Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 35

2023-03-27 21:30:36 የጋምቤላ ክልል የቀድሞ ፖሊስ ኮሚሽነር እና ምክትላቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ!

የጋምቤላ ክልል የቀድሞ ፖሊስ ኮሚሽነር እና ምክትላቸውን ጨምሮ 12 የጸጥታ ዘርፍ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ። የክልሉ መንግስት እነዚህን የጸጥታ አካላት እና ሲቪሎች በቁጥጥር ስር ያዋለው፤ “በዜጎች ላይ ያልተገባ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እና ግድያ ፈጽመዋል” በሚል ነው።

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አቡላ ኡባንግ እና በወቅቱ ምክትላቸው የነበሩት ቱት ኮር ለእስር የተዳረጉት፤ የጋምቤላ ነጻነት ግንባር (ጋነግ) እና የ“ኦነግ ሸኔ” ታጣቂዎች ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር በጋምቤላ ከተማ የሰነዘሩትን ጥቃት ተከትሎ በተወሰዱ እርምጃዎች “እጃቸው አለበት” በሚል ነው። ሁለቱ ታጣቂ ቡድኖች በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ ባደረሱት በዚሁ ጥቃት፤ ቢያንስ ሰባት ሲቪል ሰዎችን መግደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፈው መስከረም ላይ ባወጣው ሪፖርት አስታውቆ ነበር።

ኢሰመኮ በዚሁ ሪፖርቱ፤ ከጥቃቱ በኋላ በነበሩት ተከታታይ ሁለት ቀናት፤ 50 ሲቪል ሰዎች እንደተገደሉ ይፋ አድርጓል። መንግስታዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም አንድ ወር ለሚጠጋ ጊዜ ካደረገው ምርምራ በኋላ ባወጣው በዚሁ ሪፖርት፤ በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸሙት ግድያዎች “በተናጠል እና በጅምላ”፣ “ከፍርድ ውጪ” የተደረጉ እንደነበር አጋልጧል። እነዚህን ግድያዎች “በዋናነት የፈጸሙት” የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ኃይሎች መሆናቸውን ከዓይን እማኞች ማረጋገጡንም ኮሚሽኑ በመስከረሙ ሪፖርት አስታውቆ ነበር።

ይህንን የኢሰመኮ ሪፖርት ተከትሎ የጋምቤላ ክልል መንግስት መስከረም 22፤ 2015 ባወጣው መግለጫ፤ በሪፖርቱ የተጠቀሱ ወንጀላዎችን “መሰረት ቢስ” ሲል አጣጥሏል። የኮሚሽኑ ሪፖርት “ሚዛናዊነት እና ኃላፊነት የጎደለው”፣ “ለጠላት የወገነ” እና የጋምቤላ ህዝቦችን “ራሳቸውን የመጠበቅ ህገ መንግስታዊ መብታቸውን የደፈረ” በመሆኑ፤ የክልሉ መንግስት “እንደማይቀበለው እና እንደሚያወግዘው” በዚሁ መግለጫው አመልክቷል።

ባለፈው ሳምንት አርብ መጋቢት 15፤ 2015 በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቡላ ኡባንግ፤ በሰኔ ወር ከተፈጸመው ጥቃት በኋላ ከዚህ ኃላፊነታቸው ተነስተው የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሆነው እየሰሩ ነበር። በሰኔው ጥቃት የክልሉ ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት ቱት ኮር፤ በተመሳሳይ የጋምቤላ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን በሌላ ኃላፊነት ላይ ተሹመው ነበር።

ከፖሊስ ኮሚሽነሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር ከዋሉት የጸጥታ አካላት ውስጥ ሶስቱ በኮሎኔል ደረጃ ላይ ያሉ ሲሆን፤ አምስቱ ሌተናል ኮሎኔል ደረጃ ያላቸው መሆናቸውን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ዋና ኢንስፔክተር እና ረዳት ኢንስፔክተር ደረጃ ያላቸው የጸጥታ አባላትም በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ ይገኙበታል። የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ባለፈው አርብ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ በቁጥጥር ስር የዋሉትን 13 ግለሰቦች “የጸጥታ አካላት አመራሮች እና ሲቪሎች ናቸው” ብሎ ነበር።

