Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-25 21:01:15
በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሱዳን በተፈጠረው ውጊያ ቢያንስ ስምንት ኢትዮጵያዊያን እንደተገደሉና ሌሎች አራት ኢትዮጵያዊያን የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ኢትዮጵያዊያኑ ለሞት እና ለመቁሰል አደጋ የተዳረጉት፣ በተባራሪ ጥይት እና ከባድ መሳሪያ አረሮች ፍንጣሪ ሳቢያ መኾኑን ኢምባሲው መግለፁን ዘገባው አመልክቷል።

ከአገሪቱ መውጣት የሚፈልጉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በአውቶብስ ወደ መተማ ለመሸኘት እየመዘገበ መሆኑን ኤምባሲው መግለፁን የጠቀሰው ዘገባው፣ የኤምባሲው ሠራተኞች ካርቱምን ለቀው ለኢትዮጵያ ቅርብ በሆነችው የሰሜን ሱዳኗ ገዳሪፍ ከተማ ሥራቸውን እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሷል።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.1K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 20:08:19
#ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ እና አራጋው ሲሳይ ከእስር ተለቀዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.1K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 13:02:27
ዜና ችሎት!

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው ሁለቱም በ20,000 ብር ዋስትና እንዲወጡ ታዟል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
4.4K views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 12:26:05 የስዊድን ፣ ኖርዌይ ፣ ኬንያ ፣ አውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በመንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል በሚደረገዉ ድርድር እንደሚገኙ ተሰማ

ቢቢሲ አማርኛ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሁለት ምንጮቼ እነገሩኝ እንዳለዉ ፤ መንግሥት ከታጣቂ ቡድኑ ጋር በሚደረገው ንግግር የስዊድን፣ የኖርዌይ፣ የኬንያ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች እንደሚገኙ ዘግቧል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እነዚህ ምንጮች የተጠቀሷቸው አገራት በድርድሩ ይገኛሉ ይበሉ እንጂ የትኞቹ አገራት ምን ሚና ይኖራቸዋል፤ በዋናነት የማደራደር ኃላፊነትን የሚወስደው የትኛው አካል ነው የሚለው አልተለየም ብለዋል ሲል አክሏል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ መሮ ዲሪባም የሚመሩት ታጣቂ ቡድን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሚያደራድር ሦስተኛ አካል መኖሩን ያረጋግጡ ሲሆን፣ አደራዳሪዎቹ እነማን እንደሆኑ በስም ከጥቀስ ተቆጥበዋል።

መሮ ዲሪባ ታጣቂ ቡድኑን ወክለው ከመንግሥት ጋር የሚደራደሩ የልዑክ ቡድን አባላት በትናንትናዉ እለት ወደ ታንዛኒያ ጉዞ እያደረጉ ስለመሆኑም ጨምረው ተናግረዋል።

የሠራዊቱ ዋና አዛዥ መሮ ዲሪባ ይህ ንግግር በታንዛኒያዋ ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው ዛንዚባር ደሴት ላይ እንደሚከናወን ገልጸው፤ “የጥይት ድምጽ ሳይሰማ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ መልስ የሚያገኝ ከሆነ በራችን ሁሌም ክፍት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

መሮ እንደሚሉት “በቅርቡ” የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና መንግሥት ሦስተኛ ወገን ባለበት በኬንያ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘው የታጣቂ ቡድኑ ተወካዮች በቦታው ቢገኙም የመንግሥት ተወካዮች ግን ሳይገኙ ቀርተዋል ማለታቸዉን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል።
“በሌሎች አገራት ግብዣ በኬንያ ለመገናኘት ቀጠሮ ነበር። ነገር ግን መንግሥት ሳይገኝ ቀረ” ያሉ ሲሆን፤ በአሁኑ ድርድር ስኬት ላይ ጥርጣሬዎች ቢኖሯቸውም የንግግር ሂደቱ ሰላም ሊያመጣ ይችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ጨምረው ተናግረዋል።

“ንግግር መጀመሩ ጥሩ ነው። መነጋገር እና መፍታት ያለብን ብዙ ነገሮች ስላሉ ጉዳዩ በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቅ አይሆንም” ብለዋል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.3K views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 08:24:27 ራያ ፣ አክሱም እና መቀሌ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸዉን መመዝገብ ጀመሩ!

የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የመማር ማስተማር ስራቸዉን አቋርጠዉ የነበሩ በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ዳግም ትምህርት ለመጀመር በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን አስታዉቀዋል።ከነዚህም ዉስጥ የራያ ፣ አክሱም እና መቀሌ ዩኒቨርስቲዎች ለተማሪዎቻቸዉ ጥሪ ማቅረባቸዉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በአክሱም ዩኒቨርስቲ የኤሌክትሪካል ምህንድስና 4ኛ አመት ተማሪ የሆነዉ በርናባስ የሺጥላ ለብስራት ራዲዮ እንደተናገረዉ ፤ ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ ለዩኒቨርስቲው መረጃ እንደሰጡ እና የኦንላይን ምዝግባ መከናወኑን ገልጿል። ዩኒቨርስቲው ባወጣዉ ማስታወቂያ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዉ ትምህርታቸዉን ከሚከታተሉ ተማሪዎች ዉጭ ሁሉም ተማሪዎቹ ምዝገባዉን እንዲያከናዉኑ ጥሪ አድርጓል።

ከሁለት አመታት በላይ ከትምህርት የራቀዉ በርናባስ ፤ ያሳለፋቸዉ ግዚያት ተስፋ አስቆራጭ የነበሩ ቢሆንም ዳግም ትምህርት ለመጀመር ተስፋ ማድረጉን ተናግሯል። የቅርብ ጓደኞቹን ዋቢ አድርጎ እንደነገረን ከሆነም ተማሪዎች ትምህርት በተቋረጠባቸዉ ግዜያት በርካታ ተማሪዎች ወደ ሌላ የስራ መስክ የገቡ እና ሌላ ትምህርት የጀመሩ በመሆኑ ወደ ዩኒቨርስቲው የሚመለሱ ተማሪዎች ሊቀንስ እንደሚችል ጠቁሟል።

በተመሳሳይ የመቀሌ እና ራያ ዩኒቨርስቲዎችም ባስቀመጧቸዉ የስልክ ቁጥሮች ተማሪዎቻቸዉ እየደወሉ አልያም የጽሁፍ መልዕክት እየላኩ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። አክሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹ እስከ ሚያዚያ 18 ድረስ እንዲመዘገቡ ቀነ ገደብ አስቀምጧል። ዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርት የሚጀምሩባቸዉን ቀናት ወደፊት እንደሚያሳዉቁም አስታውቀዋል።

[Bisrat FM]

@Leyu_News
@Leyu_News
4.2K views05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 07:56:45
“የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ”- ጄነራል ዳጋሎ

ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ዋና አዛዥ ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ “የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ” አሉ።

ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ ከስካይ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ “አሁን ላይ እየተዋጋን ያለነው ከሱዳን ጦር ጋር ሳይሆን ከቅጥረኛ ኃይሎች ጋር ነው፤ ምክንያቱም 90 በመቶ የሱዳን ጦር ከጥቅም ውጪ ሆኗል” ብለዋል። ዳጋሎ አክለውም፤ “ከዚህ በኋላ ከሱዳን ጦር ዋና አዛዣ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተቀምጦ መነጋገር ምንም ዋጋ እንደሌለውና አልቡርሃን ከዚህ በኋላ ያለው አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

