Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-04 10:37:10
3.0K views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 09:55:09 መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ያላስማማው የሽግግር መንግሥት ምሥረታ ጉዳይ መሆኑ ተነገረ!

በፌደራሉ መንግሥት እና እራሱን በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራውና በመንግስት "ኦነግ ሸኔ" ተብሎ በሚጠራው ቡድን መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሜናዊ ምሥራቅ ዛንዚባር ሙዪኒ የባሕር ዳርቻ ለዘጠኝ ቀናት ያህል በተካሄደው ውይይት፤ ኹለቱን አካላት ካላስማሙ ጉዳዮች መካከል አንዱ የጋራ የሽግግር መንግሥት ምሥረታ መሆኑን ተሳታፊዎች ተናገሩ።የሰላም ውይይቱ ትናንት ረቡዕ ሚያዝያ 25/2015 ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ኹለቱም ወገኖች በተናጥል ባወጡት መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ተደራዳሪዎቹን ካላስማሟቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የጋራ የሽግግር መንግሥት መቋቋም እንደሆነ ሥማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የንግግሩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።በዚህም በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን እና ብልጽግናን ጨምሮ ሌሎች ፓለቲካ ፓርቲዎችን ያካተተ የጋራ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መጠየቁን ቢቢሲ ከተሳታፊዎች ማረጋገጡን ዘግቧል።

የጋራ የሽግግር መንግሥት ምሥረታው በፌደራል መንግሥቱ ተደራዳሪዎች በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱንም እነዚህ ምንጮች በዛንዚባር ለሚገኙት የቢቢሲ ጋዜጠኞች ተናግረዋል።ተሳታፊዎቹ እንደገለጹት፤ የሽግግር መንግሥት በዋነኝነት የሚቋቋመው በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል መተማመን እንዲኖር እና አገሪቱ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ እንድትችል የማሻገር ኃላፊነትን እንዲወጣ ለማድረግ መሆኑ ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ፤ በትናንትናው ዕለት በመጀመሪያው ዙር በነበረው ንግግር በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ ጠቅሶ፤ ውይይቱ በአመዛኙ ገንቢ መሆኑንም አስታውቋል።የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ውይይቱ መጠናቀቁን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ፤ ቁልፍ ብሎ በጠራቸው ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መደረስ አለመቻሉን አመልክቷል።

በዚህ በመጀመሪያው ዙር ውይይት ላይ ከተነሱ ሃሳቦች ሌላኛው በመንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል ሊደረስ የሚገባው ስምምነት በዘላቂነት ጦርነት በሚያከትም መልኩ፤ እንዲሁም ኹሉንም የሠራዊቱን ፖለቲካዊ እና የጦር ክንፉን ማካተት አለበት ተብሏል።ኬንያ እና ኖርዌይ በአሸማጋይነት በተሰየሙበት በዚህ የመጀመሪያ ውይይት ላይ ከደቡብ ኦሮሚያ አካባቢ ከሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት መካከል ኹለት ተወካዮች በዚህ ውይይት እንዲሳተፉ መደረጉም ተገልጿል።

በዚህ ውይይት ላይ የተገኙት ስድስት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ተወካዮች ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ልዑካን ሲሆኑ፤ ኹለቱ የሠራዊቱ አባላት በአሸማጋዮቹ በኩል እንዲሳተፉ መደረጉን እና በአጠቃላይም ቡድኑ በስምንት ተወካዮች መወከሉም ተሰምቷል።የኢትዮጵያ መንግሥትን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዴዎን ጤሞቴዎስ ተደራዳሪ ሆነው መቅረባቸውንም ተገልጿል።

በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኩል ደግሞ የታሪክ ምሁሩና በጆርጂያ ስቴት ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን፣ ከኦነግ መስራቾች አንዱና ለበርካታ ዓመታት አመራር የነበሩት ጣሃ አብዲ እንዲሁም የጦሩ አዛዥ ዋና አማካሪ የሆኑት ጂሬኛ ጉደታ ይገኙበታል።በኦሮሚያ ክልል ለዓመታት የዘለቀውና ለበርካታ ሰዎች ሞት እና መፈናቀል ምክንያት የሆነውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት በፌደራሉ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል የመጀመሪያ ዙር ውይይት የተጠናቀቀ ሲሆን ቀጣይ ዙር መቼ ሊካሄድ እንደሚችል አልተገለጸም።