Via Ethiopian Insider
@Leyu_News
@Leyu_News
771 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 20:34:37 ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ምን አሉ

የቀድሞ የአማራ ልዩ ኃይል አዛዥ ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ፤ ከሀገር ውጭ ህክምናዬን እንዳልከታተል ያገዱ አካላት ለምን እንዳገዱ ምክንያት የላቸውም ፤ ህክምናዬን በአፋጣኝ ካላደረኩ ቀኝ እግሬን እስከማጣት ሊያደርሰኝ ይችላል ብለዋል።

ቀደም ሲል በእርስ በእርስ ጦርነት የጥይት ምት እንዳለባቸው የገለፁት ጄነራሉ በተለያዩ ምክንያቶች በአግባቡ ህክምና እንዳልተከታተሉ ገልጸዋል።

እግራቸው ውስጥ ወደ 8 የሚደርሱ ፍንጣሪዎች መሰግሰጋቸውን የገለፁት ጄነራል ተፈራ ፤ እየቆየ ሲሄድ ነርቫቸውን በተደጋጋሚ እየነኩ መሆናቸውን እና የህክምና ባለሞያዎች የተሻለ ህክምና ካላገኙ እየከፋ እንደማሄድ እንደገለፁላቸው አስታውሰዋል።

ለዚሁ ህክምና ወደ እስራኤል ሀገር ለመሄድ ስርዓቱን ጠብቀው ያለውን ነገር ጨርሰው ሊወጡ ሲሉ መከልከላቸውን አስረድተዋል።

ብ/ጄነራል ተፈራ ፥ " ዓላማዬ ህክምና ነበር ምንድነው ምክንያቱ ብዬ ስጠይቅ ' እንድትወጣ አልተፈለገም ' የሚል መልስ ሰጡኝ በዛ ምክንያት ጉዞው ተደናቀፈ ፤ አሁን ህመሙ እየጨመረ መጥቶ አላንቀሳቅሰኝ አለ ፤ የነርቭ ስርዓቴም እየተናካ በመሆኑ ለመርገጥም ተቸግሬያለሁ ፤ አንዳንዴ እስከ ጉልበቴ ድረስ ይሰማኛል " ብለዋል።

አክለው ፤ " ገንዘብ ስጡን አላልነም ፣ እኔ ሄጄ መታከም አለብኝ ነው። ለምን እንደሚያግዱ እንኳን ምክንያት የላቸውም ፤ ምንድነው ምክንያቱ ለማገድ ? ህክምና ማግኘት ያለብኝን ማግኘት አለብኝ ምንድነው ምክንያታቸው ፤ ሰው ቢሰቃይ ይደሰታሉ እነዚህ ሰዎች ፤ አሁን መሄድ የለበትም ብለው ነው ከፃፉት አለ ማስረጃው ምንድነው ምክንያታቸው ወደዚህ አይነት ነገር ለምንድነው የሚገቡት ፤ መታከም አለብኝ ጤንነት የመብት ጉዳይ ነው ጤንነቴ አደጋ ላይ ነው ። እነዚህ ሰዎች በሌላ ሰው ቁስል ይደሰታሉ እንዴ ? ምንድነው የሚያስደስታቸው ? እነዚህ ናቸው ሀገር እየመሩ ያሉት ሀገር ሲመራ ሰፋ ብሎ በእኩልነት አይቶ እንጂ ካገኘው ከግለሰብም ከዚያም ጋር እየተናከሰ ነው እንዴ የሚሄደው ? " ሲሉ  ተናግረዋል።

