Get Mystery Box with random crypto!

ሜሱት ኦዚል ጫማውን ሰቅሏል ! ጀርመናዊው የቀድሞ አርሰናል እና ሪያል ማድሪድ የአማካይ ስፍራ ተ | LEYU NEWS

ሜሱት ኦዚል ጫማውን ሰቅሏል !

ጀርመናዊው የቀድሞ አርሰናል እና ሪያል ማድሪድ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሜሱት ኦዚል ራሱን ከ እግር ኳስ ማግለሉን ይፋ አድርጓል።

የ 34ዓመቱ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሜሱት ኦዚል በተደጋጋሚ ያጋጠሙት ከባድ ጉዳቶች አስራ ሰባት አመታትን ካሳለፈበት የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ህይወት እንዲርቅ እንዳስገደዱት ተናግሯል።

ሜሱት ኦዚል ባስተላለፈው መልዕክትም " የ ፕሮፌሽናል እግርኳስ ህይወቴን ያሳለፈኩባቸውን ክለቦችን ፣ አሰልጣኞች እና የቡድን አጋሮቼን በጣም አመሰግናለሁ።

በሄድኩበት ክለብ ሁሉ ለእኔ ድጋፍ ለሚያደርጉ አድናቂዎቼ ትልቅ አክብሮት አለኝ ፣ ባለፉት ወራት እና ሳምንታት ያጋጠሙኝ ጉዳቶች ከ እግርኳስ እንድርቅ ይበልጥ ገፋፍተውኛል።"ሲል ተደምጧል።
@Leyu_News
@Leyu_News