በዚህ የመጀመሪያ ውይይት የተነሱ ጉዳዮች ዝርዝር ባይጠቀሱም፣ ግጭቱን በዘላቂነት እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስቆም እንዲቻል የሰላም ውይይቱን መቀጠል አስፈላጊ ስለመሆኑ መግባባት ላይ መደረሱን ተገልጿል።በዚህም ኹለቱም አካላት ባወጡት መግለጫ በቀጣይ ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያላቸውን ቁርጠኝነት አስታውቀዋል።

[BBC]

@Leyu_News
@Leyu_News
3.4K views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 09:34:31
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በክልሉ ተፈጸመ በተባለው የዕርዳታ እህል ዝርፊያ ዙሪያ አስተዳደራቸው ምርመራ መጀመሩን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ከዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች፣ ዲፕሎማቶችና ከክልሉ ማኅበረሰብ መሪዎች የዕርዳታ እህል ላልታሰበለት ዓላማ እየዋለ ስለመኾኑ ጥቆማ እንደደረሳቸውና ድርጊቱቱ እንደተፈጸመ "በርካታ መረጃ" መኖሩን የገለጡት ጌታቸው፣ ጥፋተኛው ማንም ይኹን ማን ተጠያቂ እናደርጋለን ብለዋል። ኾኖም ኹሉም ረድኤት ድርጅቶች በክልሉ የዕርዳታ አቅርቦታቸውን እንዲቀጥሉ ጌታቸው ጠይቀዋል።

በተያያዘ ዜና የትግራይ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በክልሉ ውስጥ የተሠረቀ የዕርዳታ እህል ገዢዎችንና ሻጮችን ለመቆጣጠር ጥረት እንደሚያደርግ መግለጡን ቪኦኤ ዘግቧል። ኾኖም ኮሚሽኑ የክልሉ መንግሥት በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች የተዘረፈ የዕርዳታ እህል የለም በማላት ማስተባበሉን ዘገባው አመልክቷል።

የዓለም ምግብ ድርጅት፣ ከሽራሮ መጋዘኑ ለ100 ሺህ ተረጂዎች የሚበቃ ዕርዳታ እንደተዘረፈበትና በዝርፊያው ላይ ምርመራ እያደረገ እንደኾነ በቅርቡ አሶሴትድ ፕሬስ መዘገቡ ይታወሳል።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.3K views06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 08:10:04 3 ነጥቦች

ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ዛሬ ሚያዚያ 26/2015 አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ተሰምቷል።

በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ በርካታ ንፁሃን ሰለባ እየሆኑ እንደሚገኝ ከየአካባቢዎች የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።

ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረገው የትራንስፖርት ጉዞ ሸዋሮቢትና አካባቢው በተፈጠረ ግጭት መንገዱ ዛሬም ዝግ መሆኑ ተሰምቷል።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.5K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 20:26:42
መልካም ዜና!

ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ለህክምና ወደ ውጭ እንዲሄዱ በፍርድ ቤት ተፈቅዷል!

ከወራት በፊት ለህክምና ወደ እስራኤል ሃገር ለመሄድ ወደ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያቀኑት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ከሃገር እንዳይወጡ መከልከላቸው ይታወቃል።ይህንንም ተከትሎ ጀነራል ተፈራ ማሞ ክስ መስርተዋል። 

ፍርድ ቤቱም በጀነራል ተፈራ ማሞ ላይ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት  በህገወጥ መልክ ክልከላ ፈፅመዋል ብሏል።

በዚህም ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ከሃገር የመውጣት በህግ የተሰጣቸውን መብት የገደበ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ከአገር ወጥተው እንዲታከሙ ወስኗል ሲሉ ጠበቃቸው ለሮሃ ቲቪ ተናግረዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.2K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 20:15:47 የ5 ዓመቷን ህጻን በማገት አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመዉ ተከሳሽ በእሰራት ተቀጣ

