና ለክልሉ መንግሥት ማሳወቁንና ኹለቱም በምርመራውና ጥፋተኞችን ተጠያቂ በማድረግ ዙሪያ ከድርጅቱ ጋር ለመተባበር ፍቃደኛ መኾናቸው ተገልጧል። ዩኤስአይዲ የዕርዳታ አቅርቦቱን እንደገና የሚጀምረው፣ በክልሉ ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓት እንደተዘረጋ ካረጋገጠ ብቻ መኾኑን መግለጫው አውስቷል።


@Leyu_News
@Leyu_News
3.3K views10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 13:31:47
ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ እና ወልዲያ የሚወስደው መንገድ ከ4:30 ጀምሮ ተከፍቷል።መንገዱ ከደብረሲና ሸዋሮቢት ድረስ በፀጥታ ችግር ተዘግቶ ነበር።ማለዳ ላይ የመከላከያ ሠራዊቱ ወደ ቦታው ሄዶ ከነዋሪው ህዝብ ጋር በትብብር እንዲከፈት መደረጉን የመረጃ ምንጮቼ ነግረውኛል።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.1K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 13:27:54 ያመነ ይድናል

#ይህ  0991555017 ይደውሉ
0991555017 ይደውሉ
መርጌታ መላክ መዳኒት ቀማሚ የቀደምት የሊቃዉንት አባቶቻችን ጥበብ ይሻሉ ወይም ይፈልጋሉ እንግዲያዉስ  ከምነሰጣቸው የጥበብ  አገልግሎቶች በጥቂቱ ከታች ተዘርዝረዋል
ለጥያቄ ይደውሉልን
@0991555017@
1 መፍትሔ_ሥራይ (የጠላት ድግምት መሻሪያ)
2 ለቡዳ
3 ለቁራኛ
4 #መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5 ለጋኔን
6 ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7 ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)
8   ለፀር (ለጠላት)
9 ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11 ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12 ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13 መስተፋቅር
14 ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15 ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16 ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17 የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18 ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19 መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20 መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21 ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22 ለልሳነ_ሰብእ
23 ለበረከት
24 ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25 ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26 ጸሎተ_ዕለታት
27 ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28 ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29 ለከበሮ
30 ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31 ለሙግት
32 ለሰላቢ
33 ለስንፈት ወሲብ
34 ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35 ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36 ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)
37 ለዱላ( ዱላ የማያስመታ)
38 መንስኤ_እስኪት (ለወንድ የመራቢያ አካሉ ለደከመ ላነሰ)
39 ህገ_ጠብቅ (የትዳር አጋራችን ወደሌላ እንዳይሄድ የሚያስር
እንዳይዘሙት የሚከለክል)
40 ለአይነ_ሰብእ (ከሰው አይን የሚጠብቅ)
41 ለአዙሪት
42 ለአስቸጋሪና ተመላላሽ ሲህር
43 ለሪህ በሽታ
44 የመገጣጠሚያ ህመም
45 ለጉልበት ድርቀት
46 የባት ህመም
47 የወገብ ህመም
48 የአንገትና ትከሻ ህመም
49 የከረመ ደረቅ ሳል
50 ለደም ግፊት
51 የሆድ መረበሽ
52 የከፋ የሆድ ድርቀት
53 በመኝታ ሽንት ለሚያመልጠው
54 የአእምሮ ጭንቀት፣ ድብርት፣         ከሰው  መገለል፣እንቅልፍ ማጣት
55 እንቅልፍ መብዛት
56 የተለየ የቆዳ ህመም
57 ክብደት ለመቀነስ
58 የእንቅርት በሽታ
59 ራስ ምታት ከሚከተሉት ህመሞች ጋ
60 አይን አካባቡ ውጥረት ካለ
61 የሳይነስ ህመም
62 የሆድ ድርቀትና የሆድ ህመም
63 የወር አበባ ችግር ካለ
64 የወገብ መንሸራተት ካለ
65 ውጥረትና የአእምሮ ጭንቀት
66 ለከፍተኛ ራስ ምታት
67 ማስታወስ፣ንቃት፣ተነሳሽነት ለሌላቸው
68 ለድምፅ መታፈን
69 ከአጫሽነት ለመላቀቅ
70 ራስን ስቶ በስቃይ ለሚኖር
0991555017
   0991555017 ይደውሉ
3.0K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 11:57:08
ተጨማሪ ቪዲዮ ጎንደር!

@Leyu_News
@Leyu_News
3.1K views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 11:23:26
ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ጎንደር ከተማ እንቅስቃሴዎች ቆመዋል።ምክንያቱ ደግሞ በክልሉ "ህግ ማስከበር" በሚል የሚካሄደውን ዘመቻ በመቃወም እንደሆነ የደረሱኝ መረጃዎች ያመለክታሉ።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.2K views08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 10:37:51 የሚዲያ ባለሙያዎችን ማዋከቡ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
የሚዲያ ባለሙያዎችን ማዋከቡ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ገለጹ፡፡

ዶ/ር ዳንኤል ይህን ያሉት በትናንትናው ዕለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛው የተከበረውን የፕሬስ ነጻነት አስመለክቶ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሚዲያ ነጻነት በአሁኑ ወቅት አደጋ ውስጥ መግባቱን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ በአሁኑ ወቅት ቢያንስ ስምንት ጋዜጠኞች በእስር ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በእስር ላይ ከሚገኙት ጋዜጠኞች በተጨማሪ በመንግሥት በመሳደድ ላይ ያሉ ጋዜጠኞች ስለመኖራቸውም ጠቁመዋል፡፡

የሚዲያ ነጻነት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር መሰረት መሆኑን ያስታወሱት ኮሚሽነሩ፤ ከአራት ዓመት በፊት የታየው የነጻነት ዝንባሌ በሂደት አደገኛ ወደሆነ ሁኔታ መለወጡን ጠቁመዋል፡፡ በወቅቱ የታየውን የሚዲያ ነጻነት ዝንባሌ ተከትሎ የተሻሻለው የሚዲያ አዋጅ ትልቅ ለውጥ የታየበት ቢሆንም፤ አፈጻጸሙ ላይ በርካታ ከፍተቶች መታየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በሕጉ አፈጻጸም ላይ ከታዩ ከፍተቶች መካከል ጋዜጠኞች በአዋጁ ላይ የተሰጣቸውን መብት በግልጽ የሚጥሱ እስሮችና ተገቢ ያልሆነ ወከባ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በአዋጁ ላይ በሚዲያ ላይ በቀረበ ይዘት የተፈጸመ ወንጀል ሲኖር፤ ከእስር በፊት ክስ መቅረብ ያለበት ቢሆንም አሁን እየታየ ያለው ከዚያ በተቃራኒ መሆኑን ዳንኤል ገልጸዋል፡፡

ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከሚዲያ ነጻነት የሚቀዳ ሲሆን፤ ከሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ የሚመዘንበት ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ የሚዲያ ሕግ ጥሩ ቢሆንም፤ አፈጻጻሙ ላይ በርካታ ክፍትቶች ታይተውበታል።

“ቅድመ ክስ እስር በሕጉ ቢከለከልም መንግሥት ይህን ሕግ በተደጋጋሚ ጥሶታል” ያሉት ዳንኤል፣ ችግሩን አሁንም ተባብሶ መቀጠሉ አሳሳቢ ከመሆኑ ባሻገር ችግሩን ለመቀልበስ ብዙ ሥራ እንደሚጠይቅም አመላክተዋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
3.2K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