Get Mystery Box with random crypto!

በነገው እለት በአደባባይ ሊከበር የነበረው የላብ አደሮች  ቀን ተሰረዘ! ዓለም አቀፍ የላብአደሮች | LEYU NEWS

በነገው እለት በአደባባይ ሊከበር የነበረው የላብ አደሮች  ቀን ተሰረዘ!

ዓለም አቀፍ የላብአደሮችን ቀን በማስመልከት በነገው እለት በአደባባይ ሊከበር የነበረው ክብረ በዓል መሰረዙ ተሰምቷል።

የኢትዮጲያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ቀኑን በአደባባይ ማክበር እንደማንችል የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ  አሳውቁናል ብለዋል።

አቶ ካሳሁን እንዳሉት (ሜይዴይ) የላብ አደሮች  ቀን ሚያዚያ 23/2015  ሠራተኛውን የተመለከተ መልእክቶችን በማስተላለፍ በአደባባይ ለማክበር ታስቦ እንደነበር አንስተዋል።

ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በአሉ በአደባባይ እንዳይከበር መከልከሉን ነግረውናል።የኢትዮጲያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን የአደባባይ ክብረ በዓሉ መሰረዙን ተኮትሎ በቀጣይ ሊኖሩ የሚችሉ ሂደቶችን እንደሚያሳውቅም ገልጸዋል።

[Ethio FM]

@Leyu_News
@Leyu_News