በምእራብ አርሲ ዞን  ኤቨን አርሲ ወረዳ የአምስት ዓመቷን ልጅ ከትውልድ መንደሯ አታሎ በወዉሰድ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመዉ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የዞኑ ፖሊስ አቃቢ ህግ ጽህፈት ቤት አቃቢ ህግ ወ/ሮ መሪያ አደም በተለይ ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በዞኑ ኤቨን አርሲ ወረዳ ተከሳሽ ፍሪ ዋቄ  የተባለ ግለሰብ  የአምስት አመቷ ህጻን ልጅ አታሎ ከትውልድ ስፍራዋ ይዞ ሊሰወር ሲንቀሳቀስ በጥበቃ ላይ የነበሩ ፖሊሶች ተጠራጥረው በቁጥጥር ስር እንዳዋሉት አስረድተዋል፡፡ሆኖም ግለሰቡ የተያዘው ህጻናትን በማስኮብለል ተጠርጥሮ ቢሆንም ህጻኗ ላይ አጠራጣሪ ነገሮች በመታየቱ  በኤቨን አርሲ ወረዳ ሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ  ፖሊስ ወንጀል  ምርመራ  በኩል የህክምና ምርመራ ተደርጎላታል፡፡ በምርመራዉ የአስገድዶ  መደፈር ጥቃት የፈጸመባት መሆኑን በበቂ የህክምና ማስረጃ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ፖሊስ ከአቃቤ ህግ ጋር በመሆን በተገቢ ሁኔታ የወንጀሉን አፈጻጸሙን በማጣራት  የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ  የላከ ሲሆን  አቃቤ ህግ ቀረበለትን የምርመራ መዝገብ በማጣራት  ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን ሲከታተል የቆየው  የምእራብ አርሲ  ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት  ተከሳሽ ፍሪ ዋቄ የተባለው ግለሰብ በፈጸመው የህጻናትን አግቶ  በመውሰድ እና አስገድዶ መድፈር ወንጀል  በ16 ዓመት ጽኑ እስራት  እንዲቀጣ መወሰኑን  ወ/ሮ መሪያ አደም ጨምረው ለብሰራት ሬዲዮ  ተናግረዋል፡፡

ዳጉ_ጆርናል
@Leyu_News
@Leyu_News
4.1K views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 17:01:17 "መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረውን ጥቃት በአስቸኳይ ያቁም!"፦ እናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ 

መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረውን  ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቆም እናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።

ፓርቲዎቹ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ የአማራ ህዝብ መፈናቀል፣ ስደትና እንግልት እንዲቆም፣ የጋዜጠኞች፣ የምሁራንና ማኅበራዊ አንቂዎችን በግፍ ማሰር፣ መደብደብ፣ ማንገላታት እና አፍኖ-መሰወርን እንዲቆም እንዲሁም ማንነትን ማዕከል ባደረገ ሁኔታ የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች በላያቸው ላይ ማፍረስና ማባረር እንዲቆም አሳስበዋል።

የጋራ መግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ የጀመረውን ጥቃት በአስቸኳይ ያቁም!

በወቅታዊ ጉዳይ ከእናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ  የተሰጠ የጋራ መግለጫ

ባለፉት 30 ዓመታት የተከተልነው “የጎሳ ፌደራሊዝም” የኢትዮጵያ ህዝብ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች በሰብዓዊነቱ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እንዳያደርግ አግዶታል፡፡ የሠላምና የጸጥታ ዕጦት፣ መረን የለቀቀ ሙስና፣ አድሏዊ አሠራር፣ ዘውገኛነትና ጎጠኝነት ሥር ሠዶ የገነገነበት ዘመን ላይ እንድንደርስም አስገድዶናል። በዚህ ላይ ስለሀገሩ ኅላዌ፣ አንድነትና ሉዓላዊነት የሚገደው ዜጋ ደግሞ ተብከንካኝና ባይተዋር እንዲሆን ተፈርዶበታል። ኢትዮጵያውያን ዛሬ የምንገኝበትን የብሶት ደረጃ “አላውቅም” የሚል የገዥው ፓርቲም ሆነ የመንግሥት ባለሥልጣን ካለ ያለበትን የኃላፊነት ሥፍራ የዘነጋና እውነታውን የካደ ነው፡፡  የኢትዮጵያ ህዝብ በከፍተኛ ችግር፣ ምስቅልቅልና ብሶት ዉስጥ ነው።

