Get Mystery Box with random crypto!

ሩሲያ በዩክሬን በርካታ ከተሞች ላይ ጥቃት ፈጸመች የሩስያ ሃይሎች በኪየቭ ክልል የመኖሪያ አከባቢ | LEYU NEWS

ሩሲያ በዩክሬን በርካታ ከተሞች ላይ ጥቃት ፈጸመች

የሩስያ ሃይሎች በኪየቭ ክልል የመኖሪያ አከባቢዎች ላይ በፈጸሙት የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ቢያንስ ሶስት ሰዎች ሲገደሉ በበርካታ የዩክሬን ከተሞች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።በዛሬዉ እለት የመጀመሪያዉ ጥቃት የሁለት የመኖሪያ ሕንፃዎች በዩክሬን ዋና ከተማ ዳርቻ ራሂሽቺቭ ላይ ተሰንዝሯል፡፡

ከተጎጂዎቹ መካከል የ11 አመት ታዳጊ እንደሚገኝ የነፍስ አድን አገልግሎት ገልጿል።በሌላ በኩል ሩሲያን በተቀላቀለችው ክራይሚያ ግዛት የሚገኙ ባለስልጣናት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች መርከቦቻቸውን ማጥቃቱን ተናግረዋል ።

በሴባስቶፖል የወደብ ከተማ ነዋሪዎች ከባድ ፍንዳታ እንደነበር ተናግረዋል፡፡የሩሲያ ከፍተኛ የጦር ባለስልጣን ሚካሂል ራዝቮዛይቭ በጥቁር ባህር መርከቦች ላይ ያነጣጠሩ ሶስት ጥቃቶችን ዩክሬን መፈጸሟንና ንብረት መዉደሙን ገልጸዋል፡፡ የሩሲያ የጦር መርከቦች ላይ ግን ጉዳት እንዳልደረሰ አክለዋ፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንዳሉት ሩሲያ ከ20 በላይ “ገዳይ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን” እንዲሁም ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን ተናግረዋል።የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ከሰዓታት በፊት ከሩሲያ መውጣታቸውን በመጥቀስ "በሞስኮ አንድ ሰው 'ሰላም' የሚለውን ቃል ለመስማት በሚሞክርበት ጊዜ በሌላ በኩል ጥቃት እንዲሰነዝር ትዕዛዝ ይሰጥ ነበር" ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News