ብ/ጄነራል ተፈራ ፥ አትሄዱም ብሎ የከለከላቸውን ኃላፊ " ለምንድነው የማልሄደው ? " ብለው እንደጠየቋቸውና ኃላፈው ሄደው እንዲታከሙ እንደሚፈልጉ ነገር ግን ከላይ ያሉት አካላት እግዱን እንደጣሉ እንደነገሯቸው አስረድተዋል።

ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ዶክተሮች ያዘዙት የህክምና ማስረጃ እንዳላቸው ገልጸው አግባብ ያለሆነው እግድ ተነስቶ ህክምናቸውን እንዲከታተሉ እንዲደረግ ብለዋል።

" መንግስት ሆደ ሰፊ መሆን አለበት ምክንያቱም ሀገር ነው እየመራ ያለው " ያሉት ብ/ጄነራሉ " ከግለሰቦች ጋር በሚደረግ ንትርክ ርቀት መሄድ አይቻልም የምለው ነገር ቀና ቢሆኑና ህክምናውን በወቅቱ ብወስድ ምክንያቱም ህግ እና ስርዓት አለ በዚህ መሰረት ሄጄ ታክሜ ምመጣበት እድል ቢፈጠር ይሄን ያለምንም ነገር እንደ በቀል ባይወስዱት " ብለዋል።

ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ከባለሃብቶች ለህክምና ወጪያቸው እገዛ ይፈልጉ እንደሆነ ተጠይቀው " ባላሃብቶች ለኔ ከሚያደርግ ስራ ላጣው ወጣት የስራ ዕድል ይፍጠር እኔ በራሴ እታከማለሁ የውጭ ጥያቄ አይደለም እኔ የምፈልገው እንድታከም እድሉን ላግኝ ነው " ብለዋል።

NB. ይህ የብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ቃል የተወሰደው " መድሎት " ለተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ከሰጡት ቃለምልልስ ነው።

@Leyu_News
@Leyu_News
971 views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 17:42:23
"የፒያኖዋ እመቤት" እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ አረፉ፡፡

እማሆይ ፅጌማርያም በኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የቫዮሊን እና ፒያኖ አቀናባሪ እንደነበሩ ይነገራል።

እማሆይ ፅጌማርያም ከአባታቸው ከአቶ ገብሩ ደስታ እና እናታቸው ወይዘሮ ካሣዬ የለምቱ በ1916 ዓ.ም በአዲስ አበባ ውስጥ ነው የተወለዱት።

በልጅነታቸው ለትምህርት በሄዱባት ስዊዘርላንድ ፒያኖን በደንብ ተምረዋል።

ከትምህርት መልስም በ19 አመታቸው ነበር ወደ ወሎ ግሸን ማርያም ገዳም በመሄድ በ21 አመታቸው ምንኩስናን የተቀበሉት።

ከ19 84 ዓ.ም ጀምሮ ኑሯቸውን በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ "ቅድስቲቷ ከተማ" ተብላ በምትጠራው እየሩሳሌም አድርገዋል።

አባታቸው ገብሩ ደስታ በኢትዮጵያ የከንቲባነት ታሪክ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩ ሲሆን በአፄ ሃይለስላሴ ዘመንም የፓርላማ አፈ ጉባኤ በመሆን ማገልገላቸውን ታሪክ ያስረዳል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@Leyu_News
@Leyu_News
1.2K views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 16:26:29 #ተጨማሪ

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ድረስ ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች በመንግሥት የመደበኛ ትምህርት ቤቶች ለድጋሜ ተፈታኞች እና የርቀት ትምህርት ተማሪዎች በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች አማካኝነት በበይነ መረብ #ብቻ እንደሚያካሂዱ ተገልጿል።

መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ 9 እስከ 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 በመማር ላይ ያሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ እንደሚጠበቅባቸውም ተገልጿል።

በመግለጫውም ተማሪዎ፣ ወላጆች፣ መዝጋቢዎች እና ከመምህራን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ  የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጥሪ አቅርቧል።

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለጽ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።


   @Leyu_News
@Leyu_News
1.5K viewsedited  13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 15:35:47 በጫሞ ሀይቅ ከሰጠሙት ስምንት ሰዎች መካከል የሶስት ሰዎች አስከሬን ተገኘ!

