Get Mystery Box with random crypto!

የምድራችን ኃያላኑ ሩሲያና ቻይና መሪዎች “አዲስ የዓለም ስርአት” እንፈጥራለን አሉ፡፡  መሪዎቹ | LEYU NEWS

የምድራችን ኃያላኑ ሩሲያና ቻይና መሪዎች “አዲስ የዓለም ስርአት” እንፈጥራለን አሉ፡፡ 

መሪዎቹ ይህን ያሉት የቻይናው መሪ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በሞስኮ በነበራቸው የሁለት ቀናት ጉብኝት በነበረው ዘለግ ያለ ውይይት ላይ ነው፡፡

ጉብኝቱ ትልቅ ትርጉም ያለውና የቻይናው መሪ ዓለም የእስር ማዘዣም ጭምር በማውጣት ጫና ለመፍጠር እየተረባረባበቸው ላሉት የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን ያላቸውን አጋርነት ያሳዩበት እንደሆነ እየተዘገበ ነው፡፡ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር፣ ዓለምን በበላይነት ለመቆጣጠር አሜሪካ የምትደርገው እንደቅስቃሴ ማስቆም እንዲሁም ዩክሬን ጉዳይ መሪዎቹ በነበራቸው ቆይታ ከመከሩባቸው አንኳር ጉዳዮች ናቸው፡፡

"መሪዎቹ ይህ ግንኙነት ከሁለትዮሽ ያለፈና ለዓለም አቀፋዊ ገጽታ እና ለሰው ልጅ የወደፊት ህይወት ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው መክረዋል" ስትል ባወጣቸው መግለጫ ገልጻለች፡፡“ዓለምን በበላይነት ለመቆጣጠር የሚደረገው ሙከራ” አንቀበልም የሚል ጠንካራ የጋራ አቋም ያላቸው መሪዎቹ፤ በቀጣይ “አዲስ የዓለም ስርአት” እንፈጥራለንም ብለዋል፡፡

ፑቲን በበኩላቸው “የተባበሩት መንግስታት ዋና ሚና ፣ የጸጥታው ምክር ቤት፣ ዓለም አቀፍ ህግ እንዲሁም የተመድ ቻርተር አላማ እና መርሆች ላይ የተመሰረተ ይበልጥ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ የሆነ ሁሉን አቀፍ የዓለም ስርአት መፍጠር ላይ በትብብር እየሰራን ነው" ሲሉ መናገራቸው የክሬምሊን ድህረ-ገጽ አስነብቧል፡፡

ቻይና ፕሬዝዳንት ሺ “አሁን በ100 ዓመታት ውስጥ ያልተከሰቱ ለውጦች አሉ። አንድ ላይ ስንሆን እነዚህን ለውጦች እንመራለን” ሲሉ ለፑቲን መናገራቸውም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የቻይናው አቻቻው ሃሳብ የሚጋሩት ፑቲንም “እስማማለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News