ማንኛውም ዜጋ በአገሩ ዉስጥ የህይወት ዋስትና ሊኖረው ሲገባ፣ ዛሬ ዘውግን ወይንም ሃይማኖትን፣ ወይንም ደግም ከገዥዎች ፍላጎት የተለየ ሃሳብ መግለጽን መሠረት ባደረጉ ፍረጃዎች የተነሳ በዜጎች ላይ ከባድ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል። በሠላም ወጥቶ መግባትም ፈታኝ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ በተለይም ማንነትን መሰረት ባደረገ የጥላቻ እሣቤ የአማራ ህዝብ ለመፈናቀል፣ ስደትና እንግልት ተዳርጓል፡፡ በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል-ጉምዝ ክልሎች ዜጎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፣ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፡፡

ሕወሓት መራሹ ኢህአዴግ በ1983 የፖለቲካ ሥልጣን ከጨበጠበት ወቅት ጀምሮ አማሮች በጠላትነት ተፈርጀው በተደጋጋሚ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ደርሶባቸዋል፡፡ የብልጽግና መንግስትም ይህንኑ ፈለግ ተከትሎ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ጦስ የዜጎች ህይወት በሰብአዊነት መንጠፍ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጓል።

ከዚህ አኳያ የሁሉም ዜጎች ህይወት እኩል ዋጋ፣ እኩል ክብርና  ዋስትና ሊያገኝ ይገባል ብለን እናምናለን። የመንግሥት ግንባር ቀደም ሃላፊነትና ሥራ የዜጎችን ህይወት መጠበቅ ሆኖ ሳለ ባለፉት አምስት አመታት የዜጎች ህይወት በእየለቱ ሲቀጠፍ መንግስት ያሳየው ዳተኝነት አሳፋሪ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጡ ሰሞን የነበረው የለውጥ ፍላጎትና ጠንካራ ትግል የተወሰነ ለውጥ መሣይ ብልጭታ በመፍጠሩ፣ ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት ለመግለጥ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። “ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት ይቻላል” የሚል ተስፋም አጭሮ ነበር። ይሁን እንጂ “ላም አለኝ በሰማይ …” በሆነ መልኩ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ተክዶ በተለመደው መልኩ በጎሳ ስሁት ትርክት ውስጥ የምትታሽ ሀገርና ሥርዓት ውስጥ እንድንኖር ተገደናል፡፡

ጋዜጠኞች፣ ምሁራንና ማኅበራዊ አንቂዎች፣ በተናገሩትና በጻፉት ህግን ጥሰው ከሆነ በፍርድ ቤት እንደሚጠየቁ እናውቃለን፡፡ ከዚህ ውጭ በሆነ መልኩ ዜጎችን በግፍ ማሰር፣ መደብደብ፣ ማንገላታት እና አፍኖ-መሰወርን ግን ምን አመጣው?

በቅርቡ ዳግም ጅምላ እስሩ መፈናቀሉ ግድያውና አፈናው የበረታው በአማራው ህዝብ ላይ መሆኑ ምሬትና ብሥጭት እንዲጨምር አድርጓል። በአገራችን ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሣይቀር ማንነትን ማዕከል ባደረገ ሁኔታ ማፈናቀልና ማሣደድ  ከፍተኛ  ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡  
የብልጽግና መራሹ መንግሥት የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች በላያቸው ላይ ማፍረስና ማባረር ከጀመረ ሰነባብቷል። በተለይም የዜጎችን በአገራቸው ዉስጥ በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት በሚደፈጥጥ መልኩ አማሮች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ እየተደረጉ ለከፍተኛ ችግርና እንግልት መዳረጋቸውም አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። የአማራው ህዝብ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በመሆን በደሙና በአጥንቱ  በሠራት አገር ባይተዋርና አገር አልባ ተሳዳጅ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን በግልጽ ተገንዝበናል፡፡ ከዚህ በላይ የተገለጡት እውነታዎች፣ በአማራው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ብሶቶችን እንደፈጠሩ፣ የዚህ ችግር ባለቤት በመሆን የወረራ ስልትና ፈጠራውን ያቀነባበሩ ኃይሎች ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ ከዚህ ቀደም ሦስቱም ፓርቲዎች (እናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ) ቀደም ሲል የተዘረዘሩትን ጉዳዮች እየገለጡ ችግሮች እንዳይባባሱ መንግስትን ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።

በሕወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል የተከናወነው ከባድ የእርስበርስ ጦርነት አገርንና ህዝብን ከፍተኛ ጉዳት ላይ ጥሏል። የትግራይን፣ የአማራን፣ የአፋርን ህዝብንም የበለጠ ጎድቶታል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ወገኖቻችን የጦርነቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩት የአካል ጉዳተኛ ተደርገዋል፡፡ ዜጎች በገዛ አገራቸው ተፈናቃይና ስደተኛ ሆነዋል። የመሠረተ-ልማት አውታሮችና ተቋማት ወድመዋል። ህዝቡ ገና ከጦርነቱ ቁስል አላገገመም። ታዲያ ገዥው መንግስት ይህንን መራር እውነት ዘንግቶ እንዴት በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት ሊከፍት ቻለ!? ይህ አይነቱ አካሄድ አገር አፍራሽ በመሆኑ ከወዲሁ ጊዜው ሳይሄድ መንግስት እጁን ሊሰበስብ ይገባል፡፡

ነገሮች እንዲህ በተወሳሰቡ ሁኔታዎች ውስጥ እያሉ የፌዴራል መንግሥት ችግሩን በሚያባብስ መልኩ ወደ አማራ ክልል  ሠራዊት አዝምቶ “ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን መቆጣጠርና ትጥቅ ማስፈታት” በሚል ሽፋን በየቦታው በከባድ መሣሪያ ጭምር በዜጎች ላይ ተኩስ ከፍቷል።  የተረጋጋና አስተማማኝ ሁኔታዎች ሳይፈጠሩ፣ ተቻኩሎ፣ በሃይል ትጥቅ ለማስፈታት መሞከር ሌላ ጦርነት ከመቀስቀስ የተለየ ውጤት የለውም።

ሠላም የተነፈጉና እየተሳደዱ ያሉ ዜጎችን፣ በቅድሚያ ትጥቅ ማስወረድ ለምን አስፈለገ? ኢትዮጵያ ከተዘፈቀችበት የጎሰኝነት አረንቋ ሳትወጣ፣ በዘውግ በተደራጁ ሃይሎች በሚመራ መንግሥት የሚወሰዱ ማናቸውም እርምጃዎች ወደ ሌላ ችግር የሚያስገቡ ናቸውና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለሆነም መንግስት በአማራ ክልል ዉስጥ የጀመረውን ህገ-ወጥ ጥቃት በአስቸኳይ አቁሞ ውይይትን መሰረት ባደረጉ አካሄዶች ብቻ ችግሮችን እንዲፈታ አጥብቀን እናሳስባለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ
ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፳፻፲፭
አዲስ አበባ

@Leyu_News
@Leyu_News
4.3K views14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 17:00:34
3.8K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 16:06:37 መረጃ

ሰሜን ሸዋ አንፆኪያ ከምዛ ወረዳ አምቦውሃ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከ6:00 ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊትና በአማራ ፋኖ መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ገልፀዋል!!

@Leyu_News
@Leyu_News
3.9K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 14:10:11 ተጨማሪ መረጃ

በመንግስትና በኦነግ ሸኔ መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን አምባሳደር ሬድዋን አስታወቁ

በመንግስትና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) መካከል ላለፈው አንድ ሳምንት ሲደረግ የነበረው ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን የመንግስት ዋና ተደራዳሪ ሬድዋን ሁሴን አስታወቁ።

ሬድዋን በፅሁፍ መግለጫቸው  ሁለቱ ወገኖች በታንዛኒያ በመጀመሪያው ዙር ያደረጉት ድርድር ገንቢ እንደነበር ነገር ግን በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት መድረስ አለመቻሉን ገልፀዋል። ስምምነት ያልተደረሰባቸውን ጉዳዮች ግን አልተናገሩም።

የሰላም ድርድሩ አስፈላጊነት ላይ በሁለቱም ወገን መግባባት መኖሩንና በቀጣይ ተመሳሳይ ድርድር ለማድረግ ዝግጁነት መኖሩንም ሬድዋን አመልክተዋል። አደራዳሪዎችን ያመሰገኑት ሬድዋን መንግስት ለሰላም ዝግጁ መሆኑንና በሀገሪቱ ህገመንግስት ማዕቀፍ ውስጥ ማናቸውንም ግጭቶች ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን አመልክተዋል። በድርድሩ ዙሪያ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) በኩል ይህ ዘገባ እከተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ የተባለ ነገር የለም።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.1K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