Get Mystery Box with random crypto!

የነዳጅ ክፍያን በሲቢኢ ብር  እና አዲስ ይፋ በተደረገው ‘ነዳጅ’ በተሰኘ መተግበሪያ መክፈል ይቻላ | LEYU NEWS

የነዳጅ ክፍያን በሲቢኢ ብር  እና አዲስ ይፋ በተደረገው ‘ነዳጅ’ በተሰኘ መተግበሪያ መክፈል ይቻላል፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ደንበኞች የነዳጅ ክፍያዎቸውን በሲቢኢ ብር  እና አዲስ ይፋ በተደረገው ‘ነዳጅ’ የተሰኘ መተግበሪያ መክፈል እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

ባንኩ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ የባንኩ ደንበኞች  በሲቢኢ ብር አማካኝነት በማንኛውም የስልክ አይነት፣ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች መክፈል እንደሚችሉ እና ለዚህም ዲጂታል ደረሰኝ እንደሚያገኙ ገልጿል።

ባንኩ ይፋ ባደረገው ‘ነዳጅ’ በተሰኘ መተግበሪያ መክፈል እንደሚቻልም ተጠቅሷል፤ ይህ መተግበሪያም ከደንበኞች የቁጠባ ሐሳብ ጋር የሚገናኝ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ባንኩ ለደንበኞቹ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና በቀላሉ የነዳጅ ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ ‘ሲቢኢ ብር’ እና ‘ነዳጅ’ መተግበሪያ ለዚህ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ደንበኞች እነዚያን አገልግሎት በመጠቀም ተጠቃሚ እንዲሆኑም አቤ ሳኖ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በሪኦ ሀሰን የነዳጅ ክፍያ በዲጂታል መከናወኑ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

Via:- EBC

@Leyu_News
@Leyu_News