“ጦርነት አልፈልግም ነበር፣ ከጦርነት ይልቅ ሰላም እና መረጋጋትን ነው የምመርጠው” ያሉት ዳጋሎ፤ “ወደ ጦርነት እንድንገባ የገፋፋን አልቡርሃን ነው፤ አሁን ግን እጁ ላይ ምንም አልቀረለትም” ሲሉም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ የተጠየቁት ሃሜቲ፤ “እኔ የሱዳን ህዝብ አንድ አካል ነኝ፤ ካርቱምን ለቀቄ ወደየትም መሄድ አልችልም፤ እዛው ጦር ግንባር ላይ ነኝ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የሱዳን መከላከያ ሰራዊት በበኩሉ በዛሬው እለት በቃል አቀባይ ጽህፈት ቤቱ በኩል ጦርነቱን አስመልክቶ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በሱዳን ያለው ሁኔታ እየተረጋጋ መሆኑን እና የሱዳን ጦር የካርቱም የመኖሪያ አካባቢዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ከሱዳን ከማስወጣት ጋር በተያያዘ ከሀገራት መሪዎች ጋር ግንኙነት እየተደረገ መሆኑን እና የማስወጣት ሂደቱ አሁን ባለበት ሂደት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.1K viewsedited  04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 20:24:25 የነዳጅ ክፍያን በሲቢኢ ብር  እና አዲስ ይፋ በተደረገው ‘ነዳጅ’ በተሰኘ መተግበሪያ መክፈል ይቻላል፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ደንበኞች የነዳጅ ክፍያዎቸውን በሲቢኢ ብር  እና አዲስ ይፋ በተደረገው ‘ነዳጅ’ የተሰኘ መተግበሪያ መክፈል እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

ባንኩ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ የባንኩ ደንበኞች  በሲቢኢ ብር አማካኝነት በማንኛውም የስልክ አይነት፣ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች መክፈል እንደሚችሉ እና ለዚህም ዲጂታል ደረሰኝ እንደሚያገኙ ገልጿል።

ባንኩ ይፋ ባደረገው ‘ነዳጅ’ በተሰኘ መተግበሪያ መክፈል እንደሚቻልም ተጠቅሷል፤ ይህ መተግበሪያም ከደንበኞች የቁጠባ ሐሳብ ጋር የሚገናኝ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ባንኩ ለደንበኞቹ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና በቀላሉ የነዳጅ ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ ‘ሲቢኢ ብር’ እና ‘ነዳጅ’ መተግበሪያ ለዚህ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ደንበኞች እነዚያን አገልግሎት በመጠቀም ተጠቃሚ እንዲሆኑም አቤ ሳኖ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በሪኦ ሀሰን የነዳጅ ክፍያ በዲጂታል መከናወኑ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

Via:- EBC

@Leyu_News
@Leyu_News
4.7K views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 15:59:59 #ደብረብርሃን

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ፀጥታ ለማስጠበቅ ጥሎት የነበረውን ገደብ በከፊል ማንሳቱን አስታወቀ
የደብረ ብረሀን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማ አስተዳደሩን ሰላም ለማረጋገጥና የህግ የበላይነት ለማስከበር አስቀምጧቸው የነበሩ ክልከላዎች በከፊል ማንሳቱን አስታውቋል፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ከሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን የታወጁ ክልከላዎችን በማስፈፀም ከተማዋ ወደቀድሞ ሰላሟ እንድትመለስ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሃይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ለሁሉም የከተማው የፀጥታ መዋቅር አባላት እና ለከተማው ነዋሪዎች በሙሉ ምስጋና በማቅረብ የተጣሉ ክልከላዎችን በከፊል ከዛሬ ጀምሮ መነሳታቸውን አስታውቋል፡፡

የቀጠሉ ክልከላዎች

1. በከተማ አስተዳደሩ ከተፈቀደለት የፀጥታ አካል ውጪ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል ነው፡፡
2. የሰራዊቱን ሚሊተሪ አልባሳት ከሰራዊቱ አባላት ውጪ ለብሶ መንቀሳቀስ ክልክል ነው
3. ያለ ከተማ አስተዳደሩ ፈቃድ በተለያዩ አካባዎች በቡድን መሰባሰብ ለከተማው የሠላም ችግር መንስኤ ስለሚሆን ፍፁም ተከለከለ ነው፡፡

ከተማዋም በአሁኑ ሰዓት የቀደመ ሰላሟ ተመልሶ በፍፁም መረጋጋት ውስጥ ያለች እና ሁሉም የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ የሚገኙ በመሆኑ ሰላም ወዳዱ የደብረ ብርሃን ህዝብም አሁን ያለውን  ሰላም እንዲያስቅጥል እና ማንኛውንም የተለየና አዲስ እንግዳ የሆነ ነገር ሲያጋጥም እንደተለመደው ለፀጥታ ተቋማት ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክት ተላልፏል ማለቱን የከተማው ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
@Leyu_News
@Leyu_News
4.9K views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 15:50:20 ፓስተሩ ተይዟል።

