Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-30 19:16:01 በነገው እለት በአደባባይ ሊከበር የነበረው የላብ አደሮች  ቀን ተሰረዘ!

ዓለም አቀፍ የላብአደሮችን ቀን በማስመልከት በነገው እለት በአደባባይ ሊከበር የነበረው ክብረ በዓል መሰረዙ ተሰምቷል።

የኢትዮጲያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ቀኑን በአደባባይ ማክበር እንደማንችል የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ  አሳውቁናል ብለዋል።

አቶ ካሳሁን እንዳሉት (ሜይዴይ) የላብ አደሮች  ቀን ሚያዚያ 23/2015  ሠራተኛውን የተመለከተ መልእክቶችን በማስተላለፍ በአደባባይ ለማክበር ታስቦ እንደነበር አንስተዋል።

ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በአሉ በአደባባይ እንዳይከበር መከልከሉን ነግረውናል።የኢትዮጲያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን የአደባባይ ክብረ በዓሉ መሰረዙን ተኮትሎ በቀጣይ ሊኖሩ የሚችሉ ሂደቶችን እንደሚያሳውቅም ገልጸዋል።

[Ethio FM]

@Leyu_News
@Leyu_News
3.6K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 17:18:16 በወላይታ ዞን ዉሃ ለመቅዳት ወንዝ የወረደ ታዳጊ በጅብ ተበላ

በወላይታ ዞን ዉሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ የወረደዉ ታዳጊ በጅብ መበላቱን በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በዞኑ ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር መሐል ክፍለ ከተማ ጨዉ ካሬ ተብሎ በሚጠራዉ መንደር  ነዋሪ የሆኑ ታዳጊዎች ተሰባስበዉ ዉሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ መዉረዳቸዉ ተነግሯል።ውሃ ለመቅዳት ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ ወደ ወንዝ ከወረዱ ታዳጊዎች መካከል እዩ መንግስቱ የተባለዉ የ10 ዓመት ህፃን በጅብ መበላቱን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

የ10 አመቱ ታዳጊ ጅብ ይዞት ሲሮጥ የተመለከቱት ጓደኞቹ  ሸሽተዉ ወደ ሰፈር በመመለስ መረጃዉን ማድረሳቸዉ ተከትሎ  ህብረተሰቡ  የታዳጊዉን ህይወት ለማትረፍ ወደ ስፍራዉ አቅንቶ ታዳጊዉን  ለመታደግ  የተደረገዉ ጥረት ሳይሳካ መቅረቱ ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል

በተመሳሳይ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ዋዱ ቀበሌ ሚያዝያ  14 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ሰዓት አካባቢ አከታትሎ በጣለዉ ከባድ  ዝናብ ምክንያት በጨዋታ ላይ የነበሩ የ7 እና የ9 ዓመት ሁለት ህፃናት በጎርፍ መወሰዳቸውን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።

ዳጉ ጆርናል

@Leyu_News
@Leyu_News
4.0K views14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 11:53:47
ይህንን ያውቆ ኖሯል ?

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ1997 እስከ 2018 ባሉት ዓመታት ከፍተኛ የአህያ ቁጥር እድገት ካሳዩት አስር ሀገራት አንዷ ነበረች።

በጠቅላላ የአህያ ቁጥር ደግሞ በዓለም ቀዳሚውን ስፍራ እንደምትይዝ ተመላክቷል።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.3K views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 10:35:48
ከአላማጣ በተነሱ መንገደኞች ላይ በመተሀራ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

ከሰሜን ኢትዮጵያ አላማጣ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ነበረ የተባለ፣ የኛ ባስ በተሰኘው የህዝብ ማመላለሻ ላይ ባለፈው ሐሙስ ሚያዚያ 19/2015 ምሽት 12፡30 አካባቢ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ሹፌሩ እና ረዳቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን በቦታው የነበሩ ተሳፋሪዎች ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከአምስት ያላነሱ ተጓዦች ቁስለኛ ሆነው አዳማ ከተማ ለሕክምና መወሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ከተሳፋሪዎች ጋር አብረው ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ የነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ነዋሪዎች አክለዋል።

