Get Mystery Box with random crypto!

#ደብረብርሃን የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ፀጥታ ለማስጠበ | LEYU NEWS

#ደብረብርሃን

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ፀጥታ ለማስጠበቅ ጥሎት የነበረውን ገደብ በከፊል ማንሳቱን አስታወቀ
የደብረ ብረሀን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማ አስተዳደሩን ሰላም ለማረጋገጥና የህግ የበላይነት ለማስከበር አስቀምጧቸው የነበሩ ክልከላዎች በከፊል ማንሳቱን አስታውቋል፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ከሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን የታወጁ ክልከላዎችን በማስፈፀም ከተማዋ ወደቀድሞ ሰላሟ እንድትመለስ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሃይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ለሁሉም የከተማው የፀጥታ መዋቅር አባላት እና ለከተማው ነዋሪዎች በሙሉ ምስጋና በማቅረብ የተጣሉ ክልከላዎችን በከፊል ከዛሬ ጀምሮ መነሳታቸውን አስታውቋል፡፡

የቀጠሉ ክልከላዎች

1. በከተማ አስተዳደሩ ከተፈቀደለት የፀጥታ አካል ውጪ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል ነው፡፡
2. የሰራዊቱን ሚሊተሪ አልባሳት ከሰራዊቱ አባላት ውጪ ለብሶ መንቀሳቀስ ክልክል ነው
3. ያለ ከተማ አስተዳደሩ ፈቃድ በተለያዩ አካባዎች በቡድን መሰባሰብ ለከተማው የሠላም ችግር መንስኤ ስለሚሆን ፍፁም ተከለከለ ነው፡፡

ከተማዋም በአሁኑ ሰዓት የቀደመ ሰላሟ ተመልሶ በፍፁም መረጋጋት ውስጥ ያለች እና ሁሉም የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ የሚገኙ በመሆኑ ሰላም ወዳዱ የደብረ ብርሃን ህዝብም አሁን ያለውን  ሰላም እንዲያስቅጥል እና ማንኛውንም የተለየና አዲስ እንግዳ የሆነ ነገር ሲያጋጥም እንደተለመደው ለፀጥታ ተቋማት ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክት ተላልፏል ማለቱን የከተማው ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
@Leyu_News
@Leyu_News