Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-29 13:06:08
የባልደራስ ም/ፕሬዘዳንት አቶ አመሃ ዳኜው ከእስር ተለቀቁ!

ከመጋቢት 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ በግፍ እስር ላይ የቆዩት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት አቶ አመሃ ዳኜው ዛሬ በ30 ሺህ ብር ዋስ ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.3K views10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 12:16:18 መረጃ ቆቦ..!

ቆቦ ከተማ ላይ መረጃ እንዳይወጣባቸው ኢንተርኔቱን አጥፍተውታል።  መከላከያ ሌሊቱን ሙሉ በየቤቱ እየዞረ ሲፈትሽ አድሯል። ከተማ ውስጥ የባጃጅም ሆነ ምንም አይነት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም። አስፓልት መውጣትም አይቻልም። ገበሬውም ከብቶቹን ለግጦሽ ማስወጣት አልቻለም።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.8K views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 11:24:47
ፍርድ ቤቱ "ስፐርሚነተር" የተባለውን ሰው የዘር ፈሳሽ እንዳይሰጥ ከልክሏል።

ሰውየው ከዚህ ቀደም በለገሰው የዘር ፈሳሽ 600 ልጆችን አፍርቷል።

በኔዘርላንድስ ዮናታን የተባለ የ41 ዓመቱ ሰው የወንድ የዘር ፈሳሽን በመለገሱ “ስፐርሚነተር” የሚል ቅጽል ስም አግኝቷል።

ነገር ግን በመጋቢት ወር አንዲት ሴት በሀገሪቱ ውስጥ የዝምድና አደጋ ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት ስላደረባት ከሰሰችው።

በህጉ መሰረት አንድ የዘር ለጋሽ ቢበዛ 12 ሴቶችን ማስረገዝ ይችላል ነገርግን ዮናታን ከዛ እጥፍ እጥፍ ለግሷል።።

በኔዘርላንድስ ከተከለከለ ሁሉንም ሰውዬው ወደ ኬንያ በመሸሽ የወንድ የዘር ፍሬውን በኢንተርኔት ለሌሎች ሀገራት ለሚገኙ ሰዎች ሸጧል።

ፍርድ ቤቱ አሁን ግለሰቡ በሽርክና የሰራባቸውን ክሊኒኮች በሙሉ በማነጋገር ቀሪዎቹን ናሙናዎች እንዲያወድሙ ትእዛዝ ሰጥቷል።

ዮናታን እንደገና የዘር ፍሬ ፈሳሽ ሲለግስ ከተያዘ እስከ 100 ሺህ ዩሮ ቅጣት ይጠብቀዋል ሲሉ የኔዘርላንድስ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑ ዘግበዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.0K views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 08:49:43
የኢንተርኔት አገልግሎት ላለፉት ሁለት ሳምንታት መቋረጡ በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሚገኝ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ፡፡

አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ከመምህራን የሚሰጣቸውን የቤት ሥራም ሆነ በግላቸው የሚፈልጉትን ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት መቸገራቸውን ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን ከየካቲት ወር ጀምሮ በመላ አገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ቢሆንም፤ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ግን አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በወልድያ፣ በቆቦ እና በአላማጣ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ሪፖርተር

@Leyu_News
@Leyu_News
2.6K views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 21:09:59 በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አለፋ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ300 በላይ ቤቶች ወደሙ

በአለፋ ወረዳ በመንገላ አቫጅውሃ ቀበሌ ሮብ ገበያ ከተማ ከትላንት በስትያ በተከሰተ ድገተኛ የእሳት ቃጠሎ ከ300 በላይ የመኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ድርጅቶች መዉደማቸዉ ተገለጸ፡፡

ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎው የተከሰተው ሚያዚያ 16/2015 ከቀኑ 5 ሰዓት አካባቢ ሲሆን፤ በጥንቃቄ ጉድለት ከግለሰብ ቤት የተነሳ መሆኑ ተነግሯል።

በአደጋው ከ300 በላይ የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ደርጅቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መውደማቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ኮማንደር በጋሻው ሽባባው አስታውቀዋል፡፡

ቃጠሎውን በቀላሉ ለመቆጣጠር ያልተቻለው በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ አውሎ ነፋስ እንደነበርና ቤቶች ተጠጋግተው በመሰራታቸው አደጋው የከፋ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡

በቃጠሎው የደረሰውን የንብረት ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ተጣርቶ በቀጣይ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን የገለጹት ኮማንደር በጋሻው፤ ወቅቱ ነፋሻማ አየር የሚያይልበት በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የወረዳው አደጋ መከላከልና መልሶ ማቋቋም ክትትል ባለሙያ አንባየ ይግዘው በበኩላቸው፤ በቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸው አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋም ግብዓት በነፃ ብድር ሊመቻችላቸው እንደሚችል አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል የወረዳው ቀይ መስቀል ቅ/ጽ/ቤት ተወካይ አስተባባሪ አዲሱ ምልክት፤ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በመለየት ለሚመለከታቸው አካላት መረጃውን በማድረስ ሃብት በማፈላለግ ተጎጅዎችን በዘላቂነት ማቋቋም እንደሚቻል መግለጻቸውን አዲስ ማለዳ ከወረዳው ያገኘችው መረጃ አመላክቷል፡፡

በእሳት ቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸው የህብረሰብ ክፍሎችም ዕለታዊ የምግብ ፍጆታና ቁሳቁሶች እርዳታ እንዲደረግላቸው መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
3.6K views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 21:09:34
3.3K views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 21:09:34
3.2K views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 20:29:45
በሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ቢራዘምም ውጊያው ቀጥሏል!

የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ አቁሙን ለማራዘም የተስማሙ ቢሆንም ትናንት ተዋጊ ጄቶች ዋና ከተማዋ ካርቱም ያሉ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ይዞታዎች ደብድበዋል።

የጦር ሰራዊቱ እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በተደጋጋሚ ሲጣስ የነበረውን የተኩስ አቁም እንዲያራዝሙ ሳውዲ አረቢያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ግፊት ማድረጋቸውን ተከትሎ ጥቂት ሰዐት ሲቀረው በተጨማሪ 72 ሰዐት ለማራዘም መስማማታቸውን ይፋ አድርገዋል።

ውጊያው እንዲቆም ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ የውጭ አካላት ተወካዮች በተኩስ አቁሙ መራዘም መደሰታቸውን ገልጸዋል።የአፍሪካ ህብረት፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፥ ሳውዲ አረቢያ፥ የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች፥ ብሪታኒያ እና ዩናይትድ ስቴትስ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

"ሁለቱ ወገኖች ይበልጡን ዘላቂ በሆነ መንገድ ግጭቱ እንዲቆም ወደሚያስችል ንግግር ለማምራት ብሎም የሰብዐዊ ረድዔት ያለእንቅፋት መግባት ለማስቻል ዝግጁ መሆናቸው አስደስቶናል" ብለዋል።በተያያዘ ዜና ትናንት ተዋጊ አውሮፕላኖች በዋና ከተማዋ ሰሜናዊ ጠርዝ አካባቢ ሲበሩ እንደነበር የመድፍ እና የከባድ አውቶማቲክ መሳሪያ ተኩስም ይሰማ እንደነበር ዕማኞች ገልጸዋል።

ነገ ቅዳሜ ሁለት ሳምንት በሚደፍነው የሱዳን ውጊያ ቢያንስ 512 ሰዎች ሲገደሉ 4193 መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚንስቴር መረጃ ያሳያል።ዳርፉር ውስጥም ውጊያው ማገርሸቱን ዘገባዎች አመልክተዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.5K views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 14:56:07 ኢትዮጲያ በሱዳን የተቀሰቀሰው ግጭት ተከትሎ ግብረ ሃይል አቋቋመች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በዛሬው እለት የሚኒስቴሩን ሳምንታዊ የስራ ማብራሪያና ከጋዜጠኞች ለተናነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።በሱዳን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሱዳን ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ጋር እና ከፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሀይሎች መሪ ዳጋሎን ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አምባሳደር መለስ አለም ተናግረዋል።

ለሱዳን ህዝብ ሰላም እንዲመጣ ሁለቱ መሪዎች እድል  መስጠት እንደሚያስፈልጋቸው እና የውስጥ ችግር ለመፍታት በቂ አቅም ያላቸው ስለመሆናቸው  በስልክ ውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ  ተናግረዋል።ከሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተየያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመ ግብረ ሃይል መኖራቸውን ባለሙያዎች እስከ ጋራ ድንበር ተልከው እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር መለሰ ተናግረዋል።

ግጭቱ ኢትዮጵያ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ለማድረግ፣ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዜጎች ካሉ በምን መልኩ እናስተናግድ በሚል እና ዜጎች የቆንስላ አገልግሎት እያገኙ ወደሃገራቸው እንዲመጡ ግብረ ሀይሉ ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል።ሱዳን ውስጥ ከ 100 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን አሉ ሁሉም ዜጎች ሰላም እንዲሆኑ እንሰራለን ብለዋል። እስካሁን በ100 የሚቆጠሩ  የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ከሱዳን በኢትዮጵያ ስለማለፋቸውም ጨምረው ተናግረዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.0K views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 14:53:51
የፓርላማ አባል ዶክተር ሀንጋሳ ኢብራሂም  "ካልገደሉን፤ ገዳዩን እናጋልጣለን" እያለ ነው። የፃፈውን ከታች ለጥፌዋለሁ።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.8K views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