በጫሞ ሀይቅ በጀልባ እየተጓዙ ከሰጠሙት ስምንት ሰዎች መካከል የሥስት ሰዎች አስከሬን መገኘቱን የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል ።ከአማሮ ልዩ ወረዳ አልፉጮ አቡሎ ወደ አርባምጭ ከተማ ስምንት ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟ ይታወሳል።

ለሕይወት አድን ሥራው የተለያዩ ጀልባዎች እና  ዋናተኞች የተሰማሩ ሲሆኑ በተከናወነ የፍለጋ ሥራ የሥስት ሰዎች አስከሬን መገኘቱን የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበው አዳል ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።የሰጠሙ ተሳፋሪዎችን የመፈለጉ ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ የተገለፀ ሲሆን ያለድ ማዕበል  ፍለጋውን ፈተኛ አድርጎታል ተብሏል።

በእስካሁኑ ሂደት የሥስት ሰዎች አስከሬን ይገኝ እንጂ ቀሪ አምስት ተሳፋሪዎችን ጨምሮ ጀልባዋ እንዳልተገኘች ተገልጿል ። በሀይቁ አዞ የሚገኝ ስለሆነ የሰጠሙትን በህይወት የማግኘቱ ተስፋ የመነመነ እንደሆነ ተጠቁሟል።

[ዳጉ ጆርናል/Bisrat FM]

@Leyu_News
@Leyu_News
1.4K views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 12:58:33 #ExitExam

ምን ያህል ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ?

የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አመለወቅር ህዝቅኤል በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በተመለከተ (ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ፣ ዝግጅት እና ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ ተማሪዎችን በተመለከተ) ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

ወ/ሮ አመለወርቅ እዝቅኤል ፦

" አሁን የለየናቸው አሉ ፤ የደረሰን መረጃ አለ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎች ናቸው እጃችን ላይ ያሉት።

ነገር ግን ጥር ላይ በተለያየ ምክንያት ያላጠናቀቁ ልጆች በአንደኛ ሴሚስተር የሚያጠናቅቁና ወደ ምዘናው ሊመጡ የሚችሉ ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ።

ከዛ ባሻገር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዚህ System ውስጥ የሚያልፉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የደረሱን መረጃዎች አሉ።

አሁን በቁጥር ነው የተቀበልነው ልክ እንደ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በስም እያንዳንዱ ስም በሚመጣ ሰዓት የተወሰነ የቁጥር ለውጥ ሊኖረው ይችላል አሁን ባለንበት ሁኔታ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎችን እንፈትናለን ብለን እናስባለን።

ከመጀመሪያው ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች በኩል ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው የሚገኘው። ከዛ ባሻገር አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል ፈተናዎች እንዲፈተኑ በማድረግ፣ Sociologically እንዲዘጋጁ እንዲያጠኑ እየተሰራ ነው ተማሪዎችን በዛ ልክ አውቀው እየሰሩ ነው።

ፈተናው እንዴት manage ይደረጋል በሚለው ላይ የተለያዩ ማስፈፀሚያዎች ወደ ታች ወርደዋል በዚያ መሰረት ቅድመ ዝግጅቶች እየተደርጉ ነው የሚገኙት። "

የመጀመሪያውን ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?

" ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ።

ይሄ የሚሆነው እንዴት ነው የመጀመሪያው ዙር መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ነው ከዛ በኃላ ልክ 12ኛ ክፍል Private እንደሚፈተነው ሁሉ መውጫ ፈተና ላይም ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።

እስከዛ ድረስ ደግሞ ለምሳሌ የመውጫ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ የሚያስገኘውን ፈተና ማለፍ ባይችሉ እንኳን ዝቅ ባሉ ደረጃዎች በLevel ደረጃ ባሉት (ከዲግሪ በታች ባሉ መመዘኛዎች) ተፈትነው ልክ COC እንደሚፈተነቱ ተፈትነው ማለፍ የቻሉበት ደረጃ ላይ Certify ይደረጋሉ በዛ ስራ ማግኘት የሚችሉበት አማራጭ ይኖራቸዋል። "

@Leyu_News
@Leyu_News
1.6K views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 11:24:19
አዲስ አበባ

የትግራይ ክልል ግዚያዊ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ

----ምሽቱን በአዲስ አበባ----

@Leyu_News
@Leyu_News
1.5K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 10:25:22 ጠቅላይ ሚንስትሩ ለፓርላማ ማብራሪያ ሊሰጡ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች፤ ነገ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ሊሰጡ መሆኑ ታውቋል፡፡የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ማክሰኞ መጋቢት 19፤ 2015 በሚኖረው መደበኛ ስብሰባው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎችን የሚሰጡትን ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚያዳምጥ እና  የፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ያስገቡት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር መረጃዎች ደርሰውኛል ብሏል፡፡

ከአንድ ወር ዕረፍት በኋላ የተመለሱት የፓርላማ አባላቱ፤ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ መጋቢት 9፤ 2015 በተወካዮች ምክር ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በነበራቸው ስልጠና ይኸው እንደተነገራቸው ምንጮቹ ገልጸዋል።ይህንኑ ያረጋገጡት አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፓርላማ አባል፤ “ ‘በአስቸኳይ አስገቡ’ ብለው ባለፈው ቅዳሜ ነገሩን። ቀን ላይ ነግረውን፤ ‘እስከ ማታ ድረስ’ አሉን” ሲሉ ለጥያቄ ማቅረቢያ የተሰጠው አጭር ጊዜ  እንደነበር አስታውሰዋል።

የፓርላማ አባሉ አክለውም፤ “ብዙዎቻችን ‘አይሆንም፤ ተረጋግተን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርብ አይነት ጥያቄ በአግባቡ ማዘጋጀት አለብን’ ስንል እስከ እሁድ አመሻሽ ድረስ አቅርቡ ተባለ” ሲሉ ጥያቄ የማቅረቢያ ጊዜው በአንድ ቀን እንዲራዘም መደረጉን አስረድተዋል።በዚህ አካሄድ  እስከ ባለፈው ሳምንት እሁድ አመሻሽ ድረስ፤ የፓርላማ አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች አስገብተው ማጠናቀቃቸውን ጨምረው ገልጸዋል። 

በነገው ዕለት በሚካሄደው የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚቀርቡ ጥያቄዎች መካከል፤ “የኑሮ ውድነትን የተመለከቱ  ይኖራሉ” ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች ጠቁመዋል። “ወደ አዲስ አበባ አትገቡም እየተባለ ወደ አማራ ክልል የሚመለሱ ሰዎች” ጉዳይን የተመለከቱ ጥያቄዎችም፤ በነገው የፓርላማ ስብሰባ ጥያቄ ሊቀርብ እንደሚችል ምንጮች ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

[Ethiopia Insider]
@Leyu_News
@Leyu_News
1.5K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 10:24:19 ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተሰጠ መግለጫ!