ጥቃቱ አድራሾቹ የተኩስ እሩምታ ከፍተው ጉዳት ያደረሱትም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በመተሀራ እና በወለንጭቲ ከተማ መሀል ላይ ነው ተብሏል።

ጥቃቱ ከተፈጸመ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ቁጥራቸው ከአምስት የማይበልጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ቦታው መድረሳቸውን የገለጹት የዓይን እማኞች፤ በየኛ ባስ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ በሚኒ ባስ ይጓዙ የነበሩ ሰዎችን አግተው ሲወስዱ ተመልክተናል ብለዋል፡፡

ጥቃት አድራሾች የተወሰኑት መደበኛ ሌሎች ደግሞ ወታደራዊ ልብስ የለበሱ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ መንገደኞች እነዚህ ኃይሎች የሸኔ ታጣቂዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ገምተዋል።

ተሳፋሪዎች ከአላማጣ በቆቦ መገንጠያ አድርገው በአፋር በርሃ በኩል ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ እንደነበር ጠቅሰው፤ "የሰው ህይወት እንዲህ ተራ ሲሆን እና በሚዲያዎችም ሆነ በመንግስት ምንም ሳይባል መቅረቱ ያሳዝናል።" ሲሉ ተደምጠዋል።

በሳሙኤል ታዴ

@Leyu_News
@Leyu_News
4.3K viewsedited  07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 09:42:27
የግርማ የሺጥላ አስከሬን ሽኝት በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው!

የአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ የነበሩት የግርማ የሺጥላ አስከሬን የክብር ሽኝት በወዳጅነት አደባባይ በመከናወን ላይ ይገኛል።በክብር ሽኝት ሥነ ስርዓቱ ላይም የፌደራል እና የክልል የሥራ ሃላፊዎች የግርማ የሺጥላ የሥራ ባልደረቦች፣ እንዲሁም ወዳጅ ቤተሰቦቹ የተገኙ ሲሆን፤ የአስክሬን ሽኝቱም በከፍተኛ ወታደራዊ ሥርዓት በመከላከያ እና በፌደራል ፓሊስ ማርች ባንድ አጃቢነት እየተካሄደ ነው፡፡

ሽኝቱ በወዳጅነት አደባባይ ከተካሄደ በኃላም በቤተሰቦቻቸው ጥያቄ መሰረት፤ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ መሃል ሜዳ ነገ ሰኞ ሚያዝያ 24/2015 ይፈጸማል፡፡ግርማ የሺጥላ ወ/ጻዲቅ ከእናታቸው ከወ/ሮ ዘውዴ ስመኝ እና ከአባታቸው የሺጥላ ወልደጻዲቅ በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሃገር በመንዝና ግሼ አውራጃ በጌራ ምድር ወረዳ መሃል ሜዳ ከተማ ህዳር 17/1967 መወለዳቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ከ25 ዓመታት በላይ በተለያዩ የመንግሥት የሥራ ሃላፊነት ቦታዎች ላይ በትጋትና በታማኝነት ያገለገሉት ግርማ፤ ሐሙስ ሚያዚያ 19/2015 ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን በመጓዝ ላይ ሳሉ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ በተወለዱ በ48 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ግርማ የሺጥላ ባለትዳር ሲሆኑ የሦስት ሴት እና የአራት ወንድ ልጆች አባት ነበሩ፡፡

[Addis Maleda]

@Leyu_News
@Leyu_News
4.0K views06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 08:31:44
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዛምቢያ በተካሄዱ የታዳጊዎች እና የወጣቶች አትሌቲክስ ውድድሮች ድል አደረጉ!!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዛምቢያ ንዶላ በተካሄዱ የታዳጊዎች እና የወጣቶች አትሌቲክስ ውድድሮች በመጀመሪያው ቀን ድል አድርገዋል።

በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች ከ20 ዓመት በታች በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

በዚህም

➦አትሌት አስማረች አንለይ በአንደኝነት የወርቅ ሜዳሊያ ስታጠልቅ፣

➦አትሌት የኔዋ ንብረት 2ኛ በመሆን የብር እንዲሁም

➦አትሌት ዓይናዲስ መብራቱ በሦስተኝነት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.1K views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 21:47:52
#AxumUniversity

በጦርነት ምክንያት አክሱም ዩኒቨርሲቲ አቁሟቸው ነበሩትን አገልግሎቶች ማስጀመሩን ለማወቅ ተቸሏል።

ዩኒቨርሲቲው ለቀድሞ ተማሪዎቹ ፦
➭ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት
➭ ስቱደንት ኮፒ
➭ ጊዚያዊ ሰርተፊኬት
➭ የዲግሪ ማረጋገጫ
➭ እንግሊዝኛ የማስተማሪያ ቋንቋነት ማረጋገጫ መስጠት መጀመሩን ገልጿል።

በመሆኑም የቀድሞ ተመራቂዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በዩኒቨርሲቲው በአካል በመገኘት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በሁለት ወይም በሦስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ኦሪጅናል ዲግሪ መስጠት እንደሚጀምር አሳውቋል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት በትግራይ ጦርነት ምክንያት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ስራ ለማስጀመርና ተማሪዎቹን ለመቀበል ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ችለናል።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.5K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 19:53:24
#MoE #ExitExam

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በመጪው ሀምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች #በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከ240 ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል። 

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ድግሪ የማይሰጣቸው በመሆኑ ተማሪዎች ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን አንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በሀምሌ ወር ከሚሰጠው ፈተና በፊት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የሙከራ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ በኦንላይን ፈተናው መሰጠቱ ኩረጃን ለማስቀረት፣ የወረቀት ወጪና ማጓጓዣን ለመቀነስ ይረዳል ብሏል።

ለፈተናው በአጠቃላይ ከ15 በላይ ኮርሶች በየትምህርት መስኩ ተወጣጥተው ዝግጁ መሆናቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ " የፈተናው ውጤት በኦንላይን ይፋ የሚደረግና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ይሆናል " ብሏል።

ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ያለገደብ በተደጋጋሚ የመፈተን እድል እንደሚኖራቸው በመመሪያ መቀመጡን ያስታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር " የመውጫ ፈተናው የተለየ ዓላማ የሌለው እና የተማሩትን ብቻ የሚመዝን በመሆኑ ተማሪዎች ሳይደናገጡ እንዲዘጋጁ ለተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመፈተኛ ጣቢያ እንደሚሆኑ ይፋ ተደርጓል።

#ኢብኮ

@Leyu_News
@Leyu_News
4.6K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 16:05:57
የተናቁት አባላቱ ወይስ ኢትዮጵያ?

ለውድድር ዛምቢያ የደረሱ የኢትዮጵያ አትሌትቲክስ ቡድን አባላት መሬት ተኙ መባላቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

በአፍሪካ ከ18 እና ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚወዳደረው የታዳጊና ወጣት ቡድን ዛሬ በዛምቢያ ንዶላ ቢገኝም ቡድኑ መኝታ በማጣት እስከ ለሊቱ 6:30 ድረስ ማረፊያ አላገኘም ሲል ፌደሬሽኑ ገልፆአል።

በማያያዝም ቡድኑን ከውድድሩ ስፍራ ከ65 ኪሜ በላይ ርቆ እንዲሄድ ተደርጓል ያለው ፌዴሬሽኑ ሆኖም ከፈለጋችሁ መሬት ላይ ልትተኙ ትችላላችሁ ብለውናል ሲልም ነው ፌደሬሽኑ ያስታወቀው።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.6K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 16:05:36
4.4K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