በኬንያ ምስራቃዊ ክፍል ማሊንዲ በተሰኘችው ከተማ “ከተራባችሁ ከኢየሱስ ጋር ትገናኛላችሁ፤ ገነትም ትገባላችሁ” የሚል አስተምሮ ይዞ የመጣ ፓስተር የ47 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።በዚህ ድርጊቱ በፖሊስ ተይዟል።

በጫካ ውስጥ ተደብቀው ራሳቸውን ከምግብና ከውሃ አርቀው የተባሉትን ሲጠባበቁ የነበሩና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ፍለጋውም ቀጥሎ ትናንት የ26ቱ አስከሬን ተገኝቷል።

ከዚህ ቀደም የ21 ሰዎች አስከሬን መገኘቱን የሚያስታውሰው የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ፥ ይህም አጠቃላይ በዚሁ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ቁጥር 47 ያደርሰዋል ብሏል።

የማሊንዲ ከተማ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ሃላፊው ቻርለስ ካማኡ ግን ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችልና ፍለጋና ቁፋሮው መቀጠሉን ገልጸዋል።

ከሞቱት ባሻገርም በጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ በመራብ ውስጥ ፈጣሪያቸውን ለመመልከት የሚጠባበቁ ሰዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ በርካታ የሰው ሃይል አሰማርተን እየፈለግን ነው ብለዋል።

325 ሄክታር የሚሸፍነው ሻካሆላ የተሰኘው ጫካን እጅግ ሰፊ መሆኑ ግን የፍለጋ ስራውን ረጅም እንደሚያደርገው ነው የሚጠበቀው።
የኬንያ ፖሊስ የዚህን ሁሉ ችግር ምንጭ የ“ጉድ ኒውስ ኢንተርናሽናል ቸርች” መስራች ፓስተር ማኬንዚ ንቴንጌ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገበት እንደሚገኝ ተገልጿል።

ፓስተሩ ባለፈው ወርም በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረ ቢሆንም በ100 ሺህ የኬንያ ሽልንግ ወይም 700 ዶላር ዋስ መለቀቁን የአካባቢውን መገናኛ ብዙሃን ጠቅሶ ፍራንስ24 ዘግቧል።
ንቴንጌ ከስድስት ተከታዮቹ ጋር በድጋሚ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው ስለመጀመሩም ነው ዘገባው ያከለው።

የመብት ተሟጋቾች አሁንም የፓስተሩን አስተምሮ የሚከተሉ በርካታ ሰዎች መኖራቸውንና መንግስት በጫካ ውስጥ የተደበቁትን ፈጥኖ ደርሶ ካልታደጋቸው ህይወታቸውን የሚያጡት ቁጥር ሊያሳቅብ እንደሚችል ገልጸዋል።

የኬንያ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ኪቱሪ ኪንዲኪ በበኩላቸው፥ በቂ የጸጥታ ሃይሎች ወደ “ሻካሆላ” ጫካ መላካቸውንና ፍለጋውም ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

በነገው እለትም “የሞት ጫካ” ሲሉ ወደገለጹት አካባቢ እንደሚያመሩ ነው ያነሱት።
የሃይማኖት ነጻነትን እንደሽፋን በመጠቀም በአሳሳች አስተምህሮ የዜጎችን በህይወት የመኖር መብት የሚነጥቁ አካላት “የከፋ ቅጣት” ይጠብቃቸዋልም ብለዋል።

ምንጭ:— አል ዓይን አማርኛ
@Leyu_News
@Leyu_News
4.6K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 13:43:11 መንግስት ከኦነግ ሸኔ ጋር ለሚያደርገው ድርድር አምስት አባላት ያሉት የመንግሥት ተደራዳሪ ልዑክ ዛሬ ጠዋት ወደ ታንዛንያ (ዳሬሰላም) ማቅናቱ ተሰምቷል።

የሰላም ተደራዳሪ ልዑካን አባላት አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን ፣ዶክተር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፣ አቶ ከፍያለው አስራት ፣ጄነራል ደምሰው አመኑ፣ አቶ ቦንሳ እውነቱ ናቸው ተብሏል።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.2K views10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