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ስር የሚተዳደሩ ቁጥራቸው ከዐሥራ ሦስት በላይ የሆኑ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በአዲሱ የከተማ ድንበር ማካለል ወደ ኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ክልል ውስጥ የተካለሉ ቢሆኑም ለዓመታት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ገንብተው መንፈሳዊ አገልግሎት ሲሰጡ ከቆዩ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ

፩. የኤርቱ ሞጀ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲያናትን ለማፍረስ ተሞክሮ ከእነዚህ ውስጥ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በመሉ በአፍራሽ ግብረ ሀይል እንዲፈርስ ከመደረጉም በላይ የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያን በውስጡ ከሚገኙ ንዋያተ ቅድሳት ጋር በሙሉ እንዲቃጠሉ እና እንዲወድሙ ተደርጓል፡፡

፪. በኤርቱ ሞጆ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን አጥሩን ማፍረስ ተጀምሮ ምእመናን እና የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች ባደረጉት ርብርብ የማፍረስ ሒደቱ ለጊዜው ቢቆምም አሁንም ይህን ቤተ ክርስቲያንም ሆነ በሸገር ከተማ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ስለሆነም ለሀገር ባለውለታ የሆነችን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በማሳደድ እና በማውደም ታሪካዊ መሠረቷን ለመናድ እና ከሌሎች ቤተ እምነቶች በመነጠል በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተፈጸመ ያለው አድሏዊ እና ኢ-ሕገ መንግስታዊ የሆነው ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም እንዲደረግ እያሳሰብን የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥትም የድርጊቱን ፈጻሚ አካላት ላይ ተገቢውን እርምት እንዲወስድ ስንል እንጠይቃለን።

በመሆኑም፡
፩. መንግሥት የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በመሆናቸው ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ በመንገድ ላይ ተደብድበው ሕይወታቸው እንዲያልፍ የተደረጉት የቄስ ዐብይ መለሰ ገዳዮችን ተከታትሎ ለፍርድ እንዲያቀርብ እና ችግሩን ከሥር ከመሠረቱ በመፍታት የአገልጋዮችንና የምእመናን መብት እንዲያስከብር

፪. በሸገር ከተማ አስተዳደር እየተፈፀመ ያለው አብያተ ክርስቲያናትን የማፍረስ ድርጊት በአስቸኴይ እንዲቆም እንዲደረግ፣

፫. የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት ቦታ ተመላሽ እንዲያደርግ እና የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያንም በራሱ ወጪ እንዲያሠራ እንዲደረግ እንጠይቃለን።

ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተሰጠ መግለጫ
  
@Leyu_News
@Leyu_News
1.4K views07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 08:31:03
በስልጤ ዞን ጅብ በአንድ ቀን ሁለት ህጻናቶች ላይ ጉዳት አደረሰ

መኖሪያ ቤቷ በራፍ ላይ በጅብ የተበላችው ህጻን የመትረፍ እድሏ አነስተኛ ነው

በስልጤ ዞን ጦራ ከተማ አስተዳደር ጦራ መልታሜና ጦራ ሚሊኒዬም ቀበሌዎች ላይ በሁለት ህፃናት ላይ ጅብ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የጦራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት የኮሙኒኬሽን ባለሙያ አቶ አማን ከድር ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በትላትናው እለት አመሻሽ 12:30 አካባቢ በጦራ መልታሜ ቀበሌ ልዩ ስሙ መናፈሻ መንደር አካባቢ በመኖሪያ ቤቷ በር ላይ የቆመች አንዲት የሶስት አመት ህፃን ጀቡ ወደ ጫካ ይዟት ሊገባ ሲል በህብረተሰቡ ብርቱ ትግል መትረፏ ተገልጿል።

ህፃኗ ወደ ወራቤ ሆስፒታል ሪፈር ተልካ ህክምና እየተደረገላት የሚገኝ ሲሆን የመትረፍ እድሏ አነስተኛ መሆኑ ተገልጿል።በተመሳሳይ በትላንትናው እለት በጦራ ሚሊኒዬም ቀበሌ ላይ የ10 አንድ ህፃን ወደ መስኪድ እየተጓዘ እያለ በጅብ ተበልቷ በህይወት ተርፎ ህክምና እየተደረገለት መሆኑን አቶ አማን ከድር ጨምረው ተናግረዋል።
@Leyu_News
@Leyu_News
1.5K viewsedited  05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