Get Mystery Box with random crypto!

በወላይታ ዞን ዉሃ ለመቅዳት ወንዝ የወረደ ታዳጊ በጅብ ተበላ በወላይታ ዞን ዉሃ ለመቅዳት ወደ | LEYU NEWS

በወላይታ ዞን ዉሃ ለመቅዳት ወንዝ የወረደ ታዳጊ በጅብ ተበላ

በወላይታ ዞን ዉሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ የወረደዉ ታዳጊ በጅብ መበላቱን በደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በዞኑ ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር መሐል ክፍለ ከተማ ጨዉ ካሬ ተብሎ በሚጠራዉ መንደር  ነዋሪ የሆኑ ታዳጊዎች ተሰባስበዉ ዉሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ መዉረዳቸዉ ተነግሯል።ውሃ ለመቅዳት ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ ወደ ወንዝ ከወረዱ ታዳጊዎች መካከል እዩ መንግስቱ የተባለዉ የ10 ዓመት ህፃን በጅብ መበላቱን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

የ10 አመቱ ታዳጊ ጅብ ይዞት ሲሮጥ የተመለከቱት ጓደኞቹ  ሸሽተዉ ወደ ሰፈር በመመለስ መረጃዉን ማድረሳቸዉ ተከትሎ  ህብረተሰቡ  የታዳጊዉን ህይወት ለማትረፍ ወደ ስፍራዉ አቅንቶ ታዳጊዉን  ለመታደግ  የተደረገዉ ጥረት ሳይሳካ መቅረቱ ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል

በተመሳሳይ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ዋዱ ቀበሌ ሚያዝያ  14 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ሰዓት አካባቢ አከታትሎ በጣለዉ ከባድ  ዝናብ ምክንያት በጨዋታ ላይ የነበሩ የ7 እና የ9 ዓመት ሁለት ህፃናት በጎርፍ መወሰዳቸውን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።

ዳጉ ጆርናል

@Leyu_News
@Leyu